ከዉቅያኖሱ ታርክ ጠብታ ስደግምላችሁ ማን ነዉ የደነዘዘዉ ወደ ምለዉ እንሄዳለን።በታርክ መፅሐፍት የበላይነት የምንጠቅሳቸዉ ታሪኮች ምን ያህል አሳማኝ እንደሆኑ ስለምያምን ነዉ።አንድ ታሪክ በሶስት ሰዎች ተሰርቶ ይቆያል፤የመጀመሪያዉ ታሪክ ስሰራ፣ሁለተኛዉ ታሪክ ስያወራ፣ሶስተኛዉ በህይዎቱ ላይ ታሪክ ይሰራበታል።ዳሩ ከዝህ ቀደም እንደጠቀስኩት ሰዉዬዉ ታሪክ ላይ ታሪክ ይጨምራል አልያም ይቀንሳል።
ከክፍል ፪ የቀጠለ
ገፅ/ልጥፍ ፫
ኻዮሉማ/xayouluma
ዋቢዬ ፀሐፊ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ስላሴ 1921 ዓ/ም የፃፉትን መፅሐፍ ጠቅሶ በመፅሐፍ ፩ ገፅ 61-62 ባስቀመጠዉ ሰንጠረዥ በ5ኛ፣በ28ኛዉና በ29ኛዉ ተራ ቁጥር ላይ ኢትዮጵስ ፩ኛ ከ1856-1800 ቅ.ል.ክ. ለ56 ዓመታት፣አንጋቦስ ፩ኛ ከ1408-1350 ቅ.ል.ክ. እና ሚአሙር በ1358 ቅ.ል.ክ. ለ፪ ቀናት ብቻ ኢትዮጵያን በአጋዝያን ዘመን ገዝቶአቸዋል ብሎ ፅፏል።በገፅ 95-97 በሠፈረዉ ሠንጠረዥ 16 ኛ ተራ ቁጥር ላይ 'አጭር የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ' ብለዉ የፃፉትን አለቃ ታዬን በማጣቀስ በ 665 ቅ.ል.ክ. ንጉስ ገስዮ ለ6 ሰዓታት ኢትዮጵያን እንደመሩ ይመሰክራል።
በእኝህ አራቱ የኢትዮጵያ ታላላቅ መንግስታት ላይ የምያደንቀዉ ያልታወቀና ያልተፃፈ ያልተነበበም አኩሪና ድንቅ ታሪክ ይኖራቸዋል። በ'ኔና በዋቢዬ ግምት ትላልቅ ታሪካዊ ክንዉኖችን አንዳከናወኑ እናምናለም።
ዛሬ ላይ ሁላችንም የታሪክ አንባቢ ከመሆን ለጥቀን ታሪክ የምንሰራበት ዘመን ላይ እንዳለን አምናለሁ አልያም ታሪክ ሳናዛንፍ መፃፍ ይጠበቅብናል። 515 ቶን ክብደት ይመዝናል ተብሎ የምገመተዉና ባስገራሚነቱ በ1972 እ አ አ UNESCO የተመዘገበዉ የአክሱም ሀዉልትም የአንድ ወቅት የኛ ብጠዎቹ የሌት ጊዜያቸዉን በመቆጠብ ለትዉልድ አዉርሰዋል።ገድለ ላሊበላ ዘቅዱስ መድሐኒዓለም 1157-1197 የተገነባዉ ዉቅር አብያቴ ክርስትያናት በ20 ዓመት ዉስጥ የተጠናቀቀዉ የኢትዮጵያዊያን አኩሪ ትዉፊት ነዉ።ጎኑ ዛሬስ ትዉልዳችን ምን እየሰራ ነዉ የምለዉ ነዉ ዋናዉ ጥያቀዬ ።
የምናየዉ አርተፍሻል
የምንሰማዉ አርተፍሻል
የምነፍሰዉ አርተፍሻል
የምንኖረዉ አርተፍሻል
ስሜታችን አርተፍሻል
ምኞታችን አርተፍሻል
ዉበታችን አርተፍሻል
ምቾታችን አርተፍሻል
ህይወታችን አርተፍሻል.............
የእዉነት ዘሪቱ እየፃፍኩ ልቤን ነካችዉ \\ምን ይሁን በዝህ ጊዜ ተፌጥሮን የምያዳምጠዉ የምሰማዉ የምያዳምጠዉ የምያወራለት ይህ የዘሪቱ ጥያቀ ብቻ ሳይሆን የነም ነዉ። በብዙ የልቦለድ ፀሐፊያን ልቦለድ ተወልዷል ድርሰትም ተደርሷል ታሪክም ተተርኳል ሰዉ ግን በጆሮ ማዳመጫዉ የራሱን ዳንኪራ ያዳምጣል።በየዜና ማሰራጫዉ በየምርምሩ ማዕከሉ የምሰሙ የተፌጥሮ ጉዳይ ዘገባዎች እንቅልፍ እየነሱኝ ነዉ።በአሁኑ ሰዓት እድል ላንዳንዶቹም እንቨስትሜንት ምንጭ ሆኗል።
ዘሪቱ ምን ነበር ያልሽኝ?
ዉብ ዓለም ላይ አርተፍሻል
ዉብ ምድር ላይ አርተፍሻል............
ስለእዉነት ማን ይሁን ተጠያቂዉ?
ባማረዉ ምድር አርተፍሻል ኑሮ የጀመረዉ።በዉብ ዓለምና ሀገር ላይ አርተፊሻል ህይወት የምንመራዉ፤ምን ይህል ላርተፍሻል ተገዥ ብንሆን ነዉ።ጎኑ በሀገራችን ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ ዉበቶቿን ሳይሆን ስሟ ራሱ የዉበት መጠሪያ መሆኑን ከብዙ ክርክር በኋላ እንደታመነበት ዋቢዬ በመፅሐፍ ፩ ላይ አስፍሯል።
"በዝያ ባልሰለጠነዉ የግርክ ፒክቶግራም ሆሜር ከኤልያድ/Iliad) እና ኦድሳይ(Odyssay) ላይ 'በኢትዮጵያ የሚኖሩ ህዝቦች እጅግ ሀያላን እጅግ የሚያምሩና የተከበሩ ናቸዉ።' ይላል፤መዝሙር ቁጥር 423 ላይ።
'የአማልዕክት አባት ዜዉስ ሀያላኑን ኢትዮጵያዊያንን ለማየትና አብሯቸዉ ምግብ ለመብላት /ማዕድ ለመሳተፍ/ ወደ ታላቁ ወንዝ ይወርዳል።' እያለ የተረከዉ ከ1000-900 ቅ.ል.ክ. ባለዉ ጊዜ መካከል ነበር። ያነ 'ኣይቶኦቲያ/AIOTOPIA/ ተብሎ የሚነበብ ያልሰለጠነ ፊደል ነበር የነበራቸዉ።"
ይቀጥላል.....................
ኻዮሉማ/xayouluma
No comments:
Post a Comment