Monday, May 25, 2015

ይድረስ ለኢትዮጵያ............

ዲዮጋን

ሰዉ ፍለጋ ከቤት ወጥቶ
እጅግ ብዙ ተንከራቶ
ተመለሰ ከቤቱ
ሰዉ ጠፍቶ ባገሪቱ።
                አዘርግ(2003 e.c)

ሌቱን ሙሉ ኣሰብኩ፣በጣም አሰብኩ፣ በመጨረሻም፣ከቤቴ ወጣሁ፣አዲስ አበባን በእግሬ እየኳተንኩ ቃኘዉ  አእምሮዬ ላይ የጥያቄ ክምር ተከማችቷል።መጠየቅ የምፈልገዉ ደግሞ ኢትዮጵያን ነዉ እናም ጀመርኩ.............

እኔማ ሰምቸ ነበር ይህች ኢትዮጵያ የምትባል ምድር እንኳን ለህዝቦችዋ በግዛትዋ የሚያልፍ አዉሮፕላኖች ይባረካሉ!

እኔማ ሰምቸ ነበር ዓለም ባንድ መሪ የምትመራበት ዘመን ይመጣል ! ያኔ በዓለም ላይ የበዛ ሰላም፣ የበዛ ጤና፣ የበዛ መተሳሰብ፣ የበዛ ፍቅር፣የበዛ አንድነት ይሆናል ጦርነት ፣ጥል ፣ጥላቻ ፣ዘረኝነት ፣ርሀብ ምቀኝነት ፣መነቋቆር  ይወገዳል!  ያ መሪ ደግሞ ከኢትዮጵያ ነዉ!

አስራ ሁለቱ አጋንንቶች ይዉረዱ



መጋቢት ፬ ቀን 1910 የሀገሬ ሰዉ የመንግስት ሹመኞች እንድወርዱለት ያቀረበዉ ጥያቀ በደጃዝማች ከበደ ተሰማ የታሪክ ማስታወሻ በተባለዉ መፅሐፋቸዉ የምከተለዉን ፅፈዋል።


ቃሉም ይህ ነዉ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ዓለም ፈጥሮ 12 ሐዋርያትን አገር ከፍሎ እንድያስተምሩ ያሰማራቸዉ ለመምሰል ላገሩና ለመንግስቱ ልማት በእዉነት እንድመሰክሩና እንድሰሩ 12ቱን ሚንስትሮች ደጉ ጌታችን አፄ ምንልክ መርጠዉ ቢሾሟቸዉ ለአገር ልማት ለህዝብ አንድነት በመምከር ፋንታ አንዱ ላንዱ ለየራሳቸዉ ጥቅም በመመልከት አገሩን አበላሹት እንጂ ለመንግስት የጠቀሙትና የሰሩለት ጉዳይ የለም።
12ቱ ሐዋሪያት በማየት የተሾሙት ሚንስትሮች 12 አጋንንት ስለሆኑብን እንድሻሩ እንፈልጋለን፤ለምሳሌ የሥራ ሚንስተሩ ተብሎ የተሾመዉ የራሱን ቤት ለመስራትና በቤት ላይ ቤት እየቀጠለ ወደ ሰማይ ለመዉጣት ይገሰግሳል።እንድሁም የገቢ ሚንስተር የተባለዉ የራሱን ሃብት ብቻ በማደራጀቱ ምንልክ ቤት ለግብር የምሆን መሰናዶ ታጥቶ ባለፈዉ ሰሞን ከርሱ ቤት ዱቀት ተግዞ ተሰናዳ። ይህ ምን ያሳያል ሁሉም የየራሱን ጥቅም ለማደራጀት መዘጋጀቱን ነዉ፤

ደጃዝማች ከበደ ተሰማ
በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሰ የህይወት ታርክ በምለዉ መጽሐፍ
ዮሐንስ አድማሱ ጽፎት ዶ/ር ዮናስ አድማሱ እንዳቀናበረዉ
አ አ ዩ አሳትሞት ኻዮሉማ/xayouluma እንዳስነበባችሁ
ከገጽ ፳ የተቀነጨበ

ይህ ጥያቀ ዛረስ አያስፈልግም ?

Sunday, May 24, 2015

ከFIFA በቀሰምነው የጎል ቴክኖሎጂ ምርጫዉን ታዝበናል.........!!!






"ተዉ የጀማል አባት እንዳይቆጭዎት ምልክትዎን ንብ ላይ ብያደርጉ ይሻሎታል!"

"ቆንጂዬ ምንነካሽ! ስያዩሽ እንድህ አትመስይም አንቺም ክህደት ትፈፅምያለሽ?"

"ማዘር አንድ X ያድርጉ ንቡን ልቆራርጡት ነዉ ያሰቡት? ምነዉ እርሶ ትልቅ ሰዉ አይደሉም ? አንደት አንድ ንብ ላይ ሶስት X ያኖራሉ ?"


ኻዮሉማ/xayouluma

"ከፊፋ በቀሰምነዉ የጎል ቴክኖሎጂ ምርጫዉን ታዝበናል።"

"እኔም ኮኒስ ዉስጥ ሆኘ የመታዘብ ተልዕኮዬን ተወጥቻለሁ።"

ዛሬ በሰፈራችን ሀይለኛ ጉድ የተባለለት ግጥሚያ ተስተናግዷል።ቅልጥ ያሌ ጫወታ ነበር ከኛ ቡድን ግርግርበቃኝካሊሲዉኮከብዋ በረኛችን አመዷ እና የጠብቀዉ ወንድም ጮርነ ሁሉ ሳምንቱም ሙሉ ስዘጋጁበት ከርመዋል።ጮርነ ትንሽ ከኔ ጋር ፀበኛ ስለነበር እኔ በግጥሚያዉ እንዳልገባ ያደረገዉ ከፍተኝ ጥረት ተሳክቶለታል።ከላይ ሰፈር ልጆች ቺንዲላስላስ ጠንበለልንፉቲሲሬግንቤ(ስሙን ቀስ ይጥራዉና ባለፈዉ በነሱ ሜዳ ስንጫወት ባደረገዉ ኮንጎ ጫማ ቅልጥመን ብሎኛል፤ዛሬማ ብሰለፍ ኖሮ ጉዱን አሳያለሁ ብዬ የታላቅ ወንድሜን ቦቲ ጫማ አድርገ ነበር የመጣሁት።)ሆነዉ በመለያቸዉ ላይ ስማቸዉን ፀፌዉ የጋሽ ሀይሌ ሜዳ ላይ ተሰብስበዋል።በነገራችሁ ላይ የጋሽ ሀይሌ ሜዳ በኛ ሰፈር የኳስ ተንታኞች አሊያን ዛሪና የምል ቅፅል ተሰጥቶት ነበር እኛ ግን ብዙም ስላልተመቸን ሜዳዉን የጋሽ ሀይሌ ሜዳ ብለን እንጠራዋለን።በዝህ ታላቅ የሰፈራችን ደርቢ ብዙ ተመልካች ይገኝል ተብሎ ይጠበቃል።ብያንስ ከ 20-34 ሰዉ ጫዋታዉን ለማዬት ትኬት እንደቆረጠ የጫዋታዉ ትኬት ቆራጭ ሲስኮ ነግራናለች። የ'ኛ ደጋፊዎች ስለ'ኛ እየዘመሩ ነዉ እንደምታዉቁት የነ ግንቤ ቡድን ልጆች ሁሉ እረኞችና የመደበኛ ትምህርታቸዉን እንኳ ባግባቡ ያልተማሩና ያቋረጡ ናቸዉ፤የኛዎቹ ሁሉም ግን የ ፫ኛ ፬ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸዉ።

Saturday, May 23, 2015

ምርጫዉ ተጭበርብሯል..............!!!




