Monday, June 22, 2015

ለምን ማን ነዉ? ለምን ምንድን ነዉ ?





"ለቀድሞዉ የዩንቨረሲቲዉ የቦርድ ሰብሳቢ ቶም ላቅ ያለ ምስጋናየን ልያቀርብ እገደዳለሁ።በተጨማሪም ለቦርድ ሰብሳቢነት ስትፎካከሩ የነበራች ሁ ሶስታች ሁንም ላሳያች ሁት ፍኩክር እጅግ በጣም አመሰግናለሁ።እጅግ የከበረዉን አድናቆተን ለ አዲሱ የቦርድ ሰብሳቢ ቻንስለር ለምን አበረክታለሁ።"

ፕሮፌሰር ዳም ናንሲ ሮትወል(የማንችስተር ዩንቨረሲቲ ፕረዝዴንትና ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ)

"ከዛፍ ጫፍ ብትደርስ ምናልባት አንድ የዛፉን ቅርንጫፍ ታገኝ ይሆናል፤ነገር ግን ከኮከቦች ዘንድ ብትገኝ የዛፎችን ሁሉ ጫፍ ታገኛለህ።የኔ ተቀዳሚ ዓላማዬ ትዉልዱን ማነቃቃትና ራሰን ማነቃቃት ነው።"

ደራሲ፣ገጣሚ፣ፃሀፌ ተዉነት፣የማንችስተር ዩኒቨረሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ዶክተር ለምን ሲሳይ


ሹመትና ስልጣኑን የምሰጥ እግዛብሔር ብሆንም እኔ መርቀልሃለዉ።

ኻዮሉማ/xayouluma



ሰሞኑን ከታላቋ ብርተይን ማንችስተር ከተማ ባላት ትልቁ ተማሪ ቤት ለሰባት ዓመታት በቦርድ ሰብሳቢነት የምያገለግል ጀግና መሪ ስፈልግ ነበር።ታድያ ከዩንቨረሲቲዉ ትላልቅ ሰዎች መካከል የምደረገዉ ምርጫ ደሜ ኢትዮጵያዊዉን ለምን ሲሳይን አካቶ ብቅ ብሎ ነበር የሰነበተዉ።የዩንቨረሲቲዉ ሰራተኞች እና አመራሮችን ያሳተፈዉ ምርጫ አንድ መቶ አምሳ ሺ ገደማ ተሳታፊዎች ስኖሩት የመጨረሻዎቹ እጩ ተወዳዳሪዎች

1,ጌታ ማርክ ኤልደር ( የሃለ ሙዚቃ ዳይረክተር)

2,ጌታ ፕተር ማንደልሴን ( የቀድሞ የእንግልዝ ካቢኔ እና የመኳንንት መደብ አባል)

3,ለምን ሲሳይ (ገጠሚ)


ምርጫዉ የቀድሞዉን የዩንቨረሲቲዉ የቦርድ ሰብሳቢና አምባሳደር ቶም ብሎክሳምን ለመተካት የምደረግ የሰባት ዓመት የስልጣን ዘመን ያለዉ ሹመት ነዉ።ከስድስ ት ወር በፊት የክብር ዶክቴረቱን ከዩንቨረሲቲዉ ፕረዝዴንትና ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ የተረከበዉ ለምን ምን ነበር ወደምለዉ ያሳብ ከመሄዴ በፊት የኔ ተቀዳሚ ዓላማዬ ትዉልዱን ማነቃቃትና ራሰን ማነቃቃት ነው ያለዉን ቃል ልድገመዉ።

ለምን የሳዉዝ ባንክ ተባባሪ አርቲስት፣የለተርስ ክለብ ፍቃደኛ በጎ አድራጊ፣የህፃናትን እናስጠና ክለብ አምባሳደር፣የፎርዋርድ አርጽ ፋወንደሽን የቦርድ አባል፣ያለም መፃፍት ምሽት የምረቃ ቦርድ አባልና ደጋፊ፣የደብዳቤ አፃፃፍ የክብር ዶክተር እና ገጣሚ ነዉ።

ለምን የደረሳቸዉ ግጥሞች በጥቅቱ በየድሬ ገፁ የተለቀቁ ስ ሆኑ እኝህን ያካትታሉ ስራዎቹ
    articles/አርትክል,records/ሪከርዶች, broadcasts/የብሮድካስት ስ, public arts/ፐብልክ አርቶች,commissions /ኮሚሽኖች እና plays/ተዉነቶች።በሎንደን ኦሎምፒክ ከታዋቂዉ የማርቆሱ ገጣሚ በዉቀቱ ስዩም ጋር ከሀገሩ እንግልዝ ወክሎ የቀረበዉ ለምን ብቻ ነበር።በመላዉ ማንቸስተርና በመዲናዋ ሎንደን የተወደደለት ስራ Landmark Poems ነዉ።ለሽልማት ካበቁት ስራዎች ዉስጥ አንዱ Something Dark   በዋልስ ብሔራዊ ትያትር የክብር ሽልማት ከJohn McGrath
 እጅ ተቀብሏል። ቢቢሲም ስለሱ ስራ እና ህይወት በቴለቪዥን Internal Flightና በራዲዮ Child of the State ለሚሊየኖች ዓይንና ጆሮም አድርሷል።

 ለዩንቨረሲቲ ቻንስለርነት ተወዳድሮ ከማሸነፉ በፊት I am the only candidate for chancellor who is being honoured by the university at the same time. ስል ስለራሱ ምስክርነት ሰጥቷል።

መምረጥ ከምገባዉ ..........................................................143,915
በልጥፍ በፖስት የመረጡት..............................................111
በኦንላይን የመረጡት.......................................................17,772
አጥቃላይ የመራጮች ብዛት ............................................ 17,883

ለለምን ሲሳይ .................................................................7,131
ለጌታ ማርክ እልደር.......................................................5,483

ለክቡር ጌታ ማንደልሰን.................................................5,269

መርጠዋቸዋል!!ለምንም በአንደኝነት ምርጫዉን ማሸነፉ ተዘግብዋል።

 ይህ የጥቁሮች ልጅ ያባቱን ህልም እንደፈፀመዉ ኦባማ የስከት ዘመን እንድሆንለትና የመጀመሪያዉ ጥቁር ኢትዮ እንግልዛዊ ጠቅላይ ሚንስተራቸዉ እንድሆን ተመኘዉ።

ምስል ከፈለጉ ይህ ይጫኑ!!!

 ከለምን ሲሳይ ጋር መገናኘት የምትፈልጉ በሙሉ በማንችስተር ዩንቨረሲቲ ከፍተኛ የህዝብ ግንኝኙነት ኦፍሴር አሮን ሃዋርዝ አማካኝነት ያገኙታል።
 Tel: 0161 275 8387
Mob: 07717 881563
Email: aeron.haworth@manchester.ac.uk


No comments: