Friday, June 5, 2015

ማህበራዊ ድሬ ገፆች ማህበራዊ ህይወታችን እያደናቀፉ ነዉ ?



ከቅርብ ጊዜ ወድህ የዓለማችን ወጣትና አዛዉንት ሳይቀሩ የርስ በርስ ግንኙነታቸዉን በየማህበራዊ ድሬ ገፁ አድርገዋል። 71 በመቶ ወጣት የፌስ ቡክ ደምበኛ ፣ 23 በመቶዉ የቲዊተር ተጠቃሚ ስሆን ቀሪዉ የተለያዩ ድሬ ገፆች አሳዳጅ ነዉ፤ እንደ ፐዉ የምርምር ማዕከል(Pew Research Center) ሪፖርት መሰረት። በነገራችን ላይ ማህበራዊ ድሬ ገፆች ማህበራዊ ህይወታችን እያቃወሱት ነው ስንል በጎ በጎ ጠቃሚ ጎኖቹን አልዘነጋናቸዉም።ዳሩ ግን የማህበራዊ ድሬ ገፆች በጤናችን ላይ የተወሰነ የድብርትና የመደበት ክስተቶችን ያስከትላሉ ለማለት ነዉ።

የፌስ ቡክ ፋንክ(በጥቁሮች ዘንድ የተለመደ ባህላዊ ዳንኪራ ነዉ)መሆን ይሻሉ?

ይህ የጥናት ዉጠት እንደት ማህበራዊ ድረ ገፆች የአኗኗር ሁኔታችን ይቀይራሉ ባከባቢያችን ላይ ያለዉንም የኑሮ ዘይበ ያስረሱናል ይላል።

ኻዮሉማ/xayouluma

በርግጥ ሁሉን የፈጠራ ዉጤቶች ላይ እምነት መጣል ተገቢ አይደለም !!


የሆስተን ዩንቨረሲቲ ጥናት እንደምያመለክተዉ፤ በፌስ ቡክ ላይ በምለጠፉ ምስሎች ተመስጦ ራሳችን ከለላዉ ጋር በማነፃፀር ወደ ተለየ የቅናት መንፈስና ያለመነፃፀር ጭንቀት ይከተናል።ለምሳሌ እርሶ ከዝክ ቀደም የትዳር አጋሮን የፈቱና ባሳለፉት የፍቅር ጊዜ እጅግ የምኩራሩበት ከሆነ በተቃራኒዉ የርሶ የፌስ ቡክ ጓደኛ በቅርቡ ያደረገዉን የጫጉላ ሽርሽር ፎቶ በግድግዳዎ ላይ ብለጥፍ የምሰማዎትን ስሜት መገመት አያቅትም፤ ግምቱም ድብርት ይሆናል ይላል።ተመራማሪዎች ደርሰንበታል እንደምሉት ከሆነ ይህን መሰል አጋጣሚ የራሶን ይህወት ልያዛባዉ አልያም ልያናጋዉ ይችላል። የዩንቨረሲቲዉ መምህርና የጥናት ቡድኑ አባል ማኢ ኤልዋይ ንጉየን ስትሪት(Mai-Ly Nguyen Steers) እንድህ ስሉ ይገልፃሉ

"ፌስ ቡክ የማህበራዊ ግንኙነታችን ያጠናክራል እንላለን ይህ ግን ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የምኖረዉ ከዝህ ቀደም የነበሩን ወዳጆች አጠገባችን ሆነዉ ድምፃቸዉን አሰምተዉ እየኮረኮሩን ካላጫወቱን ምኑ ላይ ነው የማህበያዊ ግንኙነታችን የምተሳሰረዉ?"

ብለዉ ሃሳባቸዉን በጥያቀ ይገልፃሉ።በጥናቱ የተሳተፉ ተጠቃሚዎች ከ 30 እስከ 60 ደቂቃዎች በቆዩ ቁጥር በሀሰተኛ መርጃ ላይ መሰረታቸዉን ይጥላሉ።

ቀናተኛ ኖት? በፌስ ቡክ ላይ ማድፈጥዎን ያቁሙ!!

በጣም ስለምያፈቅሯት የፍቅር አጋሮ ሁለ በፌስ ቡክ የምወራዉን ማየት ያዘወትራሉ?
ወይስ ወደ ክፍላገር የምዘዋወሩ የስራ አለቆቻችሁን በጥብቅ ይቀታተላሉ?

ለምሳሌ በሀገራችን ምሳሌ የምሆንልን የዉጪ ጉዳይ ሚንስተራችን ይዉሰዱና እሳቸዉ የስራ አለቃችሁ ብሆኑ ብለዉ ያስቡ፤ከዝያም የሳቸዉን እያንዳንዷን ልጥፍ ይከታተላሉ ብየ ልጠይቃችሁ?

ስለተቆጣጣሪዎ እያንዳንዷን በራሪ ልጥፍ ለማወቅ መጣርዎ መሪዎትን እንደ አርዓያ ልመለከቱ ይችላሉ ይህ ግን መቶ በመቶ ጎጅ ልማድ ነዉ ይላል የኮሎምቢያዉ መሶሪ ዩንቨረሲቲ( University of Missouri in Columbia)።

በተደጋጋሚ የምናደርገዉ የአካዉንት አሰሳ ከተከታተለብን ራሱን ወደቻለ ጭንቀት ልያድግብን ይችላል።
የስትራተጅክ ግንኙነት ፋካሊቲ ሃላፊ የሆኑት መምህር ማርጋረት ኢ ዱፊ( co-author Margaret E. Duffy, chair of the strategic communications faculty at the Missouri School of Journalism.)ይናገራሉ ከመሶሪ ዩኒቨረሲትይ የጋዘጠኝነት ትምህርት ክፍል።
ዱፊ እንደምሉት ከሆነ "አዘዉትረዉ የምከታተሉት የፌስ ቡክ አጋሮ ወይም ገፅዎ በየ ዕለቱ የአስደናቂነት ስመቱ እየቀነሰባ ሁ ስመጣ ራሳች ሁን እንድህ ብላችሁ ጠይቁት ለምንድን ነዉ ይህን ድርጊት ደጋግመ የምያደርገዉ?"

"መምህሩ ሳክሉም በየቀኑ ቸክ አድርግ ብሎ ዉስጥክ እያነሳሳ ግን በድብርት መንፈስ ሁለ የምትጠቀም ከሆነ ራስ ህን ፈት ሽ፤ይህ ስሜት አዎንታዊ ነዉ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረብኝ ነዉ ብለክ ጠይቅ።"

በቲዊተርም ብሆን እያንዳንዷን እንቅስቃሰዎን አይለጥፉ !!

እንደምታዉቁት ከቅርብ ጊዜ ወድህ ሁሉም የፌስ ቡክ ማህበርተኛ እያንዳንዱ ክስቱን እየለጠፈብን ያሰለቸንም ይኖራል።እኔ በግል አንዳንድ የታዘብኳቸዉ ሴቶቻችን ጠዋት ከንቅልፍ ስነሱ ምስላቸዉን ያሳዩናል ትንሽ ቆይተዉ ቁርስ ስበሉ አረፍ ሳንል ፀጉራቸዉን ስፈቱ አልያም ስያስሩ ለጥቆ መስተዋት ላይ ስገተሩ ረፋዱ ላይ ቀጠሮአቸዉን ለመሄድ ታክሲ ስጠብቁ ከታክሲ ከወረዱ በኋላ ከቀጠራቸዉ ሰው ቀድመዉ ያሉበት ሆቴል ከዝያም ከቀጠራቸዉ ሰዉ ጋር እየተሳሳሙ እየተላፉ ፎቶ ያሳዩን እና ደፈር የምሉት የአልጋ ላይ ትግላቸዉንም ልያሳዩን ይሞክራሉ። ይህ ሁሉ ማስታወሻ አስፈላጊ አይደለም ማለተ ሳይሆን ይህ ሁሉ መለጥፍ አለበት ወይ ነዉ ጥያቄዬ

ይህ ድርግት የማህበራዊ ህይወታችን ያስተሳስረዋል ብየ አላምንበትም ይህ አይነቱ ድርጊት የሁለቱን ሰዎች ግንኙነት የምያስተሳስር ብሆንም ከለላዉ ጋር ያለን መረብ ግን እየተበጣጠሰ ይሄዳል።ከመበጣጠስ አልፎም እስከ ዘለቀታዉ ልያዘጋጋንም ይችላል።
የቦስተን ዩንቨረሲቲ ተመራማሪዎችና የሳንቲያጎዉ ፖንቲፊሻል ካቶሊክ ዩንቨረሲቲ አጥኝዎች እንዳሉት 32 በመቶ የምሆኑት ከትዳራቸዉ የተፋቱ ሰዎች ስላለፈ ትዳራቸዉ ዳግም ምስረታ ያስባሉ።በዝህ መሰረት ያለፈዉ ትዳር እንዳይመለስ አዳዲስ የምናደርጋቸዉ ግንኙነቶች አዲስ እንቅፋት ይሆኑባቸዋል።ወደ ቀደመዉ ትዳራቸዉ ውይም ፍቅራቸዉ እንዳይመለሱ የተለጠፉት ልጥፎች ይጋርዱታል።

ስለዝክ ነዉ የማህበራዊ ድሬ ገፆች ላንዳንዶቻችን አዳዲስ ግንኙነቶችን የምንፈጥርበት ስሆን ለሌሎቻችን ግን ያለፈዉን ፍቅራችን እንዳይመለስ የምጋርድ ግድግዳ ነዉ።

ስለዝክ ወዳጆቸ በምትጠቀሙት የማህበራዊ ድሬ ገፆች ግንኙነታችሁ ስለነገዉም አስቡበት እላለሁ።

ሀሳባችሁን ልታጋሩ ትችላላችሁ !!

ኻዮሉማ/xayouluma

http://www.latimes.com/health/la-he-social-wellbeing-20150606-story.html

No comments: