በስትሮክ የመሞት አደጋን ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል
ለስኳር ህመምና ለደም ማነስ ሙዝን መመገብ ይመከራል
ለስኳር ህመምና ለደም ማነስ ሙዝን መመገብ ይመከራል
በኢትዮጵያ እንደተገኘ የሚነገርለትና በዓለማችን በስፋት
እየተመረተ ለምግብነት የሚውለው ሙዝ እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ሙዝ ከምግብ ይዘቱ በተጨማሪ ለተለያዩ
በሽታዎች ፈውስ ሊያስገኙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም አካቶ ይዟል። እነዚህ ንጥረነገሮች ለበርካታ በሽታዎች ፈውስ
ከመሆናቸውም በላይ፣ በሽታው ከመከሰቱም በፊት ለመከላከል የሚያስችለንን አቅም ያጐናጽፉናል፡፡ በጥቁር አንበሳ
ሆስፒታል በጠቅላላ ህክምና ክፍል ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ታዬ አለማየሁ እንደሚናገሩት፤ ሙዝ በስትሮክ ምክንያት ሊከሰት
የሚችለውን ሞት በግማሽ መቀነስ ይችላል፡፡
ሙዝ በውስጡ የካርቦሃይድሬት ንጥረነገሮችን የያዘ በመሆኑ ከፍተኛ ሃይል እንድናገኝ ይረዳናል። ሁለት ሙዝ በልተን በምናገኘው ሃይል ለዘጠና ደቂቃ አድካሚ የጉልበት ሥራዎችን መሥራት እንደምንችል ዶ/ር ታዬ ይናገራሉ፡፡
ብዙዎቻችን ሙዝን ለምግብነት በማዋል ለሰውነታችን ሃይልና ሙቀት ለማግኘት እንደምንችል ከማወቅ የዘለለ ነገር አስበን አናውቅም፡፡ ነገር ግን ሙዝ በውስጡ የያዛቸው ተፈጥሮአዊ የስኳር ወይም የጣፋጭ ምንጭ የሆኑት ግሉኮስ፣ ስክሮስ፣ እና ፍሩክቶስ የተባሉት ንጥረነገራት ከሙዝ የፋይበር (የቃጫነት) ተፈጥሮ ጋር ተዳምረው መጠነሰፊ ጠቀሜታዎችን ይሰጣሉ። ከበርካታ የሙዝ ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን ከዚህ እንደሚከተለው ለማየት እንሞክራለን፡፡
1. ለአእምሮ እድገት
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ የፖታሺየም ንጥረነገርን ይዟል፡፡ ይህም ንጥረ ነገር የአንጐልን የሥራ ብቃት ለማሻሻል እና ለማሳደግ እንዲሁም ንቁና ጤናማ አዕምሮ እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
2. ለስትሮክ
በሙዝ ውስጥ ያለው ፖታሺየም፣ የደም ሥርዓትን በማስተካከል ባልታሰበ ሁኔታና በድንገት የሚከሰተውን የስትሮክ ችግር ለመከላከል ያግዛል። ሙዝ በሰው ልጆች የአመጋገብ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ ዘወትር ለምግብነት የሚውል ከሆነ፣ በስትሮክ ምክንያት የሚመጣውን ድንገተኛ ሞትና የአካል ጉዳት ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡
3. ለደም ግፊት
ሙዝ በተፈጥሮው በውስጡ የሚይዘው ዝቅተኛ የጨው መጠን በመሆኑ የደም ግፊትን ለማረጋጋት ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውስጡ ያለው ፖታሺየም የደም ግፊትን ለማስተካከልና በግፊት ሳቢያ የሚከሰቱ ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
4. ለጨጓራ ህመም
አብዛኛዎቻችን ሙዝ ከበድ ያለ ምግብ እንደሆነ በማሰብ፣ ሙዝ የጨጓራ ህመማችንን እንደሚያባብስብን ስንናገር እንደመጣለን፡፡ ይሁን እንጂ ሙዝ ለጨጓራ ችግሮች ሁነኛ መፍትሔ ነው። ሙዝ በባህርይው በጣም ለስላሳ በመሆኑ በጨጓራ ላይ መጨናነቅን የማይፈጥር ሲሆን የጨጓራ አካባቢን በመሸፈን፣ የጨጓራ ውስጥ አሲድን በማስተካከልና በማመጣጠን የጨጓራ ቁስለት እንዳይፈጠር ለማድረግ ያስችላል፡፡
5. ለድብርት
ሙዝ በውስጡ የሚይዘውና ትራይፕቶፋን የተባለው ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ሴሮቶኒን የባለ ሆርሞን እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
ይህ ሆርሞን አይነተኛ ተግባሩ ሰውነታችንን ከድካምና ከድብርት በማላቀቅ ወደተሻለ ስሜት ውስጥ እንድንገባ ማድረግ ነው፡፡
6. ለሆድ ድርቀት
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው ፋይበር ለምግብ መፍጨት ሥርዓታችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡ የምግብ መፍጨት ሥርዓትን የሚያከናውኑት የሰውነታችን ክፍሎች በቂ የውሃ መጠን እንዲኖራቸው በማድረግ ሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ አንጀት የተለሳለሰ እንዲሆን በማድረግ ከሰውነታችን መውጣት የሚገባቸው አላስፈላጊ ነገሮች (ቆሻሻዎች) እንዲወገዱ ለማድረግ ይረዳል፡፡
7. ለስኳር ህመም
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ ቫይታሚን B6 የያዘ ነው። ይህም በደም ውስጥ የሚኖረውን ከፍተኛ የስኳር መጠን እንዲቀንስ በማድረግ፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ያስችለናል፡፡ ከስኳር መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የጠዋት ህመምንም ያስቀራል፡፡
8. ሙዝና ደም ማነስ
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው የብረት ማዕድን ጠቀሜታው በደማችን ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የሔሞግሎቢን ምርት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ይህም በሔሞግሎቢን እጥረት ሳቢያ የሚከሰተውን የደም ማነስ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡
9. ሙዝ ለስካር
ሙዝ ከወተትና ከማር ጋር ተደባልቆ ለምግብነት ሲውል በከፍተኛ መጠጥ ወይም በስካር ሳቢያ የሚከሰትን ሃንግኦቨር (ያደረ ድምር) በቀላሉ ያስወግዳል፡፡ በመጠጥ ሳቢያ የተጐዳን ሰውነት እንዲነቃቃና ብርታት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድም ሙዝ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡ የሲጋራ እና መሰል ሱሶች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሱሱን ለማቆም እንዲችሉ ሙዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
10. ለሞቃታማ አየር
በሞቃታማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሙዝን ቢመገቡ ሰውነታቸው ሙቀቱን እንዲቋቋም በማድረግ፣ የተረጋጋና የተስተካከለ የሰውነት ሙቀት እንዲኖረን ያደርገናል፡፡
11. የሙዝ ተጨማሪ ጠቀሜታዎች
በወባ ትንኝ የተነደፈ ሰው ወይንም በማንኛውም ተናካሽ ወይም ተናዳፊ ነፍሳት የተነደፈ (የተነከሰ) ሰው በሙዝ ልጣጭ የውስጠኛው ክፍል የተነደፈበትን (የተነከሰበትን) ቦታ በደንብ በማሸት እብጠቱን መቀነስ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ንድፍያው (ንክሻው) የፈጠረበትን የማቃጠልና የመለብለብ ስሜት ለማስወገድ ይችላል፡፡ ጫማዎን ከጠረጉና ቆሻሻውን ካስወገዱ በኋላ በሙዝ ልጣጭ ቢወለውሉት ጫማዎ እንደመስታወት ያበራልዎታል።
ፍሪጅዎ መጥፎ ጠረን (ሽታ) ካመጣብዎ አንድ ሁለት ሙዞችን ያስቀምጡበት፡፡ የፍሪጅዎ ጠረን በቅጽበት ይቀየራል፡፡
ሰውነትዎ በድካም ወይም በህመም ከተጐዳና የምግብ ፍላጐት ከሌለዎ አንድ ሙዝ እንደምንም ይመገቡ፡፡ ሰውነትዎ ሲበረታና የምግብ ፍላጐትዎ ሲጨምር ይታወቅዎታል፡፡
በአጠቃላይ ሁላችንም እንደቀላል የምናየውና ብዙም ትኩረት የማንሰጠው ሙዝ ለከፍተኛ የጤና ችግር የሚዳርጉንን በሽታዎች ለመከላከልና ለማስወገድ ይረዳናል፡፡
ታዲያ ይህን የግል ሐኪምዎ የሆነ ፈዋሽ ፍሬ በፍሪጅ ውስጥ ከተው አያበላሹት፡፡ ንፋስ ያለበት ያልታመቀ አየር ለሙዝ የሚስማማ ነውና - በዚያ ያኑሩት፡፡

No comments:
Post a Comment