Tuesday, June 2, 2015

መንግስት ግንቦት 16 ስራ ያስፈታቸዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ካሳ ልከፍልለት ይገባል!


እሁድ ግንቦት 16/2007 ዓ/ም ላይ በመንግስት አዋጅና ንግርት መሰረት የተወደደዉ የሀገሬ ህዝብ ስራ ለፈታበት ካሳ ልከፈለዉ ይገባል።
ኻዮሉማ/xayouluma

ኑሮ የዝሆን ክብደት ያክል የተጫነበት ህዝቤ ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት በሰልፍ ያባከነዉን የትግል ጊዜዉን የቆመረበት መንግስት ይህን 40 ሚሊየን ህዝብ ልክሰዉ ይገባል።አሃ ምርጫ ቦርድ 38 ሚሊየን መራጮችን ነበር የመዘገበዉ፤ይሁና የምርጫ ታዛቢዉ፣አጨብጫቢዉ፣ተወዳዳሪዉ( እነ ዶ/ር መራራን ጨምሮ)እና ዳኛዉ ባጠቃላይ ሁለት ሚሊየን አይሞላም?
ከጉሊቲ እስከ ጉልበት ሰራተኛ፣ከታካሚ እስከ አካሚ፣ከገዢ እስከ ተገዢ፣ከደላላ እስከ ደሀስፖራ፣ ከስደተኝ(በሀገር ዉስጥ የተሰደዱት)እስከ አሳዳጅ እና ሌሎች ብዙ ብዙ ሚሊየን ህዝብ ከተፈፀመበት ክህደት ጋር የምስተካከል ባይሆንም ተገቢ ካሳ ልከፍለዉ ይገባል ባይ ነኝ። መብቴ መሰለኝ
ኑሮ ሱሪ ባንገት ለሆነበት ዜጋ ካርድ ካልጣልክልኝ ወየዉልህ የተባለዉ ወገን በቴሌቪዥን፣በሬድዮ፣በጋዜጣ እና በየሞባይሉ የተደረጉ ቅስቀሳዎች ለኑሮ ግብዓታችን የጠብታ ያህል ባይጨምርም ለመምረጥ ተገደናል።ተወዳዳሪዎቹስ ብሆኑ ራሳቸዉንም የካዱ ባስመስለዉ ዉድድር የህዝብ ድምፅን እንደ አየር ሁኔታ የተተነበየዉ ፭ኛ ዙር ምርጫ በሰላም ተጠናቋል። የምገርመዉ ነገር  አወዳዳሪዉ፣ተወዳዳሪዉ፣ታዛቢዉና አሸናፊዉ ፓርቲ ለዉድድሩ ድምቀት የተጠቀማቸዉ ኢትዮጵያን ለራሳቸዉ እንኳን ከኢህአዴግ በላይ ቦታ የሌላቸዉ በማስመሰል የለጠፋቸዉ ዉጠቶች አስገርሞኛል።


ዉይ ዉይ ረስቸዉ ይህ ፅሁፍ ከየትኛዉም የ አሸባሪ፣ተሸባሪ፣ፖለቲካና እምነት ቡድን አቋም አይወክልም።ኧረ አይደለም የነሱን የናንተንም ሃሳብ አይወክልም።እናቴ ትሙት ይህ አቋም የኔና የኔ ብቻ ነዉ፤የኻዮሉማ/xayouluma ና የኻዮሉማ/xayouluma ብቻ ነዉ።

ሰሞኑን በወጡት ሁሉም የምርጫ ወሬዎች ባይሆንም በአብዛኛዉ የምርጫ ልጥፎች ዉስጥ ተወዳድረዉ ለራሳቸዉ እንኳን ድምፅ ያልሰጡትና ተወዳዳሪዎች ተስተዉለዋል።ጎበዝ ነገሩ ተወዳዳሪዎቹ በምርጫዉ ዕለት ራሳቸዉን አንቀዉ ገደሉ? ወይስ  የተወዳደሩበት ፓርቲ እያለ ለፀሐዩ መንግስታችን ድምፅ ሰጡት? ካልሆነ ተቃዋሚ የምባል ፓርቲ አልነበረም ማለት ነው። ኧረ የነሱ ብቻ ሳይሆን የኔ የድሀዉ ድምፅ ራሱ በመረጥኩበት የምርጫ ጣቢያ አለመለጠፉ ገርሞኛል።

አንጋፋዉ ፍትሐዊዉና ገለልተኛዉ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በማይታክትዉ ንግግራቸዉ ለመሪዉ ፓርቲ የእንኳን ደስ አለህ መግለጫ ባደረጉት ንግግራቸዉ ዘላለማዊዉ ኢህአዴግ አሸነፊ ሆኗል።
ይሁን ግድ የለም እኔ የምለዉ ምርጫዉ በነፃ ነዉ እንደ የተከናወነዉ በጥቅቱ የመርጋ ደምወዝ፣የመርጋ ተላላኪዎች ደምወዝ፣ለፖለቲካ ፓርቲዎች የተለገሰዉ ገንዘብ፣ ለታዛቢዎች የታደለዉ ገንዘብ፣ለሚዲያና ለአነፍናፊዎቹ የተቸበቸበዉ ገንዘብ የጠላት ገንዘብ ነዉ ?
የድሀዉ የሀገሬ ህዝብ ግብር አይደለም?
አራት መቶ ሚሊየን እንደት አራከሱት?
የማያልፈለት የኢትዮጵያ ልጅ በላቡ ያጠራቀመዉ አይደለም?

ኧረ ተዉ በልሉኝ የምርጫም ጡር አለዉ!!
ይህ ሁሉ የኢትዮጵያ ሃብት አይደለም?
ይሁን ግድ የለም።
ከጠዋት እስከ ማታ በፀሐይ እየተንቃቃ የተሰለፈዉ የሀገሬ ሰዉ ከምርጫ ስመለስ ምን ይበላል ብሎ ያሰበለት እንኳ የለም !! እንዴ ለህዝብ ነዉ የምንሰራዉ አላላች ሁም??  ታዲያ ምናለበት ከየምርጫ ጣቢያዉ ትንሽ ለሆድ የምትሆን ቆሎ ነገር ብታዘጋጁ ? ይህን ሁሉ ገንዘብ ለቁሳቁስና ለቅስቀሳ ስታባክኑ ዋናዉና ወሳኙ ህዝብ ከምርጫ መልስ ምን ይመገባል ብላች ሁ አታስቡም?
አስቡት ከምርጫ መልስ እናት ልጆቿን ሰብስባ እሳት ስታሞቅ፣አባት የልጆቹን ዓይን ላለማየት በሄደበት ሳይመለስ ስቀር፣ልጆች በየቤታቸዉ የምበላ ነገር ስለሌለ ስሰደድና ኑሮ አስገድዷቸዉ እንደናንተዉ ለማጭበርበር ስጥሩ ( ይህችን ከናንተዉ የተማርናት ነች)አዲስ ቅጥረኛ ለሙስና እጁን ስዘረጋ። ሌላዉ ብቀር የወር ደምወዙ ከአስር ቀን በላይ የማይቆየዉ የመንግስት ሰራተኛ ለብድር ስሰናዳ፣ ምናለበት ለ'ነሱ እንኳን አስባችሁ ምርጫዉ ደምወዝ በወጣበት ሳምንት ብታደርጉ?

ይህ ሁሉ ስቆቃ ለደረሰበት የሀገረ ህዝብ ካሣ ልትከፍሉት አይገባም?
ዓለምያወቀዉ ፀሐይ የሞቀዉ የሰራተኛ ህግ አንድ ቀን ስምንት ሰዓት አይደለም?
እኛ ግን ለ12 ሰዓት ተገትረን የዋልነዉ ምንም ከቁብ ሳይገባ መቅረታችን ህዝቡ የተገተረዉ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጣለሁ ብሎ እንጅ በደቦክራሲያዊ አካሄድ እንድምጮቅነን አላስተዋለም።ምነዉ ሸዋ!!!!
ዴቦ ማለት የአንድ አካባቢ ማህበረሰብ ወይም ዘር በአንድ ላይ ለስራ የምወጡበት ባህላችን ነዉ። የግርኩ ክራሲም አስተዳደር ማለትም አይደል ያዉ እየተመራን ያለነዉ ከተወሰነ አካባቢ ማህበርና ዘር አይደለም? ለዛ ነዉ ዴቦ ክራሲ ማለት።
ያም ሆነ ይህ .....
ይህ ሁሉ ክሳራ ለደረሰበት የሀገሬ ህዝብ ካሣ ልትከፍሉለት ይገባል ባይ ነኛ። ደግሞ ባለጠማማ አስተሳሰቦች ካሣንና ጉርሻን ለዩልኝ።በሉ አሸርጋጆች ይህም ፅሁፍ የግንቦት ፯ እጅ አለበት በሉኝ አሉዋችሁ።
ሳልሰናበት አደራችሁን ሰሞኑን ደግሞ ሌላ ስራ የምያስፈታ የድጋፍ ምናምን ሰልፍ እንዳትጠሩን።አደራ፤ አደራ፤ አደራ

ምክንያቱም

ሰልፍ የረባ ዉጤት የማያስገኝ የቡክኖች ምርጫ ነዉ!!!!!!!

ብሏል ቼ ጉቨራ
xayouluma

No comments: