ማርክ ዙከርበርግ በማን አለብኝነት የሁላችሁንም የፌስቡክ ገጽ በፈረንሳይ ባንዲራ አቅልሙልኝ ስል በጠየቀዉ መሰረት አብዛኛዉ ያበረከተልን ዉለታ በማሰብ ነዉ መሰል ትዕዛዙን ተቀብለዉታል እኔና መሰሎቸ ግን አሁንም ከመከራከርና አይመለከተኝም በማለት አምጸንበታል ምናልባት በጉልበት ካልዘጋብን በስተቀር ምንም አያመጣብንም ብየ አስባለሁ። የሆነዉ ሆኖ ዙከርበርግ ለፓሪስ የተለየ ፍቅር እንዳለዉ አሳይቶናል።የከዝ ህ ቀደሙ ስቀር ፓሪስ በፈነዳች ማግስት በሩት እነም ዜጎቸን አጥታለሁ ስለዝክ ለነም የሴፍቲ መከታተያ ያስፈልገኛል ስትል በዉድ የፌስቡክ ተጠቃሚዎቿ አማካይነት ጠይቀዋለች፣ የኛ ልጆችም እንደታ ህዝባችን በረሃብ እያለቀብን ስለሆነ ዙከርበርግ ለምን የሃበሻ ረሃብተኞችን አይጠይቀንም ስሉ ተሟግተዋል። ዘዉትር ብዙ ልብ ያዘለዉ ሃበሻም ስማችን ዳግም በረሃብ አይነሳ ስል ስምዋገት ዉሎ አምስትዋል፤ በርግጥ ገጽታ ግንባታ ለላ ነገር ብሆንም ሰባዊ የርዳታ ጥሪ መቅደም አለበት ይላል የዝህ ጽሁፍ አሰናኝ። የከኒያ ጋሪሳ ተማሪዎች፣ የሶርያ ከ 150ሺ በላይ ሰላማዊና ንጹሃን ዜጎች፣ ኔፓል ከ 50ሺ በላይ ዜጎቿን በተፈጥሮ አደጋ, ራሺያ ከ 200 በላይ ዜጎቿ ሲናይ በረሀ ላይ ሰሞኑን ሲያቁ, የማላዚያ ምስኪን መንገደኞች እና ሌሎች የ አፍሪካና የአረብ ሟቾች ከማርክ ዙከርበርግ አይን ያልገቡበት ምክኛት ይኖር ይሁን ወይ ስል አሰናኙ ኳዮሉማ ሃሳቡን ይሰነዝርላችኃል።- ኢትዮ-ቴሌኮም በኖኪያ ቁጥጥር ስር የነበሩ የኔትዎርክ ወረዳዎችን ነፃ አወጣ!
- አንድነት እና መኢአድ ሳይጋቡ በመፋታት ሪከርድ ሰብረዋል
- “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ትዝ የሚላቸው ምርጫ ሲቃረብ ነው
የአፍሪካ አንድነት የሰላም አስከባሪ ኃይልን የተቀላቀለው የአገራችን መከላከያ ኃይል ሶማሊያ ውስጥ አልሻባብ ተቆጣጥሯቸው የነበሩትን ቦታዎች ማስለቀቁን በኢቴቪ ዜና እወጃ ላይ ሰምቼ ደስ ብሎኝ ነበር (ኢትዮጵያዊ ሆኖ ድል የማይወድ አለ እንዴ?) በነጋታው ነው መሰለኝ … ሌላ የምስራች ደግሞ ሰማሁ፡፡ ኢትዮ-ቴሌኮም በኖኪያ ቁጥጥር ስር የነበሩትን አየር ጤና፣ ቄራና ዓለም ባንክ አካባቢዎች ነፃ ማውጣቱ ተነገረ-በዜና ሳይሆን በተባባሪ ወሬ፡፡ እናላችሁ …. ሁለቱ አካባቢዎች አሁን ኔትዎርካቸው ያለመቆራረጥ እየሰራ ነው፤ ተብሏል (ኢንተርኔትና ፌስቡክም ያለችግር ማግኘት ችለዋል) ኢትዮ-ቴሌኮምን የማሳስበው ግን በዚህ የድል ብስራት ተኩራርቶ ሌሎቹን በቁጥጥር ስር ያልዋሉ የኔትዎርክ ወረዳዎች ነፃ ከማውጣት እንዳይዘናጋ ነው። ያለዚያ እኮ የሦስቱ አካባቢዎች ነፃ መውጣት ትርጉም የለውም (ተመልሰው በ“ጠላት እጅ” ሊወድቁም ይችላሉ!) እናላችሁ … ሌሎች የመዲናዋ አካባቢዎችም ከ “ባዕድ እጅ” ነፃ ሲወጡ ነው እነ ዓለም ባንክ ነፃነታቸውን በቅጡ የሚያጣጥሙት፡፡ እስከዛ እኮ እርስ በርስ ብቻ ነው ኮሙኒኬሽኑ!









