Saturday, September 28, 2013

ከአስር ሺ ካድሬዎች አንድ ጀግና አትሌት ይሻለኛል!

የፌዴሬሽን ነገር አልተሳካልንም!
ሩጫ እንደ አፍ አይቀናም (ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽን!)
.የዛሬውን ፖለቲካዊ ወጌን የምጀምረው በአትሌቲክስ ነው፡፡ አትሌቲክስና ፖለቲካ ምን አገናኛቸው እንዳትሉኝ ብቻ! (ቀላል ይገናኛሉ!) ወዳጆቼ … አትሌቲክስ ስፖርትነቱ ለጀግኖች አትሌቶቻችን ነው እንጂ ወደ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሲገባ መልኩን ይቀይራል፡፡ (የቀለጠ ፖለቲካ ይሆናል!) ይሄ እኮ ሃሜት አይደለም፡፡ በመረጃም በማስረጃም የተደገፈ ሃቅ ነው (ፍ/ቤት የመሄድ ፍላጐት ግን የለኝም!) ለነገሩ ፍ/ቤትም ለካ እረፍት ላይ ነው፡፡ እናንተዬ … ፍ/ቤት በክረምት የሚዘጋው (የሚያርፈው) ድሮ ወንዝ እየሞላ መሻገሪያ ስለሚጠፋ ነው የሚባለው እውነት ነው እንዴ? አሁን ታዲያ የትኛው ወንዝ አስቸግሮን ይሆን? (የልማድ እስረኞች እኮ ነን!) 
ይሄውላችሁ … ስለ ፌዴሬሽኑ ፖለቲካ ከማውጋታችን በፊት ትንሽ “ሰለብሬት” ማድረግ አለብን - ስለ አትሌቶቻችን ድል!! እናንተ … የጦቢያ አትሌቶች እንዴት አንጀት አርስ ናቸው ባካችሁ! (ኧረ ሺ ጊዜ ይመቻቸው!) ለዓለማችን ኮከብ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ (እውነትም ነገር የገባት ሰጐን!) እጅ ነስቻለሁ! ለ800 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ባለድሉ ለመሃመድ አማንም እጅ ነስቼአለሁ - በአዲስ ርቀት ላስመዘገበው ድንቅ ውጤት! ነሐስን ጨምሮ ሌሎች ድሎችን (ከ4-10 ለወጡትም) ላገኙም እጅ ነስቼአለሁ፡፡ ለደረጃ ባይበቁም ጦቢያን አደባባይ ወክለው ለሮጡልን ምርጥ የአገሬ ልጆችም እጅ ነስቼአለሁ፡፡ በሴቶች ማራቶን በገጠማቸው አንዳንድ እክሎች ውድድሩን አቋርጠው ለወጡት የጦቢያ ጀግና አትሌቶችም እጅ ነስቼአለሁ (ፌዴሬሽኑ ደብዳቤ ፃፉ ቢልም) አንዳንዴ ምን እንደማስብ ታውቃላችሁ? ኢትዮጵያን የሚመሯት ምነው አትሌቶች በሆኑ እላለሁ (የድል አርማ ናቸዋ!)

ሙዝ!

የግል ሐኪምዎ የሆነው ሙዝ!
በስትሮክ የመሞት አደጋን ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል
ለስኳር ህመምና ለደም ማነስ ሙዝን መመገብ ይመከራል
በኢትዮጵያ እንደተገኘ የሚነገርለትና በዓለማችን በስፋት እየተመረተ ለምግብነት የሚውለው ሙዝ እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ሙዝ ከምግብ ይዘቱ በተጨማሪ ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስ ሊያስገኙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም አካቶ ይዟል። እነዚህ ንጥረነገሮች ለበርካታ በሽታዎች ፈውስ ከመሆናቸውም በላይ፣ በሽታው ከመከሰቱም በፊት ለመከላከል የሚያስችለንን አቅም ያጐናጽፉናል፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጠቅላላ ህክምና ክፍል ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ታዬ አለማየሁ እንደሚናገሩት፤ ሙዝ በስትሮክ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን ሞት በግማሽ መቀነስ ይችላል፡፡

የጀግና አሟሟት

ምዕራፍ አንድ፡- አጼ ቴዎድሮስ እና ሞት
አትጠገብ የምትባል ሴት ከ195 አመታት በፊት ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ ወይዘሮ አትጠገብ ሀይለ ጊዮርጊስ ከሚባል ውድ ባለቤቷ ካሣ የሚባል ልጅ ወለደች፡፡ ልጁ ካሣ ሀይሉ ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ ካሣ ሲያድግ ንጉስ መሆን አማረው፡፡ ካሣ በተወለደበት ዘመን ተራ ሠው አይነግስም፡፡ ነገሥታት የሚሆኑት የሠለሞን ዝርያ ያላቸው፣ በእግዚአብሔር የተመረጡ እና የተሰየሙ እናም የነዚህ ሠዎች ዝርያዎች ነበሩ፡፡ ካሣ ግን ንጉሥ መሆን አማረው፡፡ ሲያስብ እንዲህ እያለ ነበር ፡- “የነገስታቱ ዝርያ አይደለሁም፡፡” “እና ባልሆንስ?!” “አትቆጣ?!” “መቆጣት አይደለም፡፡” “እና ታዲያ;!” “ንጉሥ መሆን አምሮኛል!” “እና ንጉሥ መሆን የምችል ይመስልሃል?!” “Yes, I can” ብሎ ተነሳ፡፡ የአሜሪካው ንጉስ ባራክ ኦባማ `Yes, we can` የሚለውን የምርጫ መወዳደሪያ መፈክር የኮረጀው ከካሳ ሀይሉ ነው፡፡ የምናውቅ እናውቃለን፡፡

አ ገ ሬ

አገሬ ውበት ነው፣
ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት፣
ፀሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ፣
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ እስኪነጋ።
አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ፣
አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፣
ውበት ነው በበጋ ፀሃይ አትፋጅም፣
ክረምቱም አይበርድም፣
አይበርድም፣ አይበርድም።
አገሬ ጫካ ነው፣
እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት፣
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።

ከሠማይ ወረደ በተባለው መስቀል ላይ ቅዱስ ሲኖዶሡ ውሣኔ ይሰጣል

በአቃቂ ቃሊቲ ገላን ጉራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ከሠማይ ወረደ ስለተባለው መስቀል ቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ እስኪያስተላልፍ ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠባበቅ የአዲስ አበባና የጅማ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አሣሠቡ፡፡ “መስቀል ከሠማይ ወርዷል አልወረደም? ትክክለኛ ነው አይደለም?” የሚለውን ለመመለስ የግድ ቅዱስ ሲኖዶሡ ጉዳዩን መርምሮ ውሣኔ ሊያስተላልፍበት ይገባል ያሉት ብፁዕነታቸው፤ ይህን ለማድረግም ጉዳዩን ለቅዱስ ሲኖዶሱ ቋሚ አባላት እንዳሣወቁ ተናግረዋል፡፡ መስቀሉ እንደተባለው ከሠማይ የወረደ አለመሆኑ ከተረጋገጠም የቤተክርስቲያኒቱ ሃላፊዎች ይጠየቁበታል ብለዋል-ብፁዕነታቸው፡፡
መስቀሉ ከሠማይ ወረደ በተባለ በ4ኛው ቀን ነሐሴ 27 ቀን 2005 ከሠአት በኋላ ወደ ስፍራው በማቅናት ተገቢውን የፀሎት ስርአት ከካህናቱና ከቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ጋር ካደረሡ በኋላ መስቀሉን ከወደቀበት መሬት አንስተው ወደ ቤተመቅደሡ እንዲገባ ማድረጋቸውን የገለፁት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፤ መስቀሉ ከሠማይ ስለመውረዱ በአይናችን አይተናል ካሉት የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች እንደማንኛውም ሠው መስማታቸውን ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
መስቀሉን ከወደቀበት መሬት ያነሱት ብፁዕነታቸው፤ “መስቀሉ ያቃጥላል፤ ብርሃናማ ነፀብራቅ አለው” የሚባለውን አለማስተዋላቸውን ጠቁመው፤ “መስቀል የሚያቃጥል ሣይሆን የድህነት ሃይል ነው ያለው፣ የሚያቃጥል ቢሆን ኖሮ ከመሬት ላይ ማንሣት ባልተቻለ ነበር” ብለዋል፡፡ ወረደ የተባለውን መስቀል ለመመልከት ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ምዕመናን ለምን እንዳይመለከቱት ተከለከለ የሚል ጥያቄ ያነሣንላቸው ብፁዕነታቸው፤ ጉዳዩ በቅዱስ ሲኖዶሡ ተጣርቶ ውሣኔ እስኪያገኝ ድረስ ህዝበ ክርስቲያኑ ጉዳዩን በጥሞና እንዲያጤነው በማሠብ ነው” ብለዋል፡፡