Saturday, June 13, 2015

1,400,000,000,000,000,000,000 ዶላር ነች ወራዊ ገቢዬ።

እስት ዛሬ ደግሞ ቁጥር ከማይፍሩት አፍሪካዊያን ጋር ላገናኛችሁ። ምንም ቁጥር አይፈሩም በቃ ለነገሩ ቁጥሩ ላንዳንዶቻችን ተዓምር ልመስል ይችላል።አንድ ጓደኛችሁ ቁርስ ልጋብዛችሁ ብል ስንት ብር ያወጣላችኋል።ከ፭ ብር እስከ ፳ ብር ይሆናል። ምን አላት የምንል ከሆነ ተሳስተናል።ይህ ብር በመንግስቱ ሀይሌ ማሪያም ሃገር ዝምባብዌ የገንዘብ ንጣፍ ልሰራላቸዉ ይችላል።

"ከዶላር ተምች እግዘሩ ይጠብቃችሁ!!"
ይህ የምትመለከቱት ዶላር ላሜሪካኖቹ አርባ ሳንቲም ነዉ።
ኻዮሉማ/xayouluma

እድመ ዘመናችሁን ጥራችሁ የማታገኙትን ነገር ግን እዝህ ሀገራችሁ ለሚጢጥዬ ቲ -ሸርት የምታወጥዋት ገንዘብ 175 ቁጥር ትፅፉና አስራ አምስት ዜሮዎችን ትደረድራላችሁ ከዝያም አንድ መቶ ሰባ አምስት ኳድርልየን(መምህራችሁን ጠይቁት ምን ማለት እንደሆነ)ብላችሁ ትጠሩታላችሁ።መቶ ብር ማለተ ነዉ ፋራ ሁላ!! ልክ ከገንዘብ ጋር እንደተወለድክ አፍህን አትክፈት በሙጋቤ ሀገር ትልቅ ዋጋ ያለዉ ሰዉ እንጅ ገንዘብ አይደልም።ከምንም ነገር በላይ እነሱ ሀገር የሰዉ ልጅ ዋጋ በጣም ትልቅ ስሆን በጣም ርካሹ ደግሞ ገንዘብ ነዉ።ሶፍት መግዛት ብፈልጉ የፍቅር እስከ መቃብር መፃፍን ስድስት እጥፍ የምሆን ገንዘብ ያወጣሉ።ባገራችን "መንግስት ግንባር ቀደም አርሶ አደሮች በ25 ዓመት ልፋት ወደ መካከለኛ ሚሊንየርነት እየተቀየሩ ነዉ" ማለት የማይሰለጨዉ ተመስገን በየነ አንድ ቀን ዝምብዝብዌ ብሄድ ያገራችን ህዝቦች "በኳድሪሊዬን መርፌ መግዛት ጀመሩ" እያለ ቱልቱላዉን ይነፋ ነበር።ዳሩ ምን ያደርጋል የምሄድበት በጀት የላቸዉም ።አንድ ክፍል የምለጥፍ ጋዘጣ ለመሸመት ዘጠኝ ክፍል የምለብድልን ዶላር እናወጣለን ከመንጌ ጋር ብንሰደድ።አንድ የክብርት እንጨት ለመግዛት በጆንያ ሙሉ ዶላር ልንቆጥር እንገደዳለን።ወይነ ኻዮሉማ!!!



የምግርሙ ያገራችን ተቃዋሚዎች ኢትዮጵያ ፵/40 በመቶ የዋጋ ግሽፈት አሳይታለች እያላችሁ የምታደነቁሩን የሙጋቤን ሀገር የዋጋ ግሽፈት አታዉቁትም ልበል? በሉ ልንገራችሁ መሰለኝ። በ2008 መጨረሻ ላይ 231 ሚሊየን %(በመቶ ) የዋጋ ንረት ተከስቶባታል።ይገርማል ያገራችን ተቃዋሚዎች ባለፉት ወራት የሳንቲም አድማ አድርጋችሁ መንግስት እንደማትጎዱት በመገመት አይቶ ዝም አላችሁ አይደል? በርቱ ግን የምትደብቁት ሳንቲም የኢህአዴግ ነዉ ወይስ የህዝቡ ነው? በርግጥ በ2013 ዝንባብዌ በሃገሪቱ የሳንትም እጥረት አስጨንቋት የ ፲ ሚሊዬን የአሜሪካ ዶላር አሳትማ አሁንም የት እንደገባ ሳይታወቅ ተሰዉሮባቸዋል ሙጋቤና ቤተሰቡ።ዜጎቹ በጃቸዉ ለመንካት የተፀየፉት ገንዘብ እንድህ የረከሰዉ ሙጋቤ ከተሾመ በኋላ ነዉ ይላሉ።ግን ይህ ሙጋቤ የምባለዉ ሰዉየ ደሞዙ ስንት ነዉ ሳትሉም አትቀሩም ሀበሻ አይደላች ሁ። አራት ሺ የአሜሪካ ዶላር( 1,400,000,000,000,000,000,000 ዶላር ነች ወራዊ ገቢዬ።)ነዉ።

ኻዮሉማ/xayouluma
  • President Barack Obama (USA) — US$33,000
  • President Jacob Zuma (SA) — US$21,000
  • Prime Minister David Cameron (UK) US$ 20,000
 ለተጨማሪ  Zimbabwe President Mugabe has revealed that he earns US$4,000 per month

 Zimbabwe is paying people $5 for 175 quadrillion Zimbabwe dollars
 Zimbabwe dollars phased out

Zimbabwe admits hyperinflation defeat, urges currency trade-in for U.S. dollar bills 

No comments: