Tuesday, October 21, 2014

Top 10 Best Airports in the World

For travelers weary of long lines at security checkpoints and overpriced fast food, the idea that any airport could be viewed as “best” may seem laughable. However, for travelers lucky enough to have flights that originate or end at any of the airports listed below, the word “best” is totally appropriate. These outstanding airports received the most votes from more than twelve million travelers who participated in a survey administered by Skytrax. Awards for the 2013 World’s Best Airport and nine runners-up were announced at passenger terminal EXPO in Geneva, Switzerland. The winning airports were located largely in Europe and Asia, with only one representative from North America and none from Australia, South America or Africa.  The United States was also notably absent from the list of winners.

Thursday, May 29, 2014

ዘመቻ ዘ ኃማ


የህያዉነት ልህቅ
ልህቃዊ መልህቅ
ሰማያዊ ሀዘን ዘለግላጋ እንባ
የወረደ ክብር የቅለት ክብር ካባ
የሃማ ወዳጅ ሰሞናዊ ፍቅር
የሰዉ ክብር ናፍቆት የስንፍና ሊጤ ወንበር
የዝህ ሁሉ ርቀት
የሀሳብ ጓዝ ዥረት
ለንጉሱ
    ምላሱ
ለመኳንንቱ
     ሹመቱ
መሆን ነበር
   የኃ/ማ ምኞቱ
ግና
ትናንት
      መርዶዉኪዮስክ
       ጥቅመኛዉ ሰርክ
       ምንም ሳያቆመዉ ወንበሩን ሳይሰጠዉ
        ኅወሀት ያሳጣዉ ሳይጀመር ያለቀዉ
        የዘመቻዉ መሪ
                           የንጉሱ አሽከር
                        ዘማሪዉ  ኃ/ማ ነዉ።                          

                    xayouluma

Monday, March 31, 2014

እኔ የምጨነቀው ስለአፋር እንጂ ስለ ጎሳ አይደለም”


ለመጀመሪያ ጊዜ የመጣችው በ1966ቱ ድርቅ በበጎፈቃደኝነት ሲሆን አሁን በቋሚነት ኑሮዋ አፋር ነው፡፡ በልጅነቷ ቤተሰቦቿ ከእንግሊዝ  ወደ አውስትራሊያ ሲሄዱ በመርከብ ቀይባህርን ማቋረጧን የምታስታውሰው ቫለሪ፤እጣ ክፍሌ እዚህ መሆኑን ባውቅ ኖሮ፣ያኔውኑ ከመርከቧ እወርድ ነበር ትላለች፡፡ ቫለሪ ብራውኒንግ  ስለ ህይወቷ የሚተርክ መፅሐፍ አሳትማለች፡፡
ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ኤልሳቤት እቁባይ ጋር ሰመራ ላይ የተገናኘችው ቫለሪ፤ በአስገራሚ ታሪኮች ስለተሞላው ህይወቷ እንዲህ አውግታለች፡፡

ቫለሪ ማን ናት?
እኔ በትውልድ እንግሊዛዊት፣ በዜግነት አውስትራሊያዊ፣ በጋብቻ እና በኑሮ ኢትዮጵያዊት ነኝ፡፡ ሰባት ወንድሞች እና እህቶች አሉኝ። አውስትራሊያ ከሚገኝ ኮሌጅ በነርስነት እና በአዋላጅነት ሙያ ተመርቄያለሁ፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት መጣሽ?  

የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋብቻና ፍቺ አልተጣጣመም!

  • Written by  ኤልያስ 


  • ኢትዮ-ቴሌኮም በኖኪያ ቁጥጥር ስር የነበሩ የኔትዎርክ ወረዳዎችን ነፃ አወጣ!
  • አንድነት እና መኢአድ ሳይጋቡ በመፋታት ሪከርድ ሰብረዋል
  • “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ትዝ የሚላቸው ምርጫ ሲቃረብ ነው

        የአፍሪካ አንድነት የሰላም አስከባሪ ኃይልን የተቀላቀለው የአገራችን መከላከያ ኃይል ሶማሊያ ውስጥ አልሻባብ ተቆጣጥሯቸው የነበሩትን ቦታዎች ማስለቀቁን በኢቴቪ ዜና እወጃ ላይ ሰምቼ ደስ ብሎኝ ነበር (ኢትዮጵያዊ ሆኖ ድል የማይወድ አለ እንዴ?) በነጋታው ነው መሰለኝ … ሌላ የምስራች ደግሞ ሰማሁ፡፡ ኢትዮ-ቴሌኮም በኖኪያ ቁጥጥር ስር የነበሩትን አየር ጤና፣ ቄራና ዓለም ባንክ አካባቢዎች ነፃ ማውጣቱ ተነገረ-በዜና ሳይሆን በተባባሪ ወሬ፡፡ እናላችሁ …. ሁለቱ አካባቢዎች አሁን ኔትዎርካቸው ያለመቆራረጥ እየሰራ ነው፤ ተብሏል (ኢንተርኔትና ፌስቡክም ያለችግር ማግኘት ችለዋል) ኢትዮ-ቴሌኮምን የማሳስበው ግን በዚህ የድል ብስራት ተኩራርቶ ሌሎቹን በቁጥጥር ስር ያልዋሉ የኔትዎርክ ወረዳዎች ነፃ ከማውጣት እንዳይዘናጋ ነው። ያለዚያ እኮ የሦስቱ አካባቢዎች ነፃ መውጣት ትርጉም የለውም (ተመልሰው በ“ጠላት እጅ” ሊወድቁም ይችላሉ!) እናላችሁ … ሌሎች የመዲናዋ አካባቢዎችም ከ “ባዕድ እጅ” ነፃ ሲወጡ ነው እነ ዓለም ባንክ ነፃነታቸውን በቅጡ የሚያጣጥሙት፡፡ እስከዛ እኮ እርስ በርስ ብቻ ነው ኮሙኒኬሽኑ!

ለኔትዎርኩና ለመብራቱ መጥፋት “አዋቂ” ጋ ብንሄድ ይሻላል!!

  • Written by  ኤልያስ 


  • ጐዳና የሚያፀዳ መኪና በማስመጣት ከአፍሪካ ቀዳሚ አይደለንም
  • ካሜሩን ከ11 ዓመት በፊት አስመጥቻለሁ ብላለች
  • ታንዛንያ ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ነኝ ባይ ናት
      እናንተ… ያ የማሌዥያ (እየበረረ የጠፋ) አውሮፕላን እስካሁን እኮ አልተገኘም፡፡ እኔ የምለው---የዓለም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሁኔታ ጥርጣሬ አልፈጠረባችሁም? አንዴ ቻይና ትነሳና በሳተላይት ሦስት የአውሮፕላን ስብርባሪም ባህር ውስጥ ወድቆ አይቻለሁ…ትላለች፡፡ (እስካሁን አንዲትም ስባሪ አልተገኘም!) ቬትናምም እንዲሁ አንዳች ነገር ያየሁ ይመስለኛል ብላለች (ቅዥት ነው እንዴ?) አሁን ደግሞ አውስትራሊያ አካባቢ በሳተላይት ስብርባሪ እንደታየ ተሰምቷል፡፡ ነገርየው እኮ ግራ ያጋባል። የአውሮፕላኑ ባለቤት የማሌዥያ መንግስትም በሳይንስና ቴክኖሎጂው ግራ ቢገባው ጠንቋይ ጋ ሄዶ ስለአውሮፕላኑ ጠየቀ ተብሏል፡፡ (ከሳተላይት ጠንቋይ ይሻለኛል ማለት እኮ ነው!)

የአድባራት አስተዳዳሪዎች ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት መፈረጃቸው ሊቃነ ጳጳሳቱን አስቆጣ


ቅሬታቸውን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ገልጸዋል

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ በኾኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዐት እንዲማሩ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በማቀናጀት ሞያዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ በማስተባበር ላይ የሚገኘውን ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት በመፈረጅ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካይነት ጠቅላላ ሀብቱና ንብረቱ የሚታገድበት ውሳኔ እንዲተላለፍ በመንግሥትም በኩል እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአድባራት አስተዳዳሪዎች መግለጫ አውጥተውበታል በተባለው ስብሰባ ጉዳይ ኹለት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ለከፍተኛ የመንግሥት ሓላፊዎች ቅሬታቸውን ማሰማታቸው ተገለጸ፡፡
የቅ/ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስንና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን በስም የጠቀሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች፣ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች እንደኾነ ቢገልጹም የሓላፊዎቹን ስም ከማሳወቅ ተቆጥበዋል።

ኢህአዴግ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት? አሜሪካ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ለመውጣት ወስናለች

ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ብቸኛ ተዋናይና ፊት አውራሪ አድርጎ ራሱን የሾመው ኢህአዴግ ለቀጠናው ስጋት እንደሚሆን ተጠቆመ። አልሸባብንና አልቃይዳን ከምንጩ እናጠፋለን በሚል ስትራቴጂ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ሰምጣ የነበረችው አሜሪካ ከጉድጓዱ ለመውጣት ወስናለች። ኢትዮጵያዊያን የሚያምኑትና የሚቀበሉትን መሪ በድፍረት አደባባይ የማውጣት ሃላፊነቱ “አገር ወዳድ” በሚሉ ዜጎችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጫንቃ ላይ ነው።
ህወሃት ያቋቋማቸው ጥቃቅን መንግስታት ከህዝብ ይልቅ ለህወሃት የወደፊት እቅድ ታማኝ በመሆን መጓዛቸው ከቀን ወደቅን የፈጠረው ስሜት ኢህአዴግን እየበላው እንደሆነ የጠቆሙ የዜናው ምንጮች፣ ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪቃ የሰላም አባት ሊሆን ቀርቶ የራሱንም ችግር መፍታት ወደማይችልበት የቁርሾ ማሳ ውስጥ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
ህወሃት “በነጻ አውጪነት” ያሰላውና፣ ይህንኑ ዓላማውን በፈለገበት ቀን ተግባራዊ ለማድረግ ያመቸው ዘንድ በየክልሉ ለጣጥፎ ያቋቋማቸውን ፓርቲዎች ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ በድንገት ካለፉ በኋላ ኢህአዴግ ውስጣዊ ሰላሙ መናጋቱ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። ኢህአዴግ በበኩሉ “የጓድ መለስን ውርስና ራዕይ ያለማዛነፍ እናስቀጥላለን” እያለ አገሪቱን በደቦ እንድተመራ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
አቶ መለስ በጓዶቻቸው ቋንቋ “ተሰው” ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ምክትል ጠ/ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ለመተካት ተቸግሮ ነበር። ደህንነቱን፣ መከላከያውን፣ ፖሊስና ዋንኛ የአገሪቱን ተቋማት ጠቅልሎ የያዘው ህወሃት በቀጥታ አሜሪካ ባደረገችው ጫና ሳይወድ በግዱ አቶ ሃይለማርያምን በጠ/ሚኒስትርነት ለመሰየም ተገደደ። የስልጣን ክፍተቱን በተመለከተ አቻ ድርጅቶችና ህወሃት ውስጥ አለመግባባት ተፈጥሮ ስለነበር “ምደባ” በሚል ኢትዮጵያ በደቦ የሚመሯት አራት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተሰየሙላት።

ኢህአዴግ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት? አሜሪካ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ለመውጣት ወስናለች

ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ብቸኛ ተዋናይና ፊት አውራሪ አድርጎ ራሱን የሾመው ኢህአዴግ ለቀጠናው ስጋት እንደሚሆን ተጠቆመ። አልሸባብንና አልቃይዳን ከምንጩ እናጠፋለን በሚል ስትራቴጂ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ሰምጣ የነበረችው አሜሪካ ከጉድጓዱ ለመውጣት ወስናለች። ኢትዮጵያዊያን የሚያምኑትና የሚቀበሉትን መሪ በድፍረት አደባባይ የማውጣት ሃላፊነቱ “አገር ወዳድ” በሚሉ ዜጎችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጫንቃ ላይ ነው።
ህወሃት ያቋቋማቸው ጥቃቅን መንግስታት ከህዝብ ይልቅ ለህወሃት የወደፊት እቅድ ታማኝ በመሆን መጓዛቸው ከቀን ወደቅን የፈጠረው ስሜት ኢህአዴግን እየበላው እንደሆነ የጠቆሙ የዜናው ምንጮች፣ ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪቃ የሰላም አባት ሊሆን ቀርቶ የራሱንም ችግር መፍታት ወደማይችልበት የቁርሾ ማሳ ውስጥ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
ህወሃት “በነጻ አውጪነት” ያሰላውና፣ ይህንኑ ዓላማውን በፈለገበት ቀን ተግባራዊ ለማድረግ ያመቸው ዘንድ በየክልሉ ለጣጥፎ ያቋቋማቸውን ፓርቲዎች ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ በድንገት ካለፉ በኋላ ኢህአዴግ ውስጣዊ ሰላሙ መናጋቱ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። ኢህአዴግ በበኩሉ “የጓድ መለስን ውርስና ራዕይ ያለማዛነፍ እናስቀጥላለን” እያለ አገሪቱን በደቦ እንድተመራ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
አቶ መለስ በጓዶቻቸው ቋንቋ “ተሰው” ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ምክትል ጠ/ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ለመተካት ተቸግሮ ነበር። ደህንነቱን፣ መከላከያውን፣ ፖሊስና ዋንኛ የአገሪቱን ተቋማት ጠቅልሎ የያዘው ህወሃት በቀጥታ አሜሪካ ባደረገችው ጫና ሳይወድ በግዱ አቶ ሃይለማርያምን በጠ/ሚኒስትርነት ለመሰየም ተገደደ። የስልጣን ክፍተቱን በተመለከተ አቻ ድርጅቶችና ህወሃት ውስጥ አለመግባባት ተፈጥሮ ስለነበር “ምደባ” በሚል ኢትዮጵያ በደቦ የሚመሯት አራት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተሰየሙላት።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምሬታቸውን ለፓርላማ አሰሙ

በሕይወቴ ያለምቾት የሠራሁበት ወቅት አሁን ነው›› የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሀብትና ንብረትን ለመጠበቅና ለማስተዳደር ሲባል ‹‹ራሳችንንና ቤተሰቦቻችንን ችግር ውስጥ ከተናል›› በማለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ለፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ምሬታቸውን ገለጹ፡፡
የኦዲት አገልግሎት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢና በሥሩ የሚገኙ ተቋማት ላይ ከ1999 እስከ 2002 ዓ.ም. ባለው ሒሳብ ላይ ያካሄደውን ኦዲትና የኦዲት ግኝቶችን አስመልክቶ ማብራርያ እንዲሰጡ፣ ባለፈው ዕለት በፓርላማው የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተጠርተው በተወቀሱበት ወቅት ነው አመራሮቹ ምሬታቸውን የገለጹት፡፡
በዋናው ግቢ ከልዩ ልዩ የተሰብሳቢ ሒሳብ መሰብሰብ የሚገባው 80.7 ሚሊዮን ብር ለረዥም ጊዜ መንከባለሉን፣ የሚሰበሰብ ከሆነም ከማን እንደሚሰበስብ አለመታወቁ፣ በዋናው ግቢ በግዥ ቅድመ ክፍያ ተከፍሎ የመጀመርያው ሳይወራረድና ሳይረጋገጥ ድጋሚ የግዥ ቅድሚያ ክፍያ በተለያዩ አቅራቢዎች ተመዝግቦ መገኘቱና ለረዥም ጊዜ ያልተወራረደ ሒሳብ በድምሩ 29.8 ሚሊዮን ብር

የማሕበረ ቅዱሳን የመጨረሻዎቹ ቀናት – ከተመስገን ደሳለኝ


                   
በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የሚመራው መንግስት ከናቅፋ እስከ ጉና ተራራ ያሉ ምሽጎቻቸውን ከሰማይ በጦር አይሮፕላን፣ ከምድር እሳት በሚያዘንቡ ቢ.ኤሞችና መድፎች ሳያቋርጥ ደበድብም፤ በሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን ግዛታቸውን እያሰፉ የተጠናከሩት ‹‹ወንበዴዎች›› ራስ ምታት ሆነውበታል፡፡ የኤርትራ ‹‹ነጻ አውጪ›› ቤዝ-አምባው በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለጥቃት የመጋለጥ እድሉ አናሳ በሆነው የሳህል በረሃ በመሆኑ አብዛኛው የአመራር አባል መሸሸጊያው አድርጎታል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ አካባቢ የሚንቀሳቀሱት የወያኔ መሪዎች ምሽጋቸው እንደ ሳህል ምቹ ባለመሆኑ፤ በርካታ ክፉ ቀናትን ያሳለፉት በተራራማ አካባቢዎች በሚገኙ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ገዳማት ውስጥ ተደብቀው እንደሆነና ከቦታ ቦታ መዘዋወር ሲፈልጉም የመነኮሳቱን አልባሳት ይጠቀሙ እንደነበረ በትግሉ ዙሪያ የተዘጋጁ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ በተለይም ታጋይ መለስ ዜናዊ፣

የፍትሕ ሚኒስቴር ታሪካዊ ዳራ

ፍትሕ ሚኒስቴር አሁን ያለውን ስያሜ ከመያዙ በፊት የተለያዩ መጠሪያዎችን በመያዝ አወቃቀሩም ሆነ አደረጃጀቱ በየጊዜው ለውጦች ሲካሄዱበት መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የሚኖረው አደረጃጀት ያለፈባቸውን ሥርዓተ ማህበራትና ቅርፀ መንግስታት አሠራርና ይዘት በሚያንፀባርቅ መልኩ የተደራጀ ሲሆን ይህም በተለይ ከዳኝነት ሥርዓቱ ጋር እስከ ቅርብ ጊዜያት የነበረው ቁርኝት ለዚህ አመላካች ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ስለሆነም ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርነው ሁሉ ይህ ፅሁፍ የፍትሕ ሚኒስቴር ከየት ተነስቶ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደቻለ፣በየወቅቱ ሲከተላቸው  የነበሩ አሠራሮች ምን እንደሆኑ፣እንዲሁም አሁን ያለው አወቃቀርና የደረሰበት ደረጃ  ከዚህ ቀጥሎ ለማየት እንሞክራለን፡፡
ሀ. ፍትሕ ሚኒስቴር እስከ ደርግ ውድቀት

Monday, March 24, 2014

ኃይሌና ጌጤ በሽልማት ገቢ የኢትዮጵያን አትሌቶች ይመራሉ

የዓለም አትሌቶች በጎዳና ላይ ሩጫዎችና በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ባገኙት የሽልማት ገቢ  ከ1 እስከ 50  በወጣው ደረጃ ኢትዮጵያ  በሁለቱም ፆታዎች  በ23 አትሌቶች እንደተወከለች ለማወቅ ተቻለ፡፡ ከኢትዮጵያ አትሌቶች በሽልማት ገቢያቸው ኃይሌ ገብረስላሴ እና ጌጤ ዋሚ ይመራሉ፡፡ ባለፉት 15 ዓመታት  በዓለም ዙርያ በተካሄዱ የጎዳና ላይ ሩጫዎች እና ሌሎች የአትሌቲክስ ውድድሮች አትሌቶች ያገኙአቸውን በግልፅ የሚታወቁ  የገንዘብ ሽልማቶች በመደመር ደረጃውን ከሳምንት በፊት  በድረገፁ ይፋ ያደረገው የጎዳና ላይ ሩጫዎች የስታትስቲክስ ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ማህበር

ኢትዮጵያዊቷ ተመራማሪ አለማቀፍ የሳይንቲስቶች ሽልማት ተቀበሉ

                                                                               Written by  አንተነህ ይግዛው


የሎሬትነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል

         ኢትዮጵያዊቷ ተመራማሪ ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ፣ በተለያዩ የምርምር መስኮች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ምርጥ የአለማችን ሴት ሳይንቲስቶች በየአመቱ የሚሰጠው የሎሪያል ፋውንዴሽንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አለማቀፍ የሴት ሳይንቲስቶች ሽልማት የ2014 ተሸላሚ ሆኑ፡፡
ተቀማጭነቱን  በናይሮቢ ኬኒያ ያደረገው ‘ኢንተርናሽናል ሴንተር ፎር ኢንሴክት ፊዚዮሎጂ ኤንድ ኢኮሎጂ’ የተባለ አለማቀፍ ተቋም ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሰገነት ቀለሙ፤ አፍሪካንና የአረቡን አለም በመወከል ተሸላሚ መሆናቸውን ሲስኮን ሚዲያ የተባለው የፈረንሳይ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡  ዶ/ር ሰገነት ለ16ኛው የሎሪያል ፋውንዴሽንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አለማቀፍ የሴት ሳይንቲስቶች ሽልማት የበቁት፣ በእጽዋት ምርምር ዘርፍ ባደረጉት ጥናት በተለይ አነስተኛ ይዞታ ባላቸው አርሶአደሮች ዘንድ ስነ-ምህዳርን የማይጎዳ የሰብል አመራረት ዘዴ ለማስፋፋት ሁነኛ መፍትሄ የሚለግስ ተጨባጭ ውጤት በማግኘታቸው እንደሆነ

20 ዓመት ሙሉ ውህደትና ጥምረት ያልሰመረለት የተቃዋሚ ጎራ

                                                                              Written by  ኤልሳቤጥ እቁባይ እና አለማየሁ አንበሴ




የሐሙሱ የመኢአድና አንድነት ውህደት ሳይጀመረ ፈረሰ
ምርጫን ብቻ ግብ ያደረጉ ጥምረቶች ዋጋ አይኖራቸውም
የፓርቲዎች ውህደት ባይሳካም የተገኘው ልምድ ቀላል አይደለም
ለተቃዋሚዎች አለመጠናከር ኢህአዴግ ተጠያቂ ነው
“በሀገራችን የፓርቲ ፖለቲካ ብዙ ዘመን አስቆጥሯል ማለት
ባይቻልም በአሁኑ ጊዜ ፓርቲዎች ማደግ ሲገባቸው እየቀጨጩ ነው፣ በሜዳው ላይ መኖር የማይገባቸው ፓርቲዎችም አሉ፡፡ ፕሮግራማቸው አንድ ሆኖ እንኳ ተከፍለው መንቀሳቀሳቸው ትክክለኛ አካሄድ ካለመሆኑ በተጨማሪ ለገዥው ፓርቲም የስልጣን እድሜን እየሰጠ ነው ያሉት ከዚህ ቀደም በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራረርነት ቆይተው አሁን ላይ ከፓርቲ ፖለቲካ ራሳቸው ያገለሉት ዶ/ር ያዕቆብ ሃ/ማርያም ናቸው፡፡

Tuesday, March 4, 2014

የቀልድ - ጥግ

የፖለቲካ ቀልዶች
ትርጓሜ
“የፖለቲካ ቀልዶች ችግር አንዳንዴ እንደባለቤቶቻቸው ሊመረጡ መቻላቸው ነው”
*   *   *
የፖለቲከኛ ትርጉም
ፖለቲከኛ ማለት ጀልባዋን ራሱ ነቅንቆ፣ አናግቶ ሲያበቃ፤ ከዚያ እያንዳንዱን ሰው እባህሩ ላይ ማዕበል ተነስቷል ብሎ ለማሳመን የሚችል ሰው ነው!
*   *   *
የየምርጫ ጣቢያ ትርጉም
የምርጫ ጣቢያ ማለት ገንዘባችሁን የሚያጠፋላችሁን ሰው የምትመርጡበት ቦታ ነው!
*   *   *
አንድ የሩሲያ መሪ ወደ አሜሪካ መጥቶ የአሜሪካን ወታደሮች እንዲጎበኝ ይጋበዛል። በዚሁ መሠረት ወደ አሜሪካ ጣና ወታደሮቹን ይጐበኝ ጀመር፡፡
የአሜሪካው መሪ፡- “ወታደሮቼ ለእኔና ለአገሬ በጣም ታማኝ ናቸው” አለው ለሩሲያዊው፡፡
የሩሲያው መሪ፡- “እስቲ አንዱን ወታደር ጥራልኝና ጥያቄ ልጠይቀው” አለ
አንድ ወታደር ተጠራና መጣ፡፡
ይሄኔ ሩሲያዊው ወደ አሜሪካኑ ዞሮ፤
“እስቲ ታማኝነቱን ለማረጋገጥ ከገደል አፋፍ ውድቅ በለው” አለው፡፡
የአሜሪካው መሪም ለወታደሩ “በል ከዚህ ገደል ወደ መሬት ተወርወር” አለና አዘዘ፡፡
ወታደሩም፤ “አላደርገውም ጌታዬ” አለው
መሪው፤ “ለምን?”
ወታደሩ፤ “በእኔ ሥር የሚተዳደሩ ብዙ ቤተሰቦች አሉኝ ጌታዬ” አለ፡፡

መብራት ሃይል የመ/ቤቴን “ኪራይ ሰብሳቢዎች” ታገሉልኝ እያለ ነው!

  • Written by  ኤልያስ 
  • ከኑሮ ውድነት ጋር እንታገል ወይስ ከ“ኪራይ ሰብሳቢዎች” ጋር?
  • መንግስት እኮ ታክሲ ተሳፍሮ አያውቅም--- (መንግስት መሆን አማረኝ!)
  • የጋዜጠኞች ማህበራቱ  “ፀረ-ነውጥ” ድርጅት ቢያቋቁሙ ይሻላቸዋል!

እኔ የምላችሁ … እነዚህ የጋዜጠኞች ማህበራት አሁንም እዚሁ ጦቢያ ናቸው እንዴ? እኔማ ባለፈው ጊዜ  በኢትዮጵያ “የፕሬስ ነፃነት ከየትኛውም የአፍሪካ አገር በተሻለ ተከብሯል፤ አንድም በሙያው የተነሳ የታሰረ ጋዜጠኛ የለም” የሚል መግለጫ ከሰጡ በኋላ (ኢህአዴግ እኮ ይቀረናል ነው ያለው!) አንድ ስማርት የሆነች አይዲያ አቅርቤላቸው ነበር፡፡ (ኦሪጂናል እኮ ናት!) ማህበራቱ ጦቢያ ውስጥ የፕሬስ ነፃነት በሽበሽ ነው ካሉ በኋላ እዚህ ምን ይሰራሉ አልኩና አዲስ ወደ ተቋቋሙ የአፍሪካ አገራት (እንደ ሶማሌና ደቡብ ሱዳን የመሳሰሉ) ሄደው የጋዜጠኞች ማህበራት ቢያቋቋሙና ለጋዜጠኞች መብት ቢታገሉ “አህጉራዊ የነፃነት ታጋይ” የሚል ማዕረግ ይቀዳጃሉ ብዬ እኮ ነው (የአፍሪካ ቼጉቬራ ሆኑ ማለት እኮ ነው!)
ከአህጉራዊ የጋዜጠኞች

“የአብዮተኛው ትውልድ” የተሸፋፈነ ኪሳራ

ኪሳራው በጊዜ ሲሰላ፣ የአገሪቱን የስልጣኔ ጭላንጭል ያዳፈነ፣ የ30 ዓመት የኋሊት ጉዞ ነው።
30 ዓመት ቀላል አይደለም፤ እነ ደቡብ ኮሪያ ከድህነት ወደ ብልፅግና የተሸጋገሩበት ጊዜ ነው።
“የአብዮተኛው ትውልድ”ን ኪሳራዎችን ለመደበቅ ተብሎ ብዙ ታሪክ ተድበስብሷል
ትምህርት የተስፋፋው፣ የሴት ተማሪዎች ቁጥር ያደገው ከአብዮቱ በፊት ነው ወይስ በኋላ?
የኤሌክትሪክ፣ የስልክ፣ የመንገድና የአየር ትራንስፖርት በፍጥነት የተሻሻለውስ መቼ ነው?
በእህል ምርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በኤክስፖርት መስኮች የብልፅግና ምልክት የታየውና የጠፋውስ?
የሙያ ፍቅር ያበበው፤ ስነፅሁፍ፣ ትያትርና ሙዚቃ ያደገው፤ ስፖርት የተሻሻለው መቼ ይሆን?

የአርሲ ጉዞዬ አስደናቂ ማስታወሻ 2

 

 Written by  ነቢይ መኮንን 

 

 የአርሲ ጉዞዬ አስደናቂ ማስታወሻ
(ካለፈው የቀጠለ)
ከ38 ዓመት በኋላ አስከሬናቸው የተገኘው የፊዚክስ ባለሙያው የዶክተር ሙሉጌታ በቀለ አባት የፊታውራሪ በቀለ ኦገቶ አስደማሚ የአስከሬን ማሳረፍ ሥነ ስርዓት በሳጉሬ ወረዳ/አርሲ/
የጉዳዩ ጭብጥ፤
ፊታውራሪ በቀለ ኦገቶ በደርግ መንግስት ከሌሎች 16 ወዳጆቻቸውና ዘመዶቻቸው ጋር በግፍ ተገድለው አስከሬናቸው ዘመድ ወዳጅ እንዳያውቅ፣ እንዳያገኝ ተደርጎ፤ በደርግ መንግስት አረመኔነት፤ የተጣሉበት ሳይታወቅ ለ38 ዓመታት ቆይቷል፡፡
ይሁን እንጂ በልጆቻቸው በተለይም በዶ/ር ሙሉጌታ በቀለ ጥንካሬና ፅናት፤ የተሞላበት የረጅም ጊዜ ፍለጋ፤ ታህሳስ 17/2006 ዓ.ም በአሰላ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አፅማቸው ተቆፍሮ ተገኝቷል፡፡
ሁኔታው ለዘመድ ወዳጆቻቸው፣ ለአገር ሽማግሌዎችና አብረዋቸው ለተሰዉ ሰማእታት ቤተሰቦች ታህሳስ 28/2006 ዓ.ም ይፋ ተደረገ፡፡
አፅሙን በክብር ለማሳረፍ በዘመዶቻቸው፤ በወዳጆቻቸው፣ በሰማእታቱ

Thursday, February 27, 2014

የአፍሪካ መሪዎችና አማፅያን በሩሲያዊው የክላሺንኮቭ ፈጣሪ ህልፈት አዝነዋል!




    ክላሺንኮቭ (AK-47) የተባለውን ለሁሉም ሥፍራ ተስማሚና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ  የጦር መሣሪያ በመፈልሰፍ፣ ለመላው ዓለም “እነሆ በረከት” ያሉት ሩሲያዊው “ጀግና” ሚካሄል ክላሺንኮቭ፤ ባለፈው ሰኞ በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ማዘኔ አልቀረም፡፡ (የአፍሪካ መሪዎችና አማፅያን ባለውለታ መሆናቸውን እንዳትረሱት!) በነገራችሁ ላይ ሰውየው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በልብ ችግር ሲሰቃዩ የቆዩ ሲሆን ለአንድ ወር ያህል በሆስፒታል ተኝተው የህክምና ክትትል ቢደረግላቸውም ከመሞት አልዳኑም፡፡ እሳቸውስ የእድሜ ባለፀጋ ናቸው - በ94 ዓመታቸው ነው የሞቱት፡፡ እሳቸው በሰሩት ክላሺንኮቭ ሲጠዛጠዙ በለጋ እድሜያቸው የተቀጩ አፍሪካውያንን ራሷ አፍሪካ ትቁጥረው!!  ሚኻኤል ክላሺንኮቭ በለጋ እድሜያቸው የእርሻ መሣሪያ የመሥራት ህልም ነበራቸው፡፡ (ህልሙ ነፍስ ሳይዘራ ቀረ እንጂ!) የማታ ማታም በዝነኛው ክላሺንኮቫቸው በዓለም ላይ እህል ሳይሆን ምስቅልቅል ቀውስ ዘሩበት፡፡ በህይወት ሳሉ የጦር መሣሪያ በመስራት ለህዝቦች ደም መፋሰስ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ሰላም ይነሳቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ የተጠየቁት ሚኻኤል ክላሺንኮቭ “እኔ እንቅልፌን ስለጥጥ ነው የማድረው፡፡ መስማማት አቅቷቸው የጦርነት አማራጭን የሚወስዱት ፖለቲከኞች ናቸው ተጠያቂዎቹ” በማለት ራሳቸውን ነፃ አድርገዋል (ከደሙ ንፁህ ነኝ እንደማለት!)

    የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሰራር ፈተና ላይ ወድቋል!

    ከተመሰረተ ስልሳ አምስት አመቱን ያስቆጠረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ አለምአቀፋዊ ተቋምነቱ እና የብዙዎችን ይሁንታ ያገኘበት ሀላፊነቱ በተግባር በሚያከናውነው ስራ አንፃር ሲመዘን ጥያቄ ላይ የወደቀ ድርጅት ነው፡፡ አሁን በሀላፊነት ላይ ያሉት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ ባን ኪ ሙን የመንግስታቱን ድርጅት የመለወጥ ሀሳብ በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡ ነገር ግን፣ ድርጅቱን በዋና ፀሀፊነት ካገለገሉ ስምንት ሰዎች ውስጥ አንዱ ብቻ ናቸው ስለ ለውጥ ምንም ተናግረው የማያውቁት፡፡ የተወሰኑ ለውጦች በተለያዩ ጊዜዎች የተደረጉ ቢሆንም፣ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ግን ምንም አይነት ለውጥ አለመደረጉ ጥያቄዎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲበረቱ አድርጓል፡፡
    በድርጅቱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች የአባል አገሮቹን ያህል የበዛ እና የተወሳሰበ ቢሆንም፣ በማሻሻያዎቹ ላይ ጥናት ያደረገው ዛክ ቱከር፣ ጥያቄዎቹን በሶስት ዋና ዋና ምድቦች ይከፍላቸዋል።

    “የህወኀት ዓላማ ግቡን አልመታም”

    አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ፤ ከህወኀት መስራቾች አንዱ)
    የካቲት 11 ይዛችሁ የተነሳችሁት አላማ ምን ነበር?
    እኛ በዛን ወቅት ይዘነው የተነሳነው አላማ፣ ደርግን በሰላማዊ መንገድ መጣል ስለማይቻል፣ በትጥቅ ትግል ገርስሰን እንደ መሬት ላራሹ ያሉ የህዝብ ጥያቄዎችን መመለስ ነበር፡፡ የመጀመሪያ አቋማችን የዘውዳዊውንና የደርግን ህገመንግስት መቀየር የሚል ሲሆን አቋሙ በማኒፌስቶ ፅንሰ ሀሳብ ላይ የተነደፈ አልነበረም፡፡ በቁርጥራጭ ወረቀትና በቃል ነበር የተያዘው፡፡ በሶስትና አራት ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ስልሳ ሰባት ሰው ትግሉን ተቀላቀለ፡፡ መጀመሪያ ላይ ሃገራዊ፣ ብሄራዊና መደባዊ ትግል በማካሄድ ህዝባዊ መንግስት መመስረት የሚል ዓላማ የነበረ ሲሆን ከአመራሩ አካባቢ ደግሞ “እኛ የምንታገለው ከአማራ ቅኝ ገዢዎች ነፃ ለመውጣት ነው፤ ስለዚህ ዓላማችን ነፃ ሪፐብሊክ ትግራይን መመስረት ነው” የሚሉ ሀሳቦች መፍለቅ ጀመሩ። ከአንድ ዓመት በኋላ ሃሳቡ በህወኀት መሪዎችና ለእነሱ ቅርበት በነበራቸው ታጋዮች ተረቀቀና በማኒፌስቶ ወጣ፡፡ አቶ ስዩም መስፍን ሱዳን ውስጥ አሳትመው አመጡት፡፡

    የአርሲ ጉዞዬ አስደናቂ ማስታወሻ

                                                                                                  Written by  ነቢይ መኮንን

     ከ38 ዓመት በኋላ ከመቃብር የወጣው አስከሬን ትርዒት

    የፊዚክስ ባለሙያው የዶ/ር ሙሉጌታ በቀለ አባት የፊታውራሪ በቀለ ኦገቶ አስከሬን እንዴት ተገኘ? ዝርዝሩ ብዙ ነው፤ ጉዳዩ ግን ተዓምር ተባለ!

    ወደ አርሲ አሰላ - ሳጉሬ መንገድ የጀመርነው ቅዳሜ የካቲት 8 ቀን 2006 ዓ.ም ከንጋቱ ለአንድ ሩብ ጉዳይ ነው፡፡
    ከናዝሬት .. ወደ ሶደሬ አቅጣጫ … መልካሰዲ ስንደርስ ወደ ቀኝ ዞረን ዴራ፣ ኢቲያን አልፈን በብቅል ፋብሪካ አድርገን አሰላ ገባን፡፡ ከዚያ ወዲያ እንግዲህ ከ 23 ኪ.ሜ በኋላ ሳጉሬ ወረዳ ልንሄድ ነው፡፡
    ወደ ሳጉሬ ከመሄዳችን በፊት ወደ አሰላ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መሄድ ዋንኛው የመርሀ-ግብሩ መነሻ ነው፡፡ ለምን? ታሪኩ እዚህ ጋ ይጀምራላ፡፡
    38 ዓመት የፈጀው አስከሬን ለምን ይሄን ያህል ጊዜ ፈጀ? ሂደቱ ምን ይመስላል? ከመጨረሻው ትርዒት ጀምረን ወደ ኋላ 38 ዓመት እንጓዛለን፡፡