በደቡብ ምስራቅ አዲሳባ ስሟን በማልጠራት ብጠራትም እንኳን ማንም በማያዉቃት አንዲት በማደግ ላይ ያለች ሃገር አለች።ሀገሪቷ ከቅርብ ጊዜ ወድህ ባለሁለት አሃዝ እድገት ማስመዝገቧን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተሰሚነት ክፍ እያለ እየመጣላት እንደሆነ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ይናገራሉ።ሃገርቷ በመልካም አስተዳደርና በደሞክራሲ መሰረት ላይ ከነ አሜሪካና አዉሮጳ ሀገሮችም ጋር ስነፃፀር የተሻለ አፈፃፀም ታይቶባታል።ይህች በመልክዓ ምድር ያነሰች በዓለም ላይ የገዘፈች ሀገር አብዛኛው የሀገሪቷ ህዝብ የገቢ ምንጩ ወሬ በማዉራትና በማስወራት ላይ የተመሰረተ ነዉ። በዳታ ስሰላ 60 ከመቶ የአጠቃላይ ገቢዋ የምገኘዉ ወደ ዉጪ በምትልከዉ ወሬ ላይ ነዉ። የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ኻዮሉማ/xayouluma እንደምናገሩት ከሆነ የህዝቧ ወሬኛነትና ከመቸዉም ጊዜ በላይ ስላደገ ፈጣኑን የኢንፎርሜሽን መረብ በመዘርጋት ካለም አንደኛ ነች። ሀገሪቷ በተለያዩ ወሬ ብቻ በምያዘዋዉሩ ወሬኞች ብዛትም ካለም አንደኝ ነች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በአፍሪቃ አህጉርና በሌሎች ዓለማት በምገኙ መንግስታት ስር ብዙ ወሬ አቀባይ ዜጋዎቿን በማስቀጠር ካለም አንደኝ ነች።በየፖለቲካ ፓርቲዉ ፣ በየሀይማኖት ድርጅቱ፣ በየንግድ ማህበራቱ፣ በየሙያ ማህበራቱና በየመደቡ የተሰገሰጉት የዝህች አገር ነዋሪዎች በሰባቱም አህጉር በመበተን ወሬ በማፈትለክ ስራ ተጠበዋል።አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገሪቷ ለስራ ቦታ የለላት ሀገር ብሏትም እሷ ግን ገቢዋን አጠናክራ ጉዞዋን ቀጥላለች።በሌላ ሀገር ያሉ ዜጎቿ የሀገሪቱን መሪዎች አቋሜ ቢስ ብሉም እነሱም ካንዳንድ የፖለቲካ ካባዎች ስሞቁ ተስተዉሏል።
በዝህች ሀገር ነፃ ፍትሐዊ፣ወቅታዊና ታዓማንነት ያለዉ ምርጫ በየጊዘዉ ይደረጋል። ሀገሪቷ በምርጫ ላይ ባላት ተዓማንነት እነሂዉማንስ ርይት ዎች የመሳሰሉ ቀንደኛ ድርጅቶች ሁሉ ያምኗታል። እንደዉ አንደ በሆነ የፈረንጆች ዓመት ላይ 'ለምን የአሜሪካን ምርጫ አልታዘብም ?'ብላ ጠይቃም ነበር አሉ። የካርድ ቆጠራዉ በሙሉ በፕሬዝዳንቱ ምሪትና ምራቅ ስለምካሄድ የገዘፈ ታዓማንነት አግኝታለች። ታድያ በዝህ በያዝነዉ ዓመት ግን ከተለመደዉ ዉጪ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የምርጭ ማጭበርበር ክስተት ገጥሟታል። ምርጫዉ የተጭበረበረዉ ሆድ በተባለዉ ብሔራዊ ክልሏ ስሆን ክስተቱም እንድህ ነበር።

Thursday, May 21, 2015

መንግስት ያሰራቸዉ ኔትዎርኮች ይፈቱልን ?





"ለብሔራዊ ደህንነት ስባል መራጩ የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ እስክያልፍና ዉጠቱ እስክነገር ቡና እንዳይጠጣ።"
                   ኢፌዴሪ መንግስት

"አንዳንድ አልቧልተኞች ባልተፈቀደላቸዉ ቡና ቤቶች የሽብር ወሬን ስለምነዙና ሰላማዊዉን ህዝብ ስለምያሸብሩ የመንግስት ዉሳኔ ፓርቲያችን ተገቢ ነዉ ስል አምኖ በመቀበል እንደፓርቲ ተግብሯል።"
                 የኢህአዴግ አፌ ቀላጠ ሬድዋን ሁሴን

"መንግስት በህብረተሰቡ ላይ እያደረገ ያለዉ አምባገነናዊ ተፅዕኖ ፫ ሺ ዓመት ቡና የመጠጣት ባህላችን አያስቀረዉም።"
                   ኢንዢነር ይልቃል ጌትነት

"ኢህአዴግ ሰፊዉ ህዝብ ስለምርጫ መረጃ እንዳይለዋወጥ የወሰደዉ እርምጃ አግባብነት የጎደለዉ ቢሆንም የመንግስትን ዉሳኔ እንደፓርቲ በፀጋ ተቀብለናል።"
                 የቅንዥቱ አየለ ጫሚሶ

"ወያኔ አፋኝ ስርዓቱን ስር በሰደደ ህዝባዊ ጥላቻ ላይ በማድረግ በነፃነት የመናገር፣የመወያየትና ጎረበት ጠራርቶ ቡና የመጠጣትና የማማት ሰብዓዊ መብቱን የምጥሰዉን ልያቆም ይገባል።"
               የጉንቦት ፯ቱ ነጋ ብርሃኑ

"የኦሮሞ ህዝብና ሌላዉ የሃገርቱ ህዝብ ቡና ከጂማ ከተገኘበት ጊዘ ጀምሮ 'kotta buna dhuuge 'እየተባባለ ዛሬ የደረሰበትን ቡና በዘመናዊ መልክ የማፍላትና የመጠጣት መብቱ ለቦለቲካ ግብዓትነት በማሰብ ማቆም የለበትም።"
                  ዶር መራራ ጉዲና( ገነትን ያለማዕረገ አትጥርኝ ነበር ያላት)

Wednesday, May 20, 2015

አወዛጋቢዉ የካምፓስ ምርጫ


ከሰፊዉ የእንቅልፍ ጊዜዬ መስዋዕት በመክፈል ከመኝታዬ ተነስቸ ወደ አዳራሽ ገባሁ። ባዳራሹ የምርጫ ቦርድ ተወካይ ተማሪዎችና የተወሰኑ የምርጫ እንግዶች በየወንበሩ ተሰካክተዋል፤ አብዛኞቹ ዉቃቢ የነገራቸዉ ይመስል በስፍራዉ ዝር አላሉም።እኔም የመጀመሪያዬ ስለነበር ጓጉቼ ከዝክ ቀደም እናት አባቴ የወሰዱትን የቅድሜ ምርጫ ስርዓቴ ሂደት ተከታትዬ አዉራ ጣቴን ለሰማያዊ ጂቢ አሰናድቸ ወንበር ሳብኩኝ።
የኮለጁ የምርጫ ቦርድ ተወካይ ተማሪ ስለምርጫ ብዙ ያወራል።ሌላዉ በዝምታና በግርምት ይሰማል።እኔም በዕለተ ሰንበቱ የምመርጠዉን ፓርቲ እያሰብኩ ተፎካካሪዎቹን እያነፃፀርኩ ነዉ፤ በኔ የምርጫ ክልል የምፎካከሩት አንድ ጠሚንስተር፣ አንድ አርሶ አደርና አንድ የባህል ሙዚቃ ቡድን መሪ ይፎካከራሉ። በነሱ የግል ብቃት ሳልገታ በፓርቲያቸዉ አቋምና አመለካከት የተወዳዳሪዎቹ ምስል እስክለጠፍ እየተጠባበኩ ነዉ።
የምርጫ ሁኔታዉ አዲስና ለገዥዉ ፓርቲ ግብዓት እንድሆን ከታሰቡት የምርጫ ክልሎች ዉስጥ የዩኒቬርሲስቲ የምርጫ ክልል፣ የታላላቅ ፕሮጀክቶች ምርጫ ክልልና ሌሎች አዳዲስ ኢህአዴጋዊ ታክትኮችንም አካቷል። ታድያላችሁ በዩኒቬርስቲ ደረጃ ባንድ ካምፓስ ብያንስ ፩ የምርጫ ጣቢያ ይኖራል ከበዛም በየ፯ መቶ ተማሪ ብዛት የተለያየ ጣብያ ይኖራል ተባልን ከዝያም ለጥቆ ለምሳሌ ያድሳባ ዩኒቬርስቲ 14 ቅርንጫፎችና ኮለጆች ስላሉት በየኮለጁና በየግቢዉ እንደየተማሪዉ ብዛት ይለያያል ተማሪ በብዛበት በ፮ ኪሎ ካምፓስ የምርጫ ጣቢያዎቹ እንደፌደራሉ ምርጫ ክልሎች የተከፋፈሉ ስሆኑ አነስተኛ ተማሪ ባለበት የምርጫ ጣቢያዉ እንደፌደራሉ የምርጫ ቦርድ ያስፈፅማል። ይህ ስተነተን ከላይ የጠቀስኳቸዉ ሶስቱ ዕጩዎች ሳይገለጹ ለፌደራሉ ም/ቤት የምወዳደሩ 25 ፓርቲዎች ስማቸዉ ይለጠፋል ከዝያ ባለፈ የእያንዳንዱ ምርጫ እጩዎች አይለጠፍም ማለት ነዉ።
ምኑ ነዉ ያወዛገበህ አትሉኝም
ያወዛገበኝማ በኛ የምርጭ ጣቢያ ተማሪዉ የፈለገዉን ፓርቲ ብመርጥ ዉጠቱ ወደ ዋናዉ ጣቢያ ክልል አይሄድም፤ ወደ ዋናዉ ጣቢያ የምሄደዉ የምርጫ ቦርዱ ራሱ አዲስ በምያዘጋጀዉ ቅፅ ላይ የተሞላዉ መረጃ ነዉ። ይህ ማለት በኔ አረዳድ ተማሪዉና የግቢዉ ማህበረሰብ የምጥለዉ ካርድ ለይሱሙላ ይቀመጣል(ለ ኤግዝብሽን ይሆናል እንዴምርጫ ጣቢያችን የቦርድ ተወካይ አገላለፅ)ስለዝክ ተማሪ የምጥለዉ ካርድ በና ግቢ ምርጫ ጣቢያ መሰረት ከዜሮ በታች ክብደት ያዘለ ወረቀት እንጅ ድምፅ አይደለም።
ይህች የምርጫ መላኛዉ ዉጥን ከተሳትፎ የዘለለ ምንም ፈይዳ የለዉም ማለት አትመስላች ሁም
ታዛቢዎቻችንም በስሜ ገለልተኛ በጎ መልዕክተኛ ማህበር ስም እየተቀያየሩ ይመጡብናል። ይመስገን በኛ ግቢ ግን ምንም አይታሰብም የምታዘበንና እዉነቱን የምገልጥልን የሰራዊ ጌታ የሰማዩ ንጉስ የሰማያዊ ርስት ባለቤት እግዝአብሄር ብቻ ነዉ።

ኻዮሉማ/xayouluma

የሰማያዊ ነገር


ልጅ ሆኘ ህፃን ሳለሁ የዓመት በዓል በመጣ ቁጥር ካባቴ ጋር ሙግት ገጥማለሁ። የሙግቴ መነሻ የኔ ምርጫና ያባቴ ምርጫ ነበር። አባቴ በተፈጥሮዉ ድያብሎስ ስመርቀዉ የኔን ምርጫ ይጠላል። በየእንቁጣጣሹ ሰማያዊ ፋንት በ፲ ብር፣ሰማያዊ ካልሲ በ ፲ብር፣ ሰማያዊ ጫማ በ፶ ብር፣ ሰማያዊ ሱሪ 45 ብር ፣ ሰማያዊ ሸሚዝ በ37 ብር ፣ ሰማያዊ መነፅር በ 12 ብር፣ ሰማያዊ ኮፊያ በ22 ብር፣ ሰማያዊ ሻማ በ ፶ ሳንቲም፣ ሰማያዊ ፊኛ እና ት/ቤት ስሄድ ከፀሃይና ከሰቆቃ የምታደገኝን ሰማያዊ ዣንጥላ በ17 ብር ይገዛልኝ ነበር።

ጥሎበት ያባቴ ምርጫ ሰማያዊ ባይሆንም ከብጫና መሰሎቹ ይሻለኛል ብየ ነበር የምያለቅሰዉ። አድገም ት/ት ስጀምር በት/ቤት ዉስጥ ከሰማያዊ እስክሪብቶ ሌላ ተጠቅሜ አላዉቅም።መምህራችን

"ኻዮሉማ/xayouluma ላንዳንድ ጠቃሚ ማስታወሻዎች ቀይ እስክሪብቶ ተጠቅም "

ብለኝም እኔም እንደ ሪዮት ዓለም ቀይ እስክሪብቶ ፈራለሁ።

Tuesday, May 19, 2015

በቀን ሶስተ እየበላሁ ነዉ።




"ባቢ ና ግባ ቁርህን በልተህ በምሳ ዕቃ ያስቀመጥኩልህን ይዘክ ት/ቤት አትሄድም?"   እናቴ ነች

"እምቢዮ አልበላም ደግሞም ምሳ ዕቃዬ ዉስጥ እንደትናንቱ የእንቁላል ጥብስ ከጨመርሽ አልወስድልሽም እምቢዮ ትናንት የነ አቡላ ሰፈር ልጆች ተሰብስበዉ ስቀዉብኛል የናንተ ቤት ቄረ ነዉ እንዴ ሁልጊዜ የስጋ ወጥ የምታመጣዉ ብለዉኛል አልፈልግም ከዛሬ ወዲያ ስጋ፣ እንቁላልና አይብ አልበላም "   እኔ ት/ቤት ከመሄደ በፊት ከናቴ ጋር እየተከራከርኩ

"በቃ ትቸዋለሁ ከዛሬ ጀምሮ ምንም የበግ ስጋ አላበላህም  ሃኪምም የፍየል ስጋ እንዳትበላ ብሎሃል አይደል ልጄ? " ጉምጨን እየሳመችኝ ለማማባበል እየቃጣት በሌላ ዕቃ ትንሽ ፒዛና ብዙ በርገር አረገችልኝ በምሳ ዕቃዬ ዉስጥ

"እምቢ!! እምቢ!! እሱን ከሰጠሽኝ ከማይክ ጋር ነዉ የምበላዉ"

ማይክ ዉድ ዉሻዬ ነዉ። ማይክ ከምንም በላይ በርገር ነዉ የምወደዉ።
"ባቢዬ ለዛሬ ብቻ ነገ በጠዋቱ የምትወደዉን ጣፋጭ ነገር አመጣልሃለሁ "  እናቴ።

ስገባኝ

ድንዛዘ በወሬ
ያለጥቅም ያለፍሬ
ድንዛዘ በጭፈራ
ያለ ዓላማ ያለስራ
ድንዛዘ በከተማ
ሰዉ የሰዉን ብቻ እየሰማ
እንፎርሜሽን ጠዋት ማታ
አዕምሮዉን ፈታ ፈታ
(xayouluma)
ከክፍል ፩ የቀጠለ
ገፅ/ልጥፍ ፪

ባለመፅሃፌ ጋዘጠኛ ስናገር አዳም የመጀመሪያዉ ኢትዮጵያዊ መሪ መሆኑን ሳይቃወም የራሱን ሃሳብ ግን የራሱን ሃሳብ በኖህ መሪነት ላይ ያተኩራል። እኔን የምጨንቀኝ አዳም ሆነ ኖህ ቅደም ተከተሉ አያስጨንቀኝም፤ እነኝህ ኢትዮጵያዊያን በዘመናቸዉና በህይወት ተዋረዳቸዉ ለሀገሬ ምን አበረከቱ የምለዉ ነዉ። ይህን ስላች ሁ የጥንታዊ ታሪክ ፈልፋይ እንዳልመስላችሁ በርግጥ እንደማልሆንም አዉቃለሁ ጎኑ ግን የዘመኑ ትዉልድ አባል እና የቤተሰቦቼ የቦርድ ሰብሳቢ ነኝና በዘመን ታሪካችን ምን እንስራ ጉዳይን አንስቶ መጫርና መፈርፈር ነዉ።

Thursday, May 14, 2015

ስገባኝ

 ልጥፍ/ገፅ ፩

xayouluma

ጊዜ በዘመን ባለስትራነት ላይ የተገጠመ ተሽከርካሪ ጎማ ነዉ።የሰከንድ ስነ ተዋልዶ ዑደት በተገቢዉ መጥን እየተፀነሰ ከምጠበቀዉ በላይ እየተራባ ደቂቃ ሰዓት ቀን እያለ የልጅ ልጆችን እየተተካ የዘመን የዘር መነሻ ሆኖ ያገለግላል። ተሽከርካሪ ጎማ የምድርን ህዋስ ከቀኝ በግራ ከፊት በኋላ እያዋዛ ዛረ ላይ የምድርን ልብ በመቆጣጠር የደም ዝዉዉሯን ተቆጣጥሮ ሰንበት ብሏል።የዝህችኛዋንና የምትመጣዋን ዓለም የደም ዝዉዉር የምመራዉ በጊዘ ተሽከርካሪነት ላይ በመነጨ ጎማዊ ደም መሆኑ ሳይታመን ያለጥርጥር የምንቀበለዉ የመካኒክና የስነ ህይወት ፈለግ ነዉ።
ከዝህ ተሽከርካሪ ቅፅበት( ሰከንድ)በዘመን ላይ የምያኖረዉ ታርካዊ አሻራ በየዕለቱ እየተመዘገበ በፈጣሪ ቤቴ መዛግብት በመረጃ ደስክ መላዕክት እንደምቀመጥ አያጠራጥርም የፅህፈት አሰፋፈሩ በሁለት መልኩ ነዉ የመጀመሪያዉ ፈጣሪ በዝህች ምድር የምያከናወነዉ ሁሉ ሰማይና ምድር ከመፈጠሩ በፊት የተፃፈና ሁሉ በርሱ እንደምሆን በመፅሀፍ ቅዱስ አስፍሮልናል ሁለተኛዉ አሰራር እግዝአብሔር ከፈቀደላቸዉ መንገድ ዉጪ እንደ ራሳቸዉ ፍላጎት የምኖሩትን ፍጥረታት ያኗኗር ዑደት በማስተዋል በሁለት መንገድ ባንድ መዝገብ ይመዘግባል። የምናነሳዉ ዋናዉ ነጥብ በዝህ ግዙፍ ዓለም የእያንዳንዱ ፍጥረት እንቅስቃሴና ትግበራ ካለን ጊዜ አንፃር ስንመለከት ዓለም ከጊዜዉ ጋር ባንድ ፍጥነት ለመገስገስ ተስኗታል። የኛም ምድር ካሉን ተቀሪ ሳይንሳዊ ዓለማት አንፃር ስስተያይ በተሻለ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች ብሎ መገመት በህግና በህሊና አያስጠይቅም። በነዝ ህ ሰባቱ አህጉራት አሁን ከምንፀባረቁ አዕምሮአዊ ምጥቀት በተጨማሪ በየወቅቱ የምጎበኙን አስደናቂና አሳቃቂ የተፈጥሮ አደጋዎቹም አይዘነጋም።አይስተዋሉምም። ጉዱ ግን ማን ነው ጊዘን ባግባቡ እየተጥቀመ ያለዉ ብለን ሰዉን መጠየቅ አለብን።

"አልበዛም ወይ  መፋዘዙ ነቃ በሉ
አልበዛም ወይ  ማንቀላፋት
ሀላፊነትን መዘንጋት
አልበዛም ወይ ግድ ማጣት
ሀላፊነትን መዘንጋት .........."

ፀሬ አጨብጫቢ ኬምካል ያላችሁ ድረሱልን?


.
.
.
.
ባሳለፍነዉ ነባርዊ ሁነታ እያንዳንዳችን ቤት የተለያዩ ተባዮችን በፀሬ ተባይ ማጥፊያ፣ አረሞችን በፀሬ አረም ማጥፊያ፣ አደናጋሪዎችን በፀሬ አደናጋሪ ኬምካል በመርጨት ከወባ ትንኝና ከቱሃን ጋር እነ DDTን እነ ሮች killer ን ተጠቅመን አጥፍተናል። ያሁኑ ግን አቅቶናል። ልወረን ነዉ።









ኡ የሀበሻ ልጅ ስማ የሰማ ላልገባዉ ያስረዳ ያልሰማ የሰማን ይጠይቃ !!




ኡ አጨብጫቢና አኮብኳቢ መቆምያ ልያሳጣን ነው።
በየስርቻዉ በየጥጋጥጉ ያሉ የጥቅም አሳዳጆች ቀልባችን ልጠፉ ነው።ካልመረጣችሁን ካመረጣችሁን እየተባልን ነዉ።እኛ ስንቴ እንምረጣችሁ ባለፈዉ ለምርጫዉ አራት ሳምንት ስቀረዉ በየቀበለዉ ቅፅ ፎርም ላይ ፓርቲያችሁን እህአዴግን ከመረጥን ይሄዉ ሁለት ሳምን ከምናምን አለፈን። ኧረ ተዉን ፈጣሪን ፍሩት እኛም እንደናንተዉ ሴዎች ነን ጥቅም እንፈልጋለን የምንፈልገዉ ጥቅም ግን ህዝባዊ ጥቅም ነዉ። ጥቅቱን ተጠቃሞ አብላጫዉ የምጎዳበትን ቀመር አንፈልግም።በቃ ሰምታችኋል..................

Wednesday, May 13, 2015

ንድፍ ነበር ያልሽኝ?

ንድፍ ነበር ያልሽኝ?
አሁን ነዉ የገባኝ ቀድሞ መታነጹ
ላንች ተጠቦልሽ በእጆቹ መቅረጹ
ምንም ንድፍ ብሆን ብዙም የማልረባ
ካንች ዑደት ህይዎት ከቁብ ከማይገባ
ከዛች ትርፍ ጎነ አንችን የመቅረጹ
አሁን ነው የገባኝ ቀድሞ መታነጹ

ካንች ለላ መቶ ስድስት አሉ
በሱ ተማምነዉ ከኔ የተጠለሉ
ባይሆን ንድፏ አንች ነሽ
ለተጠለሉብኝ ጎኖቸ ናሙና የሆንሽ
ከኔ ዘንድ ፻፮ አንችዎች አሉ
መጠጊያ በማጣት ከኔ የተጠለሉ።
ባይሆን ንድፏ አንች ነሽ
የምረን አንች ነሽ
ለተጠለሉብኝ ናሙናቸዉ የሆንሽ።
ኻዮሉማ/xayouluma
may 2015

እጠጣዋለሁ



መጠጥን ጎጅ ነዉ አትበሉኝ
መረነ ቢስ ምክራችሁን በከንቱ አትለግሱኝ
ጠጥቸ ነዉ ሁሉን የረሳሁት
ጨልጨ ነዉ መከራዬን ያለፍኩት
ባልጠጣ ኖሮ የትናንቱን ረሃብ እንዴት እረሳለሁ?
የዛሬንስ ጥጋብ በምን አከስማለሁ?

አልኮል ነዉ አትበሉኝ
መርዝ ነው አትበሉኝ
ገዳይ ነዉ አትበሉኝ

ጠዋት ማታ ባልጠጣ እንደት እኖራለሁ
እሷን ባልጨጣት በምን እከርማለሁ

ሰምሃልን ልጥበስ ?

   

    በዝህ ዘመን የምስተዋለዉ አንድም የሃበሻ ሴትና ወንድ ስራ አጣን ስሉ እና ጊዜያችን ና እድመያችን እየነጎደብን ነዉ የምሉ ብዙዎች ናቸው።ዳሩ ግን ሁሉም ማለት በማይቻል መልኩ ወጣቱ፣ አዛዉንቱ፣ መበሊቱና ባልቴቱ ስራ በስራ ሆነዉ ተጠምደዋል።ግምቶች እንደምጥቁም ከሆነ ከሃገራችን ጠበሳ ያዋጣቸዉ ሴቶችን ነዉ ይላሉ። መቸም ስለመጥበስና መጠበስ ሳወራ ክረምቱ እየገባ ስለሆነ አንድ ሁለት የጠበሳ ማስታወቂያዎችን ላስነብባችዉ።

    ንብረት የምድጃ በቆሎ ጠባሽ፣
    እንደደወሉልን እየጠበስን ደራሽ፣
    ብርድ ያኮማተረሽ እያንዳንድሽ፣
    አራት ብር ይጨነቅ ንብረት የበቆሎ ምድጃ አለልሽ።

    ሁለተኛዉን በኋላ እመለስበታሁ። ሴቱና ወንዱ ለመገናኘት ቦታና ታክሲ ስላላመቸ በተለያዩ ማህበራዊ ድሬ ገጾች ጥቅስ እየተገባበዙ መጠባበስ ከጀመሩ ይሄዉ አስራ አንድ ዓመት ሞላን። በርግጥ እንደቀደመዉ የጠበሳ ስነ ስርዓቱ በሆተል ግብዣና በካፌ ቡና ባይጠናከርም በምያማልሉና ቀልብ በምስቡ የአዶቤ ፎቶ ማጠቢያ አጋርነት የትዉልዱ ፍቅር ከመቸዉም ጊዜ በላይ ተጠናክሯል። የኤፍ ቢዉ፣ ቲዊተሩ፣ ጎጉል ፕላሱ፣ ስካይፒዉ፣ ታንጎዉ፣ ዋሳፑ፣ ቫይበሩ፣ ማይኮዉ፣ እናሌሎች ሳይቆጠሩ ሃበሻ ምስት ለመሆን  እና ባል ለመባል የማይከፍቱት አካዉንት የለም የማይዘጉት ፍሬንድ (የተመሳሳይ ጾታ )የለም።ያም ሆነ ይህ ግን በwww.ethiospot.com፣በwww.ethiopianspersonal.com፣በwww.eskimi.com፣በwww.waplog.com እና ሰሞኑን በተለቀቀዉ www.kingslove.com  የማይገናኝ የለም።

Tuesday, May 12, 2015

ሽ............ብሬ

እንደሁኔታዉ አድርጌ ማርማራታን በዳቦ ጨምቀ በሻይ አወራረድኩና ወደ ስራዬ ሳላረፍድ አዘገምኩ።በስራ ቦታዬ አንድ ራሱን ፕሮፌሰር እያለ የምያስጠራ ዶክቶር V.K ሚሽራ ( በነገራችን ላይ የአርባምንጭ ዉድ ጓደኞቼ በዝህ ዓመት በሞት የተለየችን ዉዷ እህታችን ምሽሪያ የገዳዯ ነገር ከምን ደረሰላት በቃ የደቡብን ፖልቲካ ፊንቲዉ አድርጋ ስለዘከዘከች በመርዝ ገለዋት ዝም ጭጭ አሉ? ታድያ ምን ይደረግ አፋችን ዘግተን በራችን ቆልፌን መቀመጥ ዕጣ ፋንታችን ከሆነ ሰነባብቷል። የታጋያችን ነፍሷን ይማርልን ከማለት በዘለለ ምን እናደርጋለን?) የተሰኘ መምህር በኮልታፋዉ የሻሩክ ቅላጸ ከሰሌዳዉና ከተማሪ መሃል ሆኖ ይለፈልፋል።ይለከችራል። እኔ ግን በድነ ብቻ ታድሞ ጭንቅላተ ማታ ስያየዉ የነበረዉን ዜማ ያመላልሳል።


ላንች ነዉ ላንች ነዉ መሰዋታችን
ላንች ነዉ ላንች ነዉ ትግላችን
ህዝባዊ ሀይል ነዉ ስማችን
ኢትዮጵያ ሀገራችን
አረንጓደ ብጫ ቀዩ ሰንደቃችን
በባርነት ሜዳ ህዝብሽ የማቀቀዉ
በባለጌ ሜዳ ክብርሽ ለጎደፈዉ
ትግል ነዉ መፍትሔዉ
አሁንም ትግል ነዉ
ለቆሜ ነጻነት ለጫኑብን ቀንበር
ለናዱት አንድነት ላረከሱት ክብር
ትግል ነዉ መፍትሔዉ
አሁንም ትግል ነዉ
ለነጻነት ክብርሽ
ለአማኝ ጸአዳሽ
ለወገን ላገሩ በመስዋዕት አገልጋይ
እንደትግል መሪ
ህዝባዊ ሀይል ነዉ አክባሪ
ኢትዮጵያ ላንች ነዉ ላንች ነዉ
ደማችን የምፈሰዉ ለዘላለም ክብርሽ ነዉ
ሰንደቃችን ኢትዮጵያዊ አርማ
ጸንተናል በአንድ ዓላማ
ኢትዮጵያችን በደማችን ይታደሳል ስሟ