- በአካባቢው የሚታየው ውጥረት ግን ቀጥሏል፤
ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሰገን አካባቢ ዞን የኮንሶ ወረዳ ሕዝብ ከመዋቅር ጥያቄ ማቅረብ ጋር በተያያዘ ደረሱብኝ ያሏቸውን ችግሮች ለማጣራት ቃል ገቡ።

የኮንሶ ሕዝብ በዞን ደረጃ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በቅርቡ በይፋ ከማቅረቡ ጋር ተያይዞ የክልሉ መንግሥት
ባሰማራው ልዩ ኃይል ወታደሮች እየተወሰዱ ያሉ ኢ-ሰብአዊ እርምጃዎችን በመቃወም ከአካባቢው ኅብረተሰብ የተውጣጡ
የሀገር ሽማግሌዎችና በኅብረተሰቡ የተመረጡ የኮሚቴ አባላት ጥቅምት 29 ቀን 2008 ዓ.ም አቤቱታቸውን
ለጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅርበዋል።
ጠ/ሚኒስትሩም የኮንሶን ሕዝብ አቤቱታ በጽ/ቤታቸው ከተቀበሉ በኋላ ወዲያውኑ ከተወካዮቹ ጋር በስልክ የተነጋገሩ ሲሆን፤ በዚህም ንግግር አንድ ቡድን በማቋቋም ሁኔታው እንዲጣራ እንደሚያደርጉ ለተወካዮቹ አረጋግጠውላቸዋል።
ከኮንሶ ለአቤቱታ ወደ አዲስ አበባ የመጡት ተወካዮች ለጠ/ሚኒስትሩ በፃፉት ደብዳቤ፤ የኮንሶ ሕዝብ የመዋቅር ጥያቄ በሠላማዊ መንገድ አቅርቦ ምላሹን በጉጉት እየጠበቀ ባለበት በዚህ ሰዓት፣ ጥያቄውን በማቅረባቸው ብቻ የክልሉ ልዩ የወታደር ኃይል በማሰማራት ሰዎችን ወደ ማሰር፣ ማስፈራራት፣