Wednesday, November 18, 2015

ጠ/ሚ ኃይለማርያም የኮንሶን ውዝግብ ለማጣራት ቃል ገቡ

- በአካባቢው የሚታየው ውጥረት ግን ቀጥሏል፤


ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሰገን አካባቢ ዞን የኮንሶ ወረዳ ሕዝብ ከመዋቅር ጥያቄ ማቅረብ ጋር በተያያዘ ደረሱብኝ ያሏቸውን ችግሮች ለማጣራት ቃል ገቡ።
የኮንሶ ሕዝብ በዞን ደረጃ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በቅርቡ በይፋ ከማቅረቡ ጋር ተያይዞ የክልሉ መንግሥት ባሰማራው ልዩ ኃይል ወታደሮች እየተወሰዱ ያሉ ኢ-ሰብአዊ እርምጃዎችን በመቃወም ከአካባቢው ኅብረተሰብ የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎችና በኅብረተሰቡ የተመረጡ የኮሚቴ አባላት ጥቅምት 29 ቀን 2008 ዓ.ም አቤቱታቸውን ለጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅርበዋል።
ጠ/ሚኒስትሩም የኮንሶን ሕዝብ አቤቱታ በጽ/ቤታቸው ከተቀበሉ በኋላ ወዲያውኑ ከተወካዮቹ ጋር በስልክ የተነጋገሩ ሲሆን፤ በዚህም ንግግር አንድ ቡድን በማቋቋም ሁኔታው እንዲጣራ እንደሚያደርጉ ለተወካዮቹ አረጋግጠውላቸዋል።
ከኮንሶ ለአቤቱታ ወደ አዲስ አበባ የመጡት ተወካዮች ለጠ/ሚኒስትሩ በፃፉት ደብዳቤ፤ የኮንሶ ሕዝብ የመዋቅር ጥያቄ በሠላማዊ መንገድ አቅርቦ ምላሹን በጉጉት እየጠበቀ ባለበት በዚህ ሰዓት፣ ጥያቄውን በማቅረባቸው ብቻ የክልሉ ልዩ የወታደር ኃይል በማሰማራት ሰዎችን ወደ ማሰር፣ ማስፈራራት፣

Monday, November 16, 2015

Now you will change you profile picture......

here is the link that changes your profile picture via the flags of

Syria, Iraq, Turkey, Lebanon, Pakistan, Yemen, Nigeria, Cameroon, Bahrain, Russia, France, Egypt, Algeria, Afghanistan, Libya, Chad, Kenya.

click the link  xayouluma 


Sunday, November 15, 2015

ረሃብ ስንት ቀን ይፈጃል?
ረሃብ ቀጠሮ ይሰጣል?
ወይስ ቀን ቆጥሮ ይፈጃል?
"የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል"
ያባላል ድሮም ይባላል
ይዘለዝላል ይከትፋል
ብቻ እስከምጨርስ ድረስ፤ ሆድ ለሆድ ጊዜ ይሰጣል

ወተት አንጀት ነጥፎ ሲላብ
ሆድቃ ደርቆ ሆድ ስራብ
ተሟጦ አንጀት ላንጀት ስሳብ...........
የጣር ቀጠሮ ስንት ነዉ
ለሰዉ ልጅ ሰዉ ለምንለዉ
ላይችል ሰጥቶት ለምያስችለዉ
ስንት ቀን ነዉ ? ስንት ለት ነዉ ?........
የማዕዱ ወዝ  ሳታጥጥ
አድባሩ አብዳ ሳትፈረጥጥ
ጥንብ ሳይተርፍ ሜዳ አይጥ
የቤት ድመት ሳታማምጥ
በእመቤቷ አስከሬን ብካይ
እሷም ዋይ ዋይ
ዉሻም በጌታ ስጋ ላይ
ቸነፈር በጣለዉ ስ ሳይ
አይ!...............
ስንት ቀን ትሁን የረሃብ አዋይ?.......
እስቲ እናንተ ተናገሩ፤ተርባችሁ የምታዉቁ
ከቸነፈር አምልጣችሁ፤ተርፋችሁ እንድሁ ሳታልቁ
ትንፋሽ ቀርቷችሁ እንድሆን፤ ያስችላችሁ እንደሆን ጥቂት
 ቀጠሮ ይሰጣል እልቂት?.
ስንት ምልዓት? ስንት ለሊት?
ጥንብ አንሳዉ ሳይወርድ በፊት፤ ሳይሞዠርጣችሁ ጥፍሩ
በጣረ ሞት አክናፋቱ፤አንዣቦ በመቅሰፍት እግሩ
አንደበት ተርፍዋችሁ እንድሁ ሳትነግሩ ከምትቀሩ
ካስቻላችሁ ተናገሩ።
ቆሽት ሲቃዉ ላያጣጥር፤ሰቀቀኑ ሳያጋግል
እስትንፋስ ስልምልም ሳትል
ቀጠሮ ይሰጣል ረሃብ ለስንት ቀን ለስንት ያህል
ስንት ስዓት ነዉ የረሃቡ አቅሙ?
ለ'ኔ ብጠማ ትርጉሙ
የሁለት ፊደል ድምጽ ነዉ ራብ የሚሉት ከነስሙ
እንጂ የ'ኔ ብጠዉማ
የት አዉቆት ጸባዩንማ
ብቻ ሲነገር ይሰማል
ይህን ሁለት ፊደል ቃል.............
ቃሉማ ያዉ በዘለማድ፤ ይነገራል ይለፈፋል
ይተረካል ይዘከራል
ይደጋግማል ይተቻል
እንጂ እንኳን ጠባዩን፤ የራብ ዕድሜዉን የት ያዉቃል..........
እና እምታዉቁት ንገሩን፤እዉነት ራብ ስንት ቀን ይፈጃል?..........
በጣር አፋፍ ላይ ያልህ ሰዉ፤ ራብ እንደት ነዉ እምያዛልቅ
ለስንት ቀን ቀን ይሰጣል፤አንደበትክን ላይሸመቅቅ
ሸረሪት በልሳንህ ላይ፤ የድር ትብትቡን ሳይሰራ
ቁራና ቀበሮ በቀን፤ ከቀየህ ድባብ ሳይደራ
ጥንብ አንሳ ልጭር ሳይመጣ፤ቅምቡርስ ከጎጆህ ጣራ
እንደፍካሬ ኢየሱስ ቃል፤ በጣር ምጽዓት ሳትጣራ
አንደበት ሳለህ ተናገር
የምታዉቅ የራብ ነገር
አስከረንክ ከየጥሻዉ፤ተርፎ እንድሁ ሳይቀረቀር
ስንት ደቂቅ ስንት ፋታ፤ ቀጠሮዉ ስንት ትንፋሽ ነበር
ቆሽት አርሮ ሳይፈረፈር
ትናጋህ በድርቀት ንዳድ፤ ጉሮሮህ ሳይሰነጠር?........
የሆድ ነገር ስንት ያቆያል
ቀጠሮ ይሰጣል እልቂት?.
ስንት ምልዓት? ስንት ለሊት?
ስንት ስዓት ነዉ ሰቆቃዉ፤ስንት ደቂቃ ነዉ ጭንቁ
እስቲ እናንተ ተናገሩ፤ተርባችሁ የምታዉቁ
ስንት ያቆያል ስንት ያዘልቃል?..........
እዉነት ራብ ስንት ቀን ይፈጃል?


ጸጋዬ ገብረ መድህን
 ጥር ፲፱፻፷፭
ዋልዲያ

ተርበዉ ለምያቁ ትሁንልኝ


ማርክ ዙከርበርግ ስለ ፓሪስ ምን አለ???


ማርክ ዙከርበርግ በማን አለብኝነት የሁላችሁንም የፌስቡክ ገጽ በፈረንሳይ ባንዲራ አቅልሙልኝ ስል በጠየቀዉ መሰረት አብዛኛዉ ያበረከተልን ዉለታ በማሰብ ነዉ መሰል ትዕዛዙን ተቀብለዉታል እኔና መሰሎቸ ግን አሁንም ከመከራከርና አይመለከተኝም በማለት አምጸንበታል ምናልባት በጉልበት ካልዘጋብን በስተቀር ምንም አያመጣብንም ብየ አስባለሁ። የሆነዉ ሆኖ ዙከርበርግ ለፓሪስ የተለየ ፍቅር እንዳለዉ አሳይቶናል።የከዝ ህ ቀደሙ ስቀር ፓሪስ በፈነዳች ማግስት በሩት እነም ዜጎቸን አጥታለሁ ስለዝክ ለነም የሴፍቲ መከታተያ ያስፈልገኛል ስትል በዉድ የፌስቡክ ተጠቃሚዎቿ አማካይነት ጠይቀዋለች፣ የኛ ልጆችም እንደታ ህዝባችን በረሃብ እያለቀብን ስለሆነ ዙከርበርግ ለምን የሃበሻ ረሃብተኞችን አይጠይቀንም ስሉ ተሟግተዋል። ዘዉትር ብዙ ልብ ያዘለዉ ሃበሻም ስማችን ዳግም በረሃብ አይነሳ ስል ስምዋገት ዉሎ አምስትዋል፤ በርግጥ ገጽታ ግንባታ ለላ ነገር ብሆንም ሰባዊ የርዳታ ጥሪ መቅደም አለበት ይላል የዝህ ጽሁፍ አሰናኝ። የከኒያ ጋሪሳ ተማሪዎች፣ የሶርያ ከ 150ሺ በላይ ሰላማዊና ንጹሃን ዜጎች፣ ኔፓል ከ 50ሺ በላይ ዜጎቿን በተፈጥሮ አደጋ, ራሺያ ከ 200 በላይ ዜጎቿ ሲናይ በረሀ ላይ ሰሞኑን ሲያቁ, የማላዚያ  ምስኪን መንገደኞች እና ሌሎች የ አፍሪካና የአረብ ሟቾች ከማርክ ዙከርበርግ አይን ያልገቡበት ምክኛት ይኖር ይሁን ወይ ስል አሰናኙ ኳዮሉማ ሃሳቡን ይሰነዝርላችኃል።

Saturday, November 14, 2015

ዉጪ ሆኘ

ዉዴ፤
አንቺ ጓዳ ሆነሽ ወዴ ዉስጥ ስትገቢ፣

እኔ ግን፤
በተቃራኒሽ ስጓዝ ስለኔ አታስቢ።

እደጅ ላይ ሆኘ እጥብቅሻለሁ፣
ከዉስጥ ስትዘጊ እታገስሻለሁ።
ከዉጪ ሆኘ ደጁን ዘግቼ፣
በፊት የነበርኩበትን ደጁን ዘግቼ።
ዉጪ ሆኘ እደጅ እወጣለሁ፣
አንቺ እስክትመጪ እደጅ እሆናለሁ።

ኻዮሉማ/xayouluma

which one is created?

which one is mutated?
which one is created?
    to live peacefully gifted
    to stay in love warned
which one is mutated or created?
     to us commanded
     the one is created
    the rest are mutated

the mutated are planned
the created one is respected
is earth mutated or planned?
are the rest created or gifted?

    xayouluma

ሽብር ያለዉ ወድህ ነዉ፣

የፓሪስ ፍንዳታ ሽብር አይደለም፣
ጠግቦ መሞትን የመሰለ የትም ክብር የለም።

ያምስት ደቂቃ ዳንኪራ
፲ ዘላለም ነዉ በተስታ ስሰላ/ራ።
በልቶ ጠጥቶ ሳይራብ የምያልፍ፣
በሰዉ በሰይጣን በዲያብሎስም የምያርፍ፣
ቀኑ ነዉ እምባል ነፍሱ ከስጋዉ ስከንፍ።

ሽብር ያለዉ ወድህ ነዉ፣
ማረፊያዉም ቆቦ ነዉ።

ከጓሮዉ አፍጦ፣
ከተራራዉ አንጋጦ፣