Tuesday, June 16, 2015

ኢትዮጵያዊ መሆኑን እያጣራን ነው !!!!!

 "የግድያዉ ሰለባ በደረሰባቸዉ ኢ-ስብዓዊና አሳቃቂ ግድያ የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ አዝኗል ዳሩ ግን የሟቹ እዉነተኛ ማንነት ኢትዮጵያዊ መሆኑ በአመራሮቻችን አማካይነት ከዝህ ሰዉ ልከን እያጣራን ነዉ።"
ተደራቢ ጠ/ሚ ሬድዋን ሁሴን

"በግለሰቦች ፀብ አጫሪነት ለተፈጠረዉ አሳቃቂ ግድያ መንግስታችን ማዘኑን ስገልፅ የሟች አሟሟት ምንም ነገር ከፖለቲካ ጋር የምያያይዘዉ ጉዳይ እንደለለ ደርሰንበታል። "
ተጠባባቂ ጠ/ሚ ቴዎድሮስ አድሃኖም

"ጉዳዩ የወንጀልና የህግ ጥሰት ስለሆነ ወንጀለኞችን አሳደን ከያሉበት አምጥተን ፍትህ ለመስጠት እየሰራን ነዉ።"
ህዝብ አልባዉ ጠ/ሚ ኃይሌ ማሪያም ደሳለኝ

"ከታሰርኩም ህሊናዬን አያስሩም ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይም የኔ ትዉልድ አደራ!!!!!!!"
ሟች ታጋይ ሳሙኤል አወቀ ዓለም

ኑና ከጀግኖች ተራ እንድቀላቀል የነፃነት አምሮተን ንጠቋት ነፍሴንም በሰማዕታት ወገን አሳርፏት

ኻዮሉማ/xayouluma


የተናገሩን ስመስለኝ እየቃዠዉ መሆነን አወቅኩ።ኧረ ምን ነካኝ በቀን እቃዥ ጀመር?እንደ ኢህአዴግ መች አስተኝቶን ህልም እናልም እንዳላልን ይሄዉላችሁ ኢህአዴጎች በቀትር ፀሐይ ያቃዠኝ ጀመር።ይገርማችኋል ብዕር ስይዝ ያቃዠኛል።እስክንድር ትዝ ይለኛል፤ሪዮት ትዉስ ትለኝለች፤ሽብሬ ደሳለኝ ትዝ ትለኛለች፤ ተመስገን ደሳለኝ ባይነ ይመጣል፤ሐይሌ ማሪያም ደሳለኝ በቀትሩ ያቃዠኛል።ወይ ጉድ ይህ ምን ይሁን ብዬ ሳስብ ይሄዉ በብዕሩ ስለፃፈ ሳሙኤልንም  ደፉት።ሳሙኤል ምን ብሎ ብፅፍ ነዉ ሰዉ በለለበት ቀጥቅጠዉ የገደሉት ብዬ አሰብኩና የሳሙኤልን የፌስ ቡክ ገፅ ስመለከት ይህ አገኘዉት

"ዉድ የደብረ ማርቆስ ከተማ ኗሪዎች፣ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣች ሁ ከ25,000  በላይ መራጮች(ኮረጆዉን )እርሱትና ተጨማሪ ሌሎች ደጋፊዎች እና የኢህአዴግ አባላትም የማያፍረዉ ብአዴን/ኢህአዴግ ድምፅ መቀማቱን ሳያንስ በ 21/08/2007 ዓ/ም አፍነዉ ደብድበዉ ከመትረፌ ቆጭቷቸዉ እስር ቤት ለመወርወር ያለመከሰስ መብቴን እንኳን ተዳፍረዉ የሐሰት ክስ እየፈጠሩ ነዉ!! በስልኬ እየተደወለም ያልፍላጎቴ ደህንነት እያስገደደኝ ይገኛል!! ተገደልሁም ታሰርሁም፣ታፈንኩም ነፃነት አይቀርም እና ለማስረጃነት የደህንነቶችን ስም፣ፎቶ ግራፍ እና ዋና ተወካዮችን የደብረ ማርቆስ ከተማ 04 ቀበሌ አመራሮች እና ፖሊስ ለታሪክ አስመዝግባለሁ ማንኛዉም የምከፍለዉ ዋጋ ለሐገሬ እና ለነፃነት ነዉ።ከታሰርኩም ህሊናዬ አይታሰርም ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይ የኔ ትዉልድ አደራ!!! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም ትግላችን የነፃነት ጉዟችን ጎርባጣ መድረሻችን ነፃነት ታርካችን ዘላለማዊ ነዉ ።( ከሳሙኤል አወቀዓለም የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ተወካዮች እጩ ተወዳዳሪ)June 3 at 9:10 pm
 ተመልከት ወገነ ይህን የኑዛዜ ሀሳብ በፌስ ቡክ ገፁ ያሰፈረዉ ሳሙኤል June 15/2015 ከዝህ ዓለም በድብደባ ተለየን።

ጀግንነት ይህ ነዉ እጥር ባለ አገላለፅ የሞተበት ምክንያትና ዉጤት ይፋ አድርጎ ለነፃነት ስል የሞተዉ ሰዉ ጀግና ልባል ይገባዋል።የስርዓቱ አራማጆች ደብረ ማርቆስንና 0፬ ቀበሌን ብቻ ሳይሆን መላዉ አፍሪቃን እንደት እንደምጮቅኑ የምያምላክቱ ክስተቶች የተከሰቱበት 2007 አሁን ቅጥ ያጣ መረነ ቢስ ትግባራቸዉን እንደ አጋጣሚ ስጠቅሱልን ቆይተዋል።ወጣም ወረደ ለነፃነት በሰላማዊ መንገድ ስታገል መሞቱ ለዘመነ ፍዳችን እንደማሳያ ይሆናል።(ድጋፍ እያደረጉ ካሉት የአፍሪቃ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችና የወንጀለኞቹን ማስተባበያ በየ መገናኛ ብዙሐን መስጠታቸዉ ምስክር ይሆንልኛል።የማታፍሩ ግለሰቦችና ካድሬዎች ለዝህ ታጋይ አሟሟት አነስተኛ ግምት ትሰጡት ይሆናል።ተጨንቃ ተጠባ የኖረችዉ ነፍሱን ከሰላማዊ ትግሉ በኋላ ለ15 ቀን ሳትቆይ በነፍስ በላዎች እጅ ገብታለች።ገብታም ተበልታለች።
ከላይ እንደመግቢያ የተጠቀምኩት ሀሳቦች ነገና ከነገ ቤስቲያ በኢብኮና በ ኤፍ ቢ(ሲ ንም ጨምሯት)ልነገሩ የምችሉትን አሃሳቦችን በቅድሚያ ለመጠቀስ ያክል ነዉ እንጅ እነሱም ሽምጥጥ አድርገዉ ልዋሹ ይችላሉ።ዓይኑን በጨዉ አጥቦ መዋሸት የማይሰለቸዉ አዲስ ዘመንና ካድሬ ፀሐፍትም ያወግዙን ይሆናል።ለነፃነት ከሆነማ ደካማ ሰዎች ማሰቃየቱንና መግደሉን የማይሰለቻቸዉ ኑፋቀ ናዚዝም ልመለምለኝም ይችላል የምል ሀሳብ አደረብኝ እዉነት ለነፃነትና ለነፃነት ፈላጊዎች ዓላማ መሳካት ስል እኔም(ኻዮሉማ) ሞተን መርጫለሁ።
 የግሌ ጀግና ታጋይ ሳሙኤል አወቀ ዓለም በሄድክበት ሰላማዊ ትግል ተከትየክ እንድሞት አርዓያየ ስለሆንክ አክብሮቴ ዘላለማዊ ነዉ።እንዳንተ ያሉ ለህዝብ ፍላጎትና ነፃነት ራሳቸዉን ያሳለፉ ሰዎች የሽብሬ ደሳለኝና ያንተ ዘመን ትዉልድ በመሆነ ኩራት ይሰማኝል።

ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ!!!!!!!!!!!!!

ይሄዉ እኔም ለነፃነት ተነፈስኩ።ኑ ና ከጀግኖች ተራ እንድቀላቀል የነፃነት አምሮተን ንጠቋት ነፍሴንም በሰማዕታት ወገን አሳርፍዋት

ኻዮሉማ/xayoulumaNo comments: