ክላሺንኮቭ (AK-47) የተባለውን ለሁሉም ሥፍራ ተስማሚና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ የጦር መሣሪያ በመፈልሰፍ፣ ለመላው ዓለም “እነሆ በረከት” ያሉት ሩሲያዊው “ጀግና” ሚካሄል ክላሺንኮቭ፤ ባለፈው ሰኞ በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ማዘኔ አልቀረም፡፡ (የአፍሪካ መሪዎችና አማፅያን ባለውለታ መሆናቸውን እንዳትረሱት!) በነገራችሁ ላይ ሰውየው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በልብ ችግር ሲሰቃዩ የቆዩ ሲሆን ለአንድ ወር ያህል በሆስፒታል ተኝተው የህክምና ክትትል ቢደረግላቸውም ከመሞት አልዳኑም፡፡ እሳቸውስ የእድሜ ባለፀጋ ናቸው - በ94 ዓመታቸው ነው የሞቱት፡፡ እሳቸው በሰሩት ክላሺንኮቭ ሲጠዛጠዙ በለጋ እድሜያቸው የተቀጩ አፍሪካውያንን ራሷ አፍሪካ ትቁጥረው!! ሚኻኤል ክላሺንኮቭ በለጋ እድሜያቸው የእርሻ መሣሪያ የመሥራት ህልም ነበራቸው፡፡ (ህልሙ ነፍስ ሳይዘራ ቀረ እንጂ!) የማታ ማታም በዝነኛው ክላሺንኮቫቸው በዓለም ላይ እህል ሳይሆን ምስቅልቅል ቀውስ ዘሩበት፡፡ በህይወት ሳሉ የጦር መሣሪያ በመስራት ለህዝቦች ደም መፋሰስ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ሰላም ይነሳቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ የተጠየቁት ሚኻኤል ክላሺንኮቭ “እኔ እንቅልፌን ስለጥጥ ነው የማድረው፡፡ መስማማት አቅቷቸው የጦርነት አማራጭን የሚወስዱት ፖለቲከኞች ናቸው ተጠያቂዎቹ” በማለት ራሳቸውን ነፃ አድርገዋል (ከደሙ ንፁህ ነኝ እንደማለት!)