Saturday, November 14, 2015

ሽብር ያለዉ ወድህ ነዉ፣





የፓሪስ ፍንዳታ ሽብር አይደለም፣
ጠግቦ መሞትን የመሰለ የትም ክብር የለም።

ያምስት ደቂቃ ዳንኪራ
፲ ዘላለም ነዉ በተስታ ስሰላ/ራ።
በልቶ ጠጥቶ ሳይራብ የምያልፍ፣
በሰዉ በሰይጣን በዲያብሎስም የምያርፍ፣
ቀኑ ነዉ እምባል ነፍሱ ከስጋዉ ስከንፍ።

ሽብር ያለዉ ወድህ ነዉ፣
ማረፊያዉም ቆቦ ነዉ።

ከጓሮዉ አፍጦ፣
ከተራራዉ አንጋጦ፣

ጉንጮቹ ሰርጉጠዉ፣
ቆዳዉ ተሸማቆ፣
በገዢዉ ተረግጦ፣
ካምስት ደቂቃ ህይወት የዘላለምን ሞት መርጦ፣
ባምላኩ ተስፋ ቆርጦ፣
የምኖር ነዉ ፣
አደጋ ዉስጥ ያለዉ።

ሽብር ማለት ይህ ነዉ፣
ባበሻ ላይ የተጋረጠዉ።

ኻዮሉማ/xayouluma

No comments: