Saturday, June 6, 2015

የሩዋንዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነባሩ ፕሬዝዴንት ሶስተኛ ዙር የምወዳደሩበት የህገ መንግስት ጥሰት ለመፈፀም ተስማሙ።"ይህ ህዝቤ ዉሳኔ የሩዋንዳ ህዝብ በራሱ መብት የመምረጥና የመወሰን መብቱን መጠቀሙን የምያሳይ አስተማሪ ዉሳነ ነው።"
ፓዉል ካጋሜ(የሩዋንዳ አርበኝች ግንባር ሊቀ መንበር )

"እኛ እንደፓርቲያችን ትናንቱኑ ለሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕረዝዳንቱ ፈር የለቀቀ የስልጣን ጥማት የሀገሪቱ ህገ መንግስት አንቀፅ 101 የምጣረስ መሆኑን ጠቅሰን አመልክተናል።"
ፍራንክ ሀበንዛ(የአረንጓዴ ፓርቲ ፕሬዝዴንት ለ ኤ ኤፍ ፒ ከተናገሩት)

"የሃምሳ ሰባት አመቱ ፕሬዝዴንት የወሰኑት ዉሳነን ሊያጠኑት ይገባል።"
የአሜሪካ መንግስት

እንዴ እኝህ የአፍሪቃ መሪ ተብዬዎች ወንበር ላይ ከተቀመጡ መነሳት ያስጠላቸዋል ወይ?

ኻዮሉማ/xayoulumaበመቶዎች የምቆጠሩ የሰዉየዉ አሸርጋጆች ባለፈዉ ሰኞ ዕለት አደባባይ በመዉጣት ለቀድመዉ የሁቲሲ አማፅ ኮማንዶ
 "ፕሬዝዴንታችን ይቀጥሉልን ዘንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፍቀድልን"
 ስሉም ጠይቀዋል።በፈረንጆች 2003 ዓ/ም ስልጣን ላይ የወጣዉ መሪ በህገመንግስት መሰረት ሁለት( 2003/2010) ሰባት ዓመታትን ካንቀጠቀጠ በኋላ የሩዋንዳ ህግ በማይፈቅደዉ መሰረት ለሶስተኛ ጊዜ እንድወዳደሩ ከተፈቀደ እንደኛዉ መንግስት ከምርጭዉ በፊት ዉጠቱ ተሰልቶ ለህዝብ ይፋ ይሆናል። ምርጫዉ ባይሳካ እንኳን እንደወዳጆቹ ጆሰፍ ካቢላ(የደሞክራሲያዊዋ ኮንጎ ፕሬዝዴንት)፣ ፒሬ ንኩሩንዚና( ሰሞኑን ብሩንዲን እንደምያምሳት ዘላን)፣ብለስ ኮምፓዉሬ( የቡርኪናፋሶዉ ጨፍጫፊ) እና ሌሎች እኛ እንደምናዉቃቸዉ መሪዎች። ከዝክ ቀደም ወደ ስልጣን ስመጡ የፕሬዝዴንትነት ዘመናቸዉን በጣም ያስረዙሙ የመሰላቸዉ ሰዉዬ ይሄዉ እንደቀላል ነገር አስራ ሁለት ዓመታትን አሳለፉበት ዛሬ ጊዘዉ ሮጦ የህዝቡ የእረፍት ዘመን ፈጥኖ ብመጣም
 "ካለ'ነ የምያዋጣችሁ የለም"
የራሳቸዉን ህግ አፍርሰዉ አዲስ ህግ ለማዉጣትና ለማስፀደቅ ቁጭ ብድግ እያሉ ነዉ፤ካጋሜ። በያዝነዉ ወረ የቡርንዲ ወዳጁን "አምባገነንነት መገለጫዉ በህግ አለመመራት ነዉ" ያሉን ፕሬዝዴንት ወር እንኳ በቅጡ ሳይሞላዉ ይሄዉ እነንም ህዝብ ወዶኛ ኤረ አፍቅሮኛል ሳይልም አይቀርም።
የቀድመዉ የእንግልዝ ጠቅላይ ሚንስተር የቅርብ ጓደኛ ፓዉል ካጋሜ ባሳለፍነዉ ዓመት ቦስቶን ለምገኘዉ ለቱፍቲስ ዩንቨረሲት ተማሪዎች ባገረጉት ንግግር የምከተለዉን ስሉ ነበር የፎከሩት

"በእኔ እምነት አንዳንድ ጊዜ መሪዎቻችን የዉሳኔ ሀሳቦችን ለህዝቡ አሳልፈዉ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።በመጀመሪያዉ የስልጣን ዘመነ ከፖለቲካዉ ለመዉጣት ና እረፍት ለማግኘት ባመለከትኩት ማመልከቻ መሰረት የሩዋንዳ ህዝብ በሀላፊነት ቦታዬ እንድቆይላቸዉ ባቀረቡልኝ ተማፅኖ መሰረት እስካሁን ህዝቡንና ህጉን አክብረ ቆይቻለሁ።"

