Wednesday, May 13, 2015

ሰምሃልን ልጥበስ ?

   

    በዝህ ዘመን የምስተዋለዉ አንድም የሃበሻ ሴትና ወንድ ስራ አጣን ስሉ እና ጊዜያችን ና እድመያችን እየነጎደብን ነዉ የምሉ ብዙዎች ናቸው።ዳሩ ግን ሁሉም ማለት በማይቻል መልኩ ወጣቱ፣ አዛዉንቱ፣ መበሊቱና ባልቴቱ ስራ በስራ ሆነዉ ተጠምደዋል።ግምቶች እንደምጥቁም ከሆነ ከሃገራችን ጠበሳ ያዋጣቸዉ ሴቶችን ነዉ ይላሉ። መቸም ስለመጥበስና መጠበስ ሳወራ ክረምቱ እየገባ ስለሆነ አንድ ሁለት የጠበሳ ማስታወቂያዎችን ላስነብባችዉ።

    ንብረት የምድጃ በቆሎ ጠባሽ፣
    እንደደወሉልን እየጠበስን ደራሽ፣
    ብርድ ያኮማተረሽ እያንዳንድሽ፣
    አራት ብር ይጨነቅ ንብረት የበቆሎ ምድጃ አለልሽ።

    ሁለተኛዉን በኋላ እመለስበታሁ። ሴቱና ወንዱ ለመገናኘት ቦታና ታክሲ ስላላመቸ በተለያዩ ማህበራዊ ድሬ ገጾች ጥቅስ እየተገባበዙ መጠባበስ ከጀመሩ ይሄዉ አስራ አንድ ዓመት ሞላን። በርግጥ እንደቀደመዉ የጠበሳ ስነ ስርዓቱ በሆተል ግብዣና በካፌ ቡና ባይጠናከርም በምያማልሉና ቀልብ በምስቡ የአዶቤ ፎቶ ማጠቢያ አጋርነት የትዉልዱ ፍቅር ከመቸዉም ጊዜ በላይ ተጠናክሯል። የኤፍ ቢዉ፣ ቲዊተሩ፣ ጎጉል ፕላሱ፣ ስካይፒዉ፣ ታንጎዉ፣ ዋሳፑ፣ ቫይበሩ፣ ማይኮዉ፣ እናሌሎች ሳይቆጠሩ ሃበሻ ምስት ለመሆን  እና ባል ለመባል የማይከፍቱት አካዉንት የለም የማይዘጉት ፍሬንድ (የተመሳሳይ ጾታ )የለም።ያም ሆነ ይህ ግን በwww.ethiospot.com፣በwww.ethiopianspersonal.com፣በwww.eskimi.com፣በwww.waplog.com እና ሰሞኑን በተለቀቀዉ www.kingslove.com  የማይገናኝ የለም።


    በፊት በፊት በሰፈር ድንጊያ ላይ ተቀምጦ( ጋሽ ፖሊሱ ክበበዉ ገዳ ጮሆ ይሀዉ አስበተናቸዉ)አላፊ አግዳሚዉን እየቆጠረ ሴትን ሴትን ከምጠባበቀዉ ታማኙና ግልጹ ወንድ በተጨማሪ ያሁኑ ባለትዳር በየማህበራዊ ደሬ ገጹ ዉሎ አዳሩን አድርጓል። ዉሃ ስትቀዳ፣ ገበያ ስትላክ፣ በቤቲያን ስታመልክ(መስጅድም)፣ ጸጉር ስትሰራ፣ ጥምቀት ስታከብር እየተግደረደረች እየተቁለጨለጨች ወንድ የምታይ ሴት ሁላ ዘንድሮ ያን የጃን ሆይ ጋሻ መሬት ያህል የምሰፋ ስልክ ገዝታ፣አስገዝታ፣ ቀፍላ፣ ቀፋፍላ፣ ለምና አለቃቅሳ ብቻ በየትኛዉም መንገድ ትይዝና ፎቶዎቿን ከተገላለጠ ጉንጯ፣ ከበሰበሱ ከናፍርቷ፣ ጸሀይ ላይ ከምዉለዉ ጡቷ፣ እንደድፎ ዳቦ ከተከመረዉ መቀመጫዋ ጋር በቅንብር እያዋዛች መበተንና መበታተን ከዝያም ባለፈ ወንድን ሁሉ ወደ እኔ ና በምል የገበያ ሽምያ መጥራት ከተጀመረ ይሄዉ አስራ አንድ አመት ሞላን። ወንዱም በጥቅሻ ፋንታ ላይክ፣ በማሽኮርመም ፋንታ ኮሜንት እየተባባለ መጠባበስ ከተጀመረ ይሀዉ አስራ አንድ አመት ካንድ ደቂቃ ሆነን።

    ኧረ ምኑ ቅጡ ኤፍ ኤም በሙሉ ማጣበስ ብርቅ ሆኖባቸዉ ይሄዉ ይራወጣሉ። ዛሚ ነሽ ሼገር፣ ብስራት ነሽ አባይ፣ አዲስ ነሽ ሀዋሳ በቃ ባጠቃላይ ኤፍ ኤሙ በማጣበስ ስራ ላይ ተጠምደዋል። ታድያ ይህን ያየ ወዳጀ

    "ሰማሃልን ላጣብስህ?"

    ስለኝ ወድያዉ ደነገጥኩኝ።

    ማስታወቂያ ፪

    ችክ ደዋዉሎ መጀንጀን ያቃተሽ፣
    ጠበሳ መለማመጃ የወላይታ እሸት አለልሽ፣
    በኛ ምድጃ ስያሰኝሽ ጠብሰሽ፣
    ካላማረሽ አስጠብሰሽ፣
    ለክረምት ማቆያ ትኩስ ትበያለሽ።

    "ስማ xayouluma /ኻዮሉማ  "አለኝ

    ምንም ሳልመልስለት አይን አይኑን ሳየዉ
    "ለምን ሰማሃልን አላጣብስህም?"

    "ምን?"

    'ሰምተሃል"


    ብሎኝ አረፈዉ ጓደኛዬ ጎይቶም።

    ይሄነ ነዉ መሸሽ። በጭንቅላተ የመሮጫ ትራክ ሽሽት ጀመርኩ። እንዴ ልጁ እያበደ ነው? ምንም ያህል ነጻነት ብሰጠን ሰማሃልን ጀንጅን ይበለኝ?  ሃገሪቱን ደሞክራሲያዊ ሰላማዊ ባደረጉት ጀግኖች ልጅ መድፈር ታሪክን መዳፈር አይሆንም?  ምድር ላይ ሁለታችን ፌስ ቱፌስ ብንቀር ከሰማሃል ጋር ልጋባ ? ኧር አፉ በል!!

   " የምረን ነዉ እዝሁ አብረን ነው የምንማረዉ፣ በዛ ላይ አንተን ትቀርባሀለች፣ አንተም እስካሁን ባፍህ አልጠየቃትም እንጅ እሷን ከከጀልክ መቆየት ህን አይነ ዉሃህ ይናገራል።"
    
    ኧረ ዝም በል በሉልኝ ይህን ክፍት አፍ

    ወይነ xayouluma/ኻዮሉማ የነ መጨረሻ ይሄ ይሁን።

    አይጥ ስትቀብጥ ስታበዛ ሩጫ ሄዳ ታሸታለች የሰምሃልን አፍንጫ  ይሉት ይሄ ነዉ። በፍጹም የማልደፍረዉ ነገር ብኖር ይሄና ይሄ ብቻ ነው።

   " ምን ያስፈራሃል? እሷ አሁን እንደበፊቱ ራሷን አታካብድም።በዝያ ላይ እናቷም ብት ሆን የሀገሯን ልጅ እንድታገባ ነዉ የምትፈልገዉ....."

    ደፋር እናቷን ብሎ ያለማዕረግ ስሟን አልጠራም። አስቡት እስት ከሰማሃል ጀርባ ስንት የተደበቀ ምስጥር፣ ክብር፣ ብር፣ ቀብር፣ ፉኩክር  ይኖራል?  አልያም።ምስጥር ብቻዉን የፖለቲካ ምስጥር፣ የቤተሰብ ምስጥር፣ የወንጀል ምስጥር እያለ ራሱን ችሎ ይከፋፈላል። ቀብርም እንደዝያዉ የሀገር ሃበሻ አጥንት ከሷ ጀርባ። ፉክክሩስ ብሆን ገና ለገና የነ ስዩም መስፍን፣ ቴወድሮስ አድሃኖም፣ በረከት ስሞን፣ አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አርከበ ዕቁባይ ልጆች ጋር ልፎካከር ነዉ ? በጣም ከባድ ገጠመኝ አትሉኝም ? ሌላዉ ቢቀር ፉክክሩ በሩጫ ብሆን እነሱ በገንዘብና በዲፕሎማ የሃይሌንና የቀነንሳን ሳንባ እየደራረቡ ገዝተዉ ይሮጣሉ ምንነዉ ሸዋ!!!

    ብሩን ብቻ አስበ የት ልደርስ?

    የሰማሃል ብር የነ ልሆን?

    የምገርም ነዉ ሃብቱ የነ ስሆን ማየት ማትፈልገዉ እናቷ በስራ ላይ ያለዉን የማይሻሻለዉን የቤተሰብ ህግ አስቀይራም ቢሆን

   " ሴቶች ከዝ ህ ቀደም ባለፈዉ ስርዓት ተጎጅ ስለነበሩ ባሁኑ ስርዓት ያፈሩት ሃብት ምንም ከትዳራቸዉ ጋር አይገናኝም ብትል ስንት የሃገረ ወንድ የምስቱን ሃብት ተማምኖ የኖረዉ ዛሬ በኔ ምክንያት በጸደቀዉ አዋጅ ከሀገር ይሰደድ

    እኔና ጎይቶም ቁርስ ልንበላ ስለነበር የካፌ ወንበር ላይ ቁርሳችንን ስንጠብቅ ጎይቶም ባቀረበዉ ልማታዊ ሃሳብ( ባጭሩ የመክበር ክራይ አሰባሳቢነት)ኩራት እየተሰማዉ በዓይኖቹ ግራ ቀኝ ስያማትር እኔ በምዕናበ የተለ ቀጠሮ ያዝኩኝ።

    ሰኞ ማለዳ ነበር ባዲስ መንፈስ ባዲስ ሃሳብ አብረን ወደምንማርበት የመንግስት ት/ቤት አቀናሁ። ተማሪዉ በሞላ ያችን ቀንጥኛ ቦርሳ፣ ነጭ የካፌ ሰርቭስ የመሳሰሉ ታብለቶች እና ዉድ ዉድ የምባሉ ሽቶዎችን ግቢያችን አሳመሩልን። ዘዉትር ከምቀመጥበት ቦታ ሳለሁ ሰምሃል ያን ያባቷን መልክ ይዛ ጸጉሯን ተተኩሳ በቀንጠኛ አረማመድና በሚያማልል አለባበስ ተዉባ ወደ እኔ ቀረበች።

    "ሀይ"

   " ሀይ"

   " እንደት አደርሽ ቤብ"

    "ሰላም አደርክ ማይ ዳርሊንግ "   አለችኝ

    "ትናንት ስልክ ስደዉልልሽ ለምድን ነዉ ያላነሳሽ  ደህንነት ሽ አሳስቦኝ ብደዉል ትንቀባረሪያለሽ  "  እየተኮሳተርኩ ጠየኳት

    "O MY GOSH !!ያስቀመጥክልኝን  ሰምቸዋለሁ በዝያን ሰዓት አንድ የቀድሞ ያባቴ ወዳጅ ከካልፎሪንያ መጥቶ ብዙ ስጨቀጭቀኝ ነበር። sorry እሽ የኔ ዉድ"

    አለችኝና ጉንጨ ላይ ሳመችኝ።

እዝያዉ በቆምንበት በክርክራችን መሃል ሳያት ደወለችልኝና ልታገኘኝ እንደምትፈልግ ነገረችኝ። ሰማሃል ማን እንደደወለች ስትጠይቀኝ ለምን እንደደወለችልኝ ጭምር ነገርኳት። ፊቷ ወድያዉኑ ተቀያየረ። አነር መሰለች። ምንም ማድረግ ስላልቻልኩ ለሳያት ቅድሚያ ሰጠዋት። ቅድሚያ የሰጠዋት ምክንያት ሳያት አሳምራ በሶስት ድጅት ዉበት ሰማሃልን ትበልጣታለች።አለቀ።ግን አልደቀቀም።

"አንዴ ስማኝ የኔ ማር " 
 ለመሄድ ጀርባዬን ሳዞር አቆመችኝ

"ለምንድን ነዉ የምትርቀኝ? ለምንድን ነው የምትሸሸኝ ? እኔስ ሴት አይደለሁም ? ለምንድን ነው ፍቅረ የማይገባህ ?"
  እንባ እያቀረራት ልታነባ እየቃጣት...

"ማን ነዉ የሸሸሽ ? ማን ነው የጠላሽ ? እንዴ? ምን ነካሽ ሰማሃል? አንችኮ የመለ......"

በመሃል አቋረጠችኝና

"please ያን የፖለቲካ ፍቅር እርሳዉና የልበን ተረዳኝ እወድሃለሁ , አፈቅርሃለሁ ,ያንተ ብቻ መሆን እፈልጋለሁ የራሰም ላደርግህ እመኛለሁ "

የማያቋርጥ ማላዘን። ምንም ማድረግ አይቻልም አለ ዲጄ ክንግስተን። ኧረ በፈጣሪ በሳያት ዉበትና በሰማሃል ገንዘብ መሃል ለመሃል ተገተርኩ። ገንዘብን ሰርቸዉ አገኘዋለሁ። እዝህ ሀገር ከሆነ ስራ ሞልቷል ትንሽ ብጥር ብዙ አተርፋለሁ እያልኩ ወደ ሳያት ሳመራ ልቤ 'የሳያት መልክ ታጥቦ አይጠጣም' 'ዉበት ረጋፊ ነዉ' በርግጥ ሳያት ምንም ቆንጆ ሆና ብታምርም የማልወድላት ነገር አለ ያ በየ አርቲስቱ ቤት እየሄደች ከአርቲስቱ ጋር ማማገጥ አይሉት ማላገጥ ያስጠላኛል። ከዝ ህ በፊትም ነግርያት አልተለወጠችም።በርግጥ ትንሽ ተሰጥዖዋ ወደ አርቱ ያደላል ለዝያም ይሆናለ ብየ ራሰን ልያሳምን ስያስብ

"አንተን'ኮ ነዉ የምያዋራህ"  ስትለኝ ወደሷ ዘወር ስል

ሰማሃል ከትግል በተመለሰ ሽጉጥ ስትመዝብኝ

ከጥልቁ ምዕናበ ስመለስ የካፌዉ ቁርስ ደርሶልን ስለነበር መብላት ጀማመርኩ
ጎይቶም አሁን ቀጠለ

ሰማሃልኮ ላንተ ትሆናለች ጥሩ ሙድ አላት ደግሞም አንተም እንደሷ አይነት ሴት እንደምትፈልግ አልጠራጠርም

ድንቄም ባለሙድ። ይቅርብኝ የሷ ገንዘብ በቴሌ ካርድ ይዉጣ። አልፈልጋትም ልበለዉ ? አልለዉም። ግን ትንሽ ላስብበት። እናንተንም ላማክርበት። እስት የምትወዱኝ በሙሉ xayouluma/ኻዮሉማ ይሄ ይሻልሃል ያ ይበጅሃል በሉኝ።

ምን ትሉኛላችሁ ?ጎይቶም

" ሰማሃልን ላጣብስህ ?"

 እያለኝ ነው


Choose a sticker or emoticon

No comments: