Friday, June 5, 2015

ሴተኛ አዳሪነት ህጋዊ ልሆን ይገባል


"አምስት መቶ ሴተኛ አዳሪዎች ጩሄታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ አሰሙ......"

"እኛ እንደማንኛዉ ዜጎች ሰርተን እንከፍላለን ስለዝክ ለምን መንግስት ከለላዉ በተለየ መልኩ ይጮቅነናል?"

"በርግጥ እኛ ስጋችን እየሸጥን መተዳደር ባንፈልግም ሰርተን እንዳንበላ ሁነታዎች አልተመቻቹልንም ለዝክ ነዉ እንደመንግስት ጉበኞች ሰርቀን ከምንበላ ሰርተን መብላት አማራጫችን አድርገናል!"

ኻዮሉማ/xayouluma

በባለፈው ወሬዬ እንድህ ብየ ነበር

የአቡጃ አከባቢ ጥበቃ ቢሮ ባለፉት ዘጠና ቀናት ዉስጥ በርከት ያሉ ለከተማችን ዉበት አያስፈልጉም በማለት ለእስር ዳረግናቸዉ ይለናል።
2,534 የጎዳና ተዳዳሪዎች
3000 ሴተኛ አዳሪዎች
102 ህገ ወጥ እንስ ሳት እና
6000 ለሎች ህገ ወጥ ተሽከርካሪዎች

http://nigeriacamera.net/3000-sex-workers-arrested-in-abuja/

ዛሬ ደግሞ ለዛ ለከፋዉ የመንግስት ጭቆና እስር ይጠብቀናል ብለዉ የምያምኑ ናይጀሪያዊያን ሴት የሴተኛ አዳሪዎች ጩሄታቸውን ለመንግስት እያሰሙ መሆኑን ብነግራችሁስ?

ክስተቱ በኛም ሀገር የምስተዋል ብሆንም ለእስር የተዳረጉ አይመስለኝም።ከታዘብኳቸዉ ዉስጥ ሀዋሳ፣ባህር ዳር፣መቛለ እና ለሎች የሀገራችን ከተሞች ሴተኛ አዳሪዉችና ፖሊስ ምሽቱን ጠብቀዉ መሯሯጥ ስራቸዉ እንዳደረጉት ታዝብያለሁ።ታድያ የናይጀሪያዎቹ እንደሀበሻዎቹ ዝም ማለት ስላልቻሉ ሰብዓዊ መንታቸን በመጠቀም ወደ ከተማዉ ሴተኛ አድሪዎች ማህበር ሰልፍ ወጥተዋል።

"እኛ ናይጀሪያዊያን ነን ስለዝክ እንደዘጋ ሰርተን ለመብላት ነው መሻታችን ፤የዕለት ጉርሳችንን ማግኘት ምን ይህል ከባድ እንደሆነ አለም ያዉቀዋል ዳሩ ግን መንግስት በተቃራኒዉ የኛን ነፍስ አድን ጥረት ይወቅሳል ይተቻል ሆኖም ግን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪም ግብር ይለቅምብናል ወንድሞቻችንም ባደባባይ ያወግዙንና መሸት ስል በገንዘባቸዉ ያባብሉናል ስለኛ ስራ ማጣት የማይጨነቀዉ መንግስት ግን ዛሬም አባሮሽ ያጫዉተናል።
ሁላችሁም እንደምታዉቁት አብዛኞቻችን ከዩንቨርሲቲ ተመርቀን ነው ወደዝህ ስራ የተሰማራነው የዝክ ሁሉ ዋነኛ መሰረት ድህነታችን ነዉ፤በተሰቦች አሉን መጦር ይፈልጋሉ ልጆች አሉን እንክብካበን ያሻሉ ማህበራዊ ህይወትም አስገዳጅ እየሆነብን ነዉ።
ስለዝክ መንግስት ያሰራቸውን ሶስት ሺ ሴተኛ አዳሪዎች ከጀርባቸዉ ያለዉን ተጥዋሪ እና እንክብካበ የሚያሻዉም ትዉልድ በማሰብ ነፃ እንድለቃቸዉ መንግስትን እናስጠንቅቃለን አለበለዝያ.................."

ይህ አስገራሚ የህይወት መረብ እንግልት ላይ የጣላቸዉ የናይጀሪያና ያገራችን መሰል እህቶቻችን ከንፈር ከመምጠጥ ባለፈ መንግስት መብታቸዉም እንድያከብር እና በየ ምሽቱ በየጥጋጥጉ ከምያሳድ ድ የተሻለ ኢኮኖሚ አስመዝግቦ ስራ አጥነትንና ድህነትን ማስወገድ አለብን ብየ አምናለሁ እናንተስ?


ኻዮሉማ/xayouluma

http://nigeriacamera.net/abuja-prostitutes-protest-enough-is-enough-prostitution-should-be-legalized/


No comments: