በዝህ ዘመን የምስተዋለዉ አንድም የሃበሻ ሴትና ወንድ ስራ አጣን ስሉ እና ጊዜያችን ና እድመያችን እየነጎደብን ነዉ የምሉ ብዙዎች ናቸው።ዳሩ ግን ሁሉም ማለት በማይቻል መልኩ ወጣቱ፣ አዛዉንቱ፣ መበሊቱና ባልቴቱ ስራ በስራ ሆነዉ ተጠምደዋል።ግምቶች እንደምጥቁም ከሆነ ከሃገራችን ጠበሳ ያዋጣቸዉ ሴቶችን ነዉ ይላሉ። መቸም ስለመጥበስና መጠበስ ሳወራ ክረምቱ እየገባ ስለሆነ አንድ ሁለት የጠበሳ ማስታወቂያዎችን ላስነብባችዉ።
ንብረት የምድጃ በቆሎ ጠባሽ፣
እንደደወሉልን እየጠበስን ደራሽ፣
ብርድ ያኮማተረሽ እያንዳንድሽ፣
አራት ብር ይጨነቅ ንብረት የበቆሎ ምድጃ አለልሽ።
ሁለተኛዉን በኋላ እመለስበታሁ። ሴቱና ወንዱ ለመገናኘት ቦታና ታክሲ ስላላመቸ በተለያዩ ማህበራዊ ድሬ ገጾች ጥቅስ እየተገባበዙ መጠባበስ ከጀመሩ ይሄዉ አስራ አንድ ዓመት ሞላን። በርግጥ እንደቀደመዉ የጠበሳ ስነ ስርዓቱ በሆተል ግብዣና በካፌ ቡና ባይጠናከርም በምያማልሉና ቀልብ በምስቡ የአዶቤ ፎቶ ማጠቢያ አጋርነት የትዉልዱ ፍቅር ከመቸዉም ጊዜ በላይ ተጠናክሯል። የኤፍ ቢዉ፣ ቲዊተሩ፣ ጎጉል ፕላሱ፣ ስካይፒዉ፣ ታንጎዉ፣ ዋሳፑ፣ ቫይበሩ፣ ማይኮዉ፣ እናሌሎች ሳይቆጠሩ ሃበሻ ምስት ለመሆን እና ባል ለመባል የማይከፍቱት አካዉንት የለም የማይዘጉት ፍሬንድ (የተመሳሳይ ጾታ )የለም።ያም ሆነ ይህ ግን በwww.ethiospot.com፣በwww.ethiopianspersonal.com፣በwww.eskimi.com፣በwww.waplog.com እና ሰሞኑን በተለቀቀዉ www.kingslove.com የማይገናኝ የለም።