ይህችን ነገር መለስ ዜናዊም እንደሙድ መያዣነት ተጠቅሟት ነበር

የማይካድለት ነገር ካለፈዉ እርስ በርስ ግጭት ጡዘት አዉጥቶ ለዛሬዉ ሰላማዊና በልማቱ አርዓያ የሆነች ሀገር ለቀጣይ ትዉልድ ማሸጋገሩ መልካም የምባልለት ትልቅ ስራ ነዉ።ዳሩ ግን ለስልጣን ብሎ ህገ መንግስት ማሻሻል ምን የምሉት ደሞክራሲ ነዉ አሜሪካን የምታክል ትልቅ ሀገር ያንድ ፕሬዝዴንት የስልጣን ዘመን አራት አመትና ከዝያም ካለፈ ስምንት አመት ስሆን የሩዋንዳ ግን ወደ ሀያ አንዳ አመት ማሳደጉ ምን የምሉ መብት ይሁን? ይህ ትናንት በእጆቹ ያረቀቀዉን ህግ በመጣስ ስልጣኑን ያራዘመ ስለነገዉስ ምን መታማመኝ ይኖረዋል እንደማያሻሻል።ይህ ማለት በየ ሰባት አመቱ የስልጣን ገደቡን የምያስረዝም ህግ ልያፀድቅ ነዉ ማለት ነዉ? ባሳለፍነዉ ሳምንት የፓርቲያቸዉን ወጣቶች በዝህ ሃሳብ ዙሪያ ለማግባባት ባደረጉት ዉይይት የሩዋንዳ አርበኞት ግንባር የወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር ሮበርት ሙቱንዳ ለአፍሪካን ሪቪዉ ስናገር

"እኛ ስንወለድ በህይወት ለመቀጠላችን ዋስትና ከቤተሰቦቻችን ዘንድ አልነበረንም ዛሬ ላይ ግን ለመጪዉ ትዉልድ የምሆን የተስፋ ስንቅ ሰንቀናል።ስለዝህ የትግል ጊዜ መሪያችን ካጋሜ ከጎናችን እንድርቅልን አንፈልግም።"

ተቃዋሚዎቹ ግን ፓዉል ካጋሜ እስከዛረ በሚዲያዉ ላይ እያደረጉት ያለዉ ፈር የሌለዉ እርግጥ ሀገሪቱን ከዝህ በላይ ማደግ የነበራት ብሆንም እድገትዋን አምቆ ይዟል።ባሳለፍነዉ ዓመት የቀድመዉ ከፍተኛ የደህንነት ሰላዩን በፖለቲካ ልዩነት ያስገደሉ እሳቸዉ ራሳቸዉ ናቸዉ፤ለባለሆቴሉ በጆሀንስ በርግ ያመቻቹት ያምሉም ጥቅቶች አይደሉም።
የዓለም አቀፉ ግጭት ፈች ማህበር የመካከለኛዉ አፍሪካ ዳይሬክቶር ተሪ ቭርኮለን የፕሬዝዴንቱን መመረጥ ይደግፋሉ።
የሀገሪቱ ገዢዉ ፓርቲ ቀንደኛ ተቃዋሚ አረንጓዴ ፓርቲ ሊቀመንበር

"እኛ እንደፓርቲያችን ትናንቱኑ ለሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕረዝዳንቱ ፈር የለቀቀ የስልጣን ጥማት የሀገሪቱ ህገ መንግስት አንቀፅ ፲፩፲ የምጣረስ መሆኑን ጠቅሰን አመልክተናል።"
ፍራንክ ሀበንዛ
ሁለት ሚሊየን ህዝብ የፈረመበት የይመረጡልን ጥያቄ ሴኔ ፮ (ዛሬ ቅዳሜ) ለፓርላማዉ እንደምቀርብ ይጠበቃል።ምንም በሚሊየን የምቆጠር ዜጋ ብፈርምም ካጠቃላይ የሃገሪቱ ህዝብ ብዛት ጋር ስነፃፀር 17 በመቶ ብቻ ነዉ።

አሜሪካም በለዘብተኝነት አስተያየት ከመወርወር የዘለለ ነገር አላደረገችም።
እኔ ግን ይህ ሰዉ ምን ያክል የተማረ ሰዉ ነው ብየ መረጃ ምንጮቸን ሳማክራቸዉ እንድህ አሉኝ

በዘጠን ዓመቱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ሪወንጎሮ የመጀመሪያ ደረጃ የጀመረዉ ፤ፓዉል 1970 ያባቱን ሞት ተከትሎ ወደ ከተማ በመሰደድ በካንፓላ ከተማ በጥንታዊዉ የካምፓላ ሁለተኝ ደረጃ የመማር እድሉን በማክሸፍ ወደ ዉትድርና እንደገባ ይጠቁማሉ።

እንግድህ መሪዎቻችን የተባረኩና የተመሰገኑ እንድሁም የተማሩና የተወደዱ ባይሆኑ ከነዝህ ጋር በመመደባቸዉ አፍርባቸዉ ነበር። ህዝብ ለመምራት ስለሀገሩ እያንዳንዱ  ስለ ሀገሩ ማጥናትና መማር አለበት ፤ ታሪኩን በሳይንስ ሳያጠና የሰለጠነዉን ህዝብ መራለሁ ማለት ደሞክራሲ በሌለበት ምርጫ እንደማካሄድ ነዉ። ይሁን ግን ሁለ የምቆጨኝ በጉብለታቸዉ ዙፋን የምጨብጡት ያፍሪቃ መሪዋች መዉረድ የምባል ነገር አያርፉም ወይ?

ኻዮሉማ/xayouluma
source:-

http://cctv-africa.com/2015/06/06/us-opposes-third-term-for-paul-kagame/

http://www.telegraph.co.uk/news/worldnews/africaandindianocean/rwanda/11631725/Rwandan-parliament-petitioned-for-third-term-for-president-Paul-Kagame.html

https://www.youtube.com/watch?v=-59gWtTo_CY

http://news.yahoo.com/rwanda-opposition-seeks-block-third-term-change-kagame-094731463.html

https://www.facebook.com/mauch.negn/media_set?set=a.455083311323600.1073741876.100004658051819&type=3

No comments: