Tuesday, May 12, 2015

ሽ............ብሬ

እንደሁኔታዉ አድርጌ ማርማራታን በዳቦ ጨምቀ በሻይ አወራረድኩና ወደ ስራዬ ሳላረፍድ አዘገምኩ።በስራ ቦታዬ አንድ ራሱን ፕሮፌሰር እያለ የምያስጠራ ዶክቶር V.K ሚሽራ ( በነገራችን ላይ የአርባምንጭ ዉድ ጓደኞቼ በዝህ ዓመት በሞት የተለየችን ዉዷ እህታችን ምሽሪያ የገዳዯ ነገር ከምን ደረሰላት በቃ የደቡብን ፖልቲካ ፊንቲዉ አድርጋ ስለዘከዘከች በመርዝ ገለዋት ዝም ጭጭ አሉ? ታድያ ምን ይደረግ አፋችን ዘግተን በራችን ቆልፌን መቀመጥ ዕጣ ፋንታችን ከሆነ ሰነባብቷል። የታጋያችን ነፍሷን ይማርልን ከማለት በዘለለ ምን እናደርጋለን?) የተሰኘ መምህር በኮልታፋዉ የሻሩክ ቅላጸ ከሰሌዳዉና ከተማሪ መሃል ሆኖ ይለፈልፋል።ይለከችራል። እኔ ግን በድነ ብቻ ታድሞ ጭንቅላተ ማታ ስያየዉ የነበረዉን ዜማ ያመላልሳል።


ላንች ነዉ ላንች ነዉ መሰዋታችን
ላንች ነዉ ላንች ነዉ ትግላችን
ህዝባዊ ሀይል ነዉ ስማችን
ኢትዮጵያ ሀገራችን
አረንጓደ ብጫ ቀዩ ሰንደቃችን
በባርነት ሜዳ ህዝብሽ የማቀቀዉ
በባለጌ ሜዳ ክብርሽ ለጎደፈዉ
ትግል ነዉ መፍትሔዉ
አሁንም ትግል ነዉ
ለቆሜ ነጻነት ለጫኑብን ቀንበር
ለናዱት አንድነት ላረከሱት ክብር
ትግል ነዉ መፍትሔዉ
አሁንም ትግል ነዉ
ለነጻነት ክብርሽ
ለአማኝ ጸአዳሽ
ለወገን ላገሩ በመስዋዕት አገልጋይ
እንደትግል መሪ
ህዝባዊ ሀይል ነዉ አክባሪ
ኢትዮጵያ ላንች ነዉ ላንች ነዉ
ደማችን የምፈሰዉ ለዘላለም ክብርሽ ነዉ
ሰንደቃችን ኢትዮጵያዊ አርማ
ጸንተናል በአንድ ዓላማ
ኢትዮጵያችን በደማችን ይታደሳል ስሟ


ትንሽ የማዳመጥ ችግር እንዳለብኝ ታዉቁታላችሁ። ታስታዉሱ እንደሆነ በሆነ የተስጥዖ ዉድድር ላይ የማዳመጥ ችግር አለብህ ብሎኝ ሰርጸ የጆሮ ማዳመጫ ሰቶኝ ነበር። ባለፈዉ ዓመት ግንቦት ፳ ስናከብር ለዝግጅቱ የተሰናዳዉ ሙዚቃ ከሙዚቃነቱ ባሻገር በጆሮ ማዳመጫ ብቻ ስለማይቻል በምልክት የዘመርነዉ፣ ታድያ በዝያን ሌት ነበር ማዳመጫየን የጣልኩት። ያም ሆነ ይህ የግጥሙን ነገር ለአበል ባርች ( የሙዚቃ ቅንብሮችን ወደ ግጥም ቅንብር የምቀይረዉ ወዳጃችን ) ትቸዋለሁ። ለትምህርት ስርዓቱ ስባል ተሻሽሎ የተወሰደ ግጥም ነዉ። ዉይ ኧረ ይሄ ዓረፍተ ነገር የትምህርት ሚንስተር ነዉ መሰለኝ። ብቻ ግድ የለም አስተዉሉኝ።
ይህ በሌሊት ካንቴቲዩብ ላይ ያየሁት you tube በምለዉ ይታረምልኝ። A song showing TPDM's soldarity with G7 popular force ይላል ስያሜዉ። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን) የባህል ቡድን አባላት ናቸዉ ዜማና ግጥሙን የደረሱት። የቪድዮ ቅንብሩን በትህዴን የህዝብ ግንኙነት ክፍል የተዘጋጀ ነዉ። በቪድዮዉ የምታየዉ የሰራዊት ምስል ከግንቦት ፯ ህዝባዊ ሀይል የሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የተወሰደ ነዉ።
የትህዴን የባህል ቡድን ይህ ዜማ የደረሰዉና የተጫወተዉ ለግንቦት ፯ ህዝባዊ ሀይል ትህዴን ያለዉን ወገንተኛነትና የአንድነት ስሜት ለመግለጽ ነዉ። ግንቦት ፯ ህዝባዊ ሀይል ትህዴን ከተመሰረተ ጀምሮ ከትህዴን አመራርና አባላት በተለገሰዉ ወገናዊ ፍቅርና ድጋፍ፣ በተመለከተዉ የትህዴን ኢትዮጵያዊ ስሜትና ጀግንነት ኮርቷል። የግንቦት ፯ ህዝባዊ ሀይል ከትህዴን ጋር የጀመረዉ ወገናዊነት አንባገነናዊ ከፋፋይ ስርዓት ከሃገራችንም ምድር በመጥረግና በቦታዉ የደሞክራሲ ልዕልና የሰፈነበት የፖለቲካ ስርዓት እንድተካ በማድረግ ከፍተኛ ታሪካዊ አስተዋጽዖ እንደምኖረዉ ያምናል። የግንቦት ፯ ህዝባዊ ሀይል ከትህዴን ጋር የጀመረዉ ወገናዊ አንድነት በእኩልነትና በፍትህ እሴቶች ላይ ተተክሎ የሚካብትና የምጠናከርበት ሁነታ በኢትዮጵያችን እስክመጣ እና ከዛም ባሻገር እንደምዘልቅ እርግጠኛ ነዉ።
ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለኢትዮጵያና ለህዝቧ ስሉ ለዘመናት መስዋዕትነት ለከፈሉ ልጆቿ በሙሉ !!!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነትና ክብር ስሉ የመጨረሻዉን መስዋዕትነት ለመክፈል ለቆረጡ ልጆቿ በሙሉ !!!!
የምል መልዕክት ያዘለ ትዕይንት በምዕናበ እየተመላለሰ የዶክትር ሚሽራን ንግግርና ልክቸራ ወደጎን በመተዉ ስለ ሃገር ልጆች የምወራዉና ስለምባሉት ማገናዘብ ተያያዝኩ።
የዘዉትር ዉሎየ ቀበሌ 0፱ ፌስቡክ መንደር ስለነበር በእኛ ሰፈር ያሉሁነታዎችን አጠነጠንኩ። በፌስቡክ መንደር መጥታችሁ xayouluma Daily Post/xamnxallee time's ብላችሁ ብትጠይቁ ያለሁበትን ማንም ይነግራችኋል። እንደማንኛዉም የፌስቡክ መንደር ልጅ

መረጃ ህይወት ነዉ !!!!

እያልኩ ካብሮ አደጎቼ ጋር ጫት አደርጋለሁ ማለቴ ቻት አደርጋለሁ፣ ኮሜንት እሰጣለሁ፣ ሪኳየስት እቀበላለሁ፣ ታግ አደርጋለሁ፣ ሼርም አከናዉናለሁ በዝህ የማህበራዊ ህይወት RIPን ጽፌ ለቅሶ ደርሳለሁ አለቅሳለሁ አስለቅሳለሁ ሞሾም ደረድራለሁ HBD ብዬ የመልካም ልደት መግለጫዬን እንኳን ተወለዱ በማለት የምጸት ደስታየን ገልጻለሁ fuck ተብየ እሰደባለሁ ደደብ ተብዬም እመከራለሁ null እያልኩ እገስጻለሁ። በቃ የኛ ሰፈር ኑሮ እንደዝኽ ከዘመነ ሰነባብቷል። ከዝኽ ቀደም የምናባክናቸዉ የታክሲ ወጭ የሰልፍ ጊዜ ምናምን የለምን። ይናፍቀናልም። "አይኖርም የምባክን ጊዜ " ብለዉ የዘፈኑት ለዝክ ይሁን በዝክ የማህበራዊ ህይወተ የመግቢያ በራቸዉን የተለያየ ምስል የምያደርጉበት ጓደኞቼና ጠላቶቼን አይቻለሁ።
የመግቢያ በሩን( profile picture) ምንልክ፣ ቴዎድሮስ፣ ሀይሌ ስላሴ፣ዮሀንስ፣ ባልቻ አባ ናፍሶና ሌሎችን የምያደርጉ ዘረኞች፣ ጽንፈኞች፣ ትምክህተኞች እና ያለፈዉን ስርዓት ናፋቂዎች ስባሉ
የመግቢያ በሩን መንግስቱ ሀይሌ ማሪያም፣ ሌኒን፣ ሞሶሎኒ፣ ሂትለርና የቀድመዉ የደርግ ዎታደሮችን( የበተሰብ አባልም ብሆኑ)ምስል ያደረገ አምባገነን፣ ጨካኝ፣ አረመነ ተብሎ ተፈርጇል።
መለስ ዘናዊ፣ ሳሞራ የኑስ፣ አርከበ ዕቁባይ፣ ኃማ ደሳለኝ፣ ቴውድሮስ አድሃኖም፣ የባቡር ግድብ፣ የኤለክትርክ ሃይል ሃዲድ፣ የኮንዶሚኒዬም ቤቶች( ንገሩት ለአሌክስ አብረሃም ሰሞኑን ሰላሳ አምስት ሺ ቤቶች ዕጣ ዎቶላቸዋል ሂድና ስምህን ፈልግ በሉት የምትደርሱት)፣ የሁመራ ሰሊጥ፣ የቦረና ሰንጋ፣ ያዳማ ፈጣን መንገድ፣ኢሌኒ ገብረ መድህን፣ ንብ፣ የማር ቀፎ( ዘመናዊም ባህላዊም ልሆን ይችላል)እና ሌሎች ሜጋ ባለስልጣናትና ሜጋ ፕሮጀክቶችን የምያደርጉ ልማታዊ ጓደኞቼ ናቸዉ( አቤ ከቤን አያካትትም abebe kebede)።
ብርሃኑ ነጋ ( ኧረ መች ነጋልን በሱ ምክንያት ስንቶቻችን ቀኑም ጨለመብን)፣ እስክንድር ነጋ( ሰቶቻችን ኑሮ አንገሽግሿቸዉ ወደ አረብ ስናሳፍር የምንድርበት ጊዜዉ ሄደንኮ ጎበዝ)፣ አንዳርጋቸዉ ጽገ( የቀድሞዉ ፎቶዎቹን እንጂ ሰሞኑን ያዳማ መንገድ ላይ የተነሳዉን ፎቶ አያካትትም)፣ተመስገን ደሳለኝ( ከዛች ሁለ ከማትለየዉ ስካርብና በእጁ የያዛት ከኒዉክለር ማብለያ ንጥረ ነገር የተፈበረከችዉ እስክርቢቶ)፣ ሪዮት አለሙ፣ይልቃል ጌትነት ( ከነ መነጽሩ)፣በየነ ጰጥሮስ( ከፍል ጎፈርያሙ ከፍል ራሱ በራዉ)፣አበበ ገላናዉ፣አቤ ቶክቻዉ፣ታማኝ በየነ፣ ሌንጮ ሌታ፣ ተስፋዬ ገብረ አብ( አባ ገዳ)፣ ልደቱ አያለዉ(የከሰረዉ ፖለቲከኛ ፤እሱ እንኳ ተከታዩ እየቀነሰ ነዉ። ቅርብ ጊዜም ከፌስቡክ ይጠፋሉ ተብሎ ይገመታል)ያሉበትን ፎቶያምያደርጉ ፍጹም ጨለምተኛና ጭፍን ተቃዋሚ ተብለዋል።
በሌላ በኩል ጥላሁን ግዛዉ፣ ሞጎስ አስግዶም፣ አብርሃም ደቦጭ ( አብረሃም ደስታ እንዳትሉ)፣ ቼ ጉቨራ ( "ሰልፍ የረባ ዉጠት የማያስገኝ የቡኩኖች አማራጭ ነዉ!" ያሉ ኢንተርናሽናል አርቢትረር ኧሬ አጨማለቅኩት ኢንተርናሽናር አርበኛ በሉልኝ)፣ ሆ ቺ ሚ ኒ፣ ማርቲን(ማርቲን ብርሃኑን አይደለም አይዞክ ማርትነ ሁለም ወድሃለዉ)እና ሌሎችን የለሰኑ አብዮተኛ ስ ሆኑ
በዓረበኛ የተጻፉትን የለጠፉ አክራሪ ሀይማኖተኛ ተብለዋል።
በተመሳሳዩ የማሪያም፣ የክርስቶስና የመላዕክትንም ምስል የለጠፉ መንፈሳዊያን ናቸዉ።
በቅርቡ በየመን፣ በደቡብ አፍሪቃ፣ በሊቢያና በኢትዮጵያ የደረሰብንን አረመናዊና ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ያዘለ ፎቶ የለጠፉት ከምርጫ በኃላ ጉዳያቸዉ ይጣራል ተብሏል(በሰፈራችን)።
እምስ፣ ቁላ፣ የምባዳ ሰዉ፣ ሴጋ የምመታ ወንድ፣ እምሷን የምታሻና ቅንጥሯን የምትቆነጥር ሴትና ሌሎች ወሲባዊ ፎቶ ያደረገ የወሲን አብዮተኛ ተብሏል( በዉሸት አካዉንት( fake accounts) የወሲብ ፎቶ የምለቁት አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ መሆኑን አንደ የሰፈራችን አብዮተኛ አዉርቶልኝ ነበር። እግዘሩ ይጠብቀኝ ብያለዉ የናንተን አላዉቅም።)።
ይህ ሁሉ የተደረሰበትና የተረጋገጠ የመግቢያ በር ስሆን አንዲት ብዙሃኑ የማያዉቃት ልጅ ፎቶ ሁሉም ህቡዕ( secured account) ትጠቃሚ ምድብ አባላት ይለጥፉታል።
ገምቱልኝ ብላችሁ ግንቦት ፯ 2007 የፍርድ ቀጠሮ የተያዘላት ሃና ላላንጎ ትሉኝ ይሆናል( ሞኞች ዘመኑ'ኮ የነ አጅሬ ነዉ ፍትህ እንደፋስት ፉድ አይደለም ደስ ካለዉ እንደነ መላኩ ፈንቴ አሁንም ይራዘማል)። ሀና የምር ነፍሷን ይማር በገነቱም ያኑራት፣ በምን ምክንያት እንደሆነ ባልዉቅም በዝኽ መዘዘኛ ግንቦት ፯ የፍድር ዉሳነ ለመስጠት ተቀጥሯል የሃና ጉዳይና ገዳይ። ምናልባት ከግንቦት ፯ የሽብር( በኢቢኮ አማርኛ) ና የአርበኞች ግንባር( በኢሳት አማርኛ) የፖለቲካ ሱሴኛ ( በኔ አማርኛ) የሃና ገዳይ ግኑኝነት ይኖረዉ ይሁን ? ምን ይታወቃል አንጋፋዉ ኢቢኮ ይህን ዘና ያሰማን ይሆናል ቀኑ ስደርስ። ካልጠፋ የሃበሻ ቀናት ዉስጥ ግንቦት ፯ ለምን አደረጉት። ግንቦት ፯ ይሁን ያስደፈራት? ለምንስ ለግንቦት ፳ አልቀጠሯትም(መዝገቡን ነዉ )?
ብቻ እሷ አይደለችም። ዉይ ግምት የማትችሉት ይሄነ ሰማሃልን ብላች ሁ እንዳይሆን። ማፈሪያ ሁላ የሰማሃል ፎቶ የመግቢያ ፎቶ ይሆናል?
እሷ ግን..............
በ1997 ድህረ ምርጫ ተቃዉሞ ሰልፍ ላይ የመጀመርያዉ ሰልፍ ላይ የመጀመሪያዉ የፌደራል ጥይት በአንገቷ ስር ጥይት የሰነቀረላት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የለዉጥ ሃዋሪያ ሽብሬ ደሳለኝ ነች።
ዛሬ በህይወት ብትኖር ወልዳ ስማ፣ ለወግ ማዕረግ የምትበቃ ነበረች።ግና አላረጉትም ጨክነዉ ገደሏት።መንግስት ካንቀላፋበት ልማታዊ ጉዞ እንድነቃ የመጅመርያዋን ደወል ያሰማች ከጀግናም በላይ ጀግና የሆነች የሀያ አንድ ዓመት ታጋይ ነች። የግንቦት ፯ የ97 ምርጫ ዉጥቱን ተቃዉማ ግንቦት 28 1997 በተደረገ የተቃዉሞ ሰልፍ ላይ በቆራጥነትና በጀግንነት መስዋዕት ለመክፈል በመወሰን ወደ ኋላ ሳትሸሽና ሳታፈገፍግ እንደጀግናዉ አፄ ዮሓንስ አንገቷ ለህዝብ ጥቅም አሳልፋ የሰጠች የሃበሻ ጀግና ነች።የዘመኑ ወጣት ዓላማ ቢስ ፣ ወነ ቢስ ነዉ ላሉን ፖልቲከኞች ምላሽ የሆነች።
የሽብሬ መሰዋት እኛን ለተሻለ ለዉጥ ስያነቃቃ መንግስት የልማት አቅጣጫዉን እንድገመግም አስችሏል። መንግስትን ካንቀላፋበት የቀሰቀሰች በዘር በጎሳ ሳትወሰን የሃገሪቱን ህዳሴ በመናፈቅ መስዋት የሆነች የጀግና ጀግና ነት። ሽ....... ..ብሬ።
የዝች ታላቅ ጀግና አንገት ከጠብ መንጃ ባሩድ ከተጋጠመ ስጋዋም ካፈር ከተዋሄደ ይሄዉ አስር ዓመት ሞላት አሁም በሽብሬ ራዕይና ዓላማ መዘወር የምጓዙ አንገታቸዉን ለኢትዮጵያ ክብር ሊሰዉ የተዘጋጁ ሽዎች አሉ።
ላንች ነዉ ላንች ነዉ መሰዋታችን
ላንች ነዉ ላንች ነዉ ትግላችን
ህዝባዊ ሀይል ነዉ ስማችን
ኢትዮጵያ ሀገራችን
አረንጓደ ብጫ ቀዩ ሰንደቃችን
.
.
.
.
.
.
ኢትዮጵያ ላንች ነዉ ላንች ነዉ
ደማችን የምፈሰዉ ለዘላለም ክብርሽ ነዉ
ሰንደቃችን ኢትዮጵያዊ አርማ
ጸንተናል በአንድ ዓላማ
ኢትዮጵያችን በደማችን ይታደሳል ስሟ
እንኳን ለጀግናችን ሰማዕት ሽብሬ ደሳለኝ አስረኛ የሙት ዓመት መታሰብያ ወር በሰላም አደረሳችhu !!!
በሉ ዶክtር ሚሽራ መጣ ቻዉ ቻዉ። ድል ለሰማዕታችን !!!!

No comments: