Monday, November 9, 2015

............."ምን ይሆን ውርሳቸው"..............

በመጀመሪያ ይህን ግጥም አንብቦ ተገብዉን ርዕስ በመስጠትና በመተየብ ለተባበረኝ ታምራት ጫ. ላቅ ያለ ምስጋናዬ አቀርባለሁ።
                      .....................................................................................................



ኦኮዬ ብያቸው ኦራታዪዮ ያሉኝ ቀን፣
ተመንደግ...እደግ...ብለዉ ስመርቁኝ፣

ከተሸበሸበው ቆዳቸው ርቄ ሳያቸው ፣
ግሩም አሮጊት ናቸው እድሜ ያልገደባቸው፣
ርተው ሠርተው ዘመን ያልሻራቸው፣
ጥረው ግረው መከራ ያልበገራቸው፣
ወልደው ወልደው ልጅ ያልወጣላቸው፣
መክረው መክረው ልብ ያልገዙላቸው፣
አዝለው ተሸክመው ማንም ያልጦራቸው፣
ከአያት የወረሱት ጥንካሬ ያላቸው፣
በላብ የቀለመ አንባር ነው ውርሳቸው፣


እናዬ...ያሉኝ ወቅት ጆሮ ስሰጣቸው፣
ይሄ የምታየው ና ሳታየው ያለፈው፣
እያንዳንዱ ቅንጣት እያንዳንዱ እምንት
የህዝባችን ላብ ነው፣


ድንጋይ ዘርተው ድንጋይ ያበቀለው።

በክረምት የዝናብ ወቅት የፀሓይ ግግርት፣
በበጋ በ
ይ የህዝባችን ስቃይ፣
አምላኩ ብቻ ነው መከርንውን የምያይ።


ከብዙ ኦላህታ በፍት በመከራ ስናቃስት፣
ቋጥኝ ስንቋጥን ከሰው ሳንቆጠር ጉያ ስንከተት፣
እምነት ነበር በተስፍችን እንደሚያልፍ ልፋታችን፣
እንደሚታይ ታሪካችን እንደም ያስጨፍ
ሙዚቃችን፣
ከጆሮአቸው 'ንደምያርፍ ጥያቄያችን፣



ያለኝን ስያስብ 

ሄው ሁለት ኦላህታ ተከልን
ተግሳጻቸዉ  የታወቀኝ

 በዋካቸው ፍትለፍት፣
የባዕድ ሥልጣኔ ግፊት

 እየወዘወዘኝ ስያስብ ለዛች አያት።




ባለፈው ሁለት ኦላህታ 

ላመጣነው እምርታ፣
የካካ ስጦታ 

የአብሮነት እርካታ፣
እንደ ክረምት አግቢ ታይቶ የሚጠፋ ደስታ ፣
ሰብል በሰብል ላይ ሁካታ 

አዕዋፍ በአዕዋፍ ላይ ጫጭታ፣
ዛሬ አስተዋልኩኝ ጉልበቴ ስረታ ።




ለካስ የ'ኔም እድሜ ገፍቷል 

የውድቀት አፋፉ ላይ ቆሟል፣


 

በልፋት ቤት ሰርተን 
በአንድነት ከትመን፣
የዋህ ወንድሞቻ
ችን "ቤታችሁን አፈረሱ፣
ጫካ ገብታችሁ አዲስ ጎጆ ቀልሱ፣
የጥንቱን በመሸሽ ወደ ምዕራባዊያን ገሰገሱ።"


የምል መልክት አዘል 

ከአብራካችን ክፍይ አካል፣
ታዘን ተበተን ገምሱ ጂንካ አንዳንዱ በድሜካ ላስካ ፣
ለላው ኮንሶ ሰፈር እያለ 

እንዴ ተሰደደ በክብሩ ቀለለ፣
የውድቀ
ን ቀንበር በጫንቃው አዘለ፣
መጠለያ ብያጣ ከቤቱ ኮበሌለ።


ይሄነው ዛሬ ያለው


 የካካ ጭንቀት 
የኦኮዬ ስጋት
የቃወታው ቱሩፋት


 ወይኔ እኔ ኻዮሉማ፣
ይህ ነበር የኔ አላማ...?


ድንጋይ ዘርተን ድንጋይ አጭደን።
ቋጥኝ ፈልፍለን ቋጥኝ እንዳላዞርን፣
ክንዳችን ተፍረከረከ ጉልበታችን ዛ

ህብረት ስለጎደለ ፈረሰ በቃውሌ




 ኻዮሉማ/xayouluma

No comments: