"ባቢ ና ግባ ቁርህን በልተህ በምሳ ዕቃ ያስቀመጥኩልህን ይዘክ ት/ቤት አትሄድም?" እናቴ ነች
"እምቢዮ አልበላም ደግሞም ምሳ ዕቃዬ ዉስጥ እንደትናንቱ የእንቁላል ጥብስ ከጨመርሽ አልወስድልሽም እምቢዮ ትናንት የነ አቡላ ሰፈር ልጆች ተሰብስበዉ ስቀዉብኛል የናንተ ቤት ቄረ ነዉ እንዴ ሁልጊዜ የስጋ ወጥ የምታመጣዉ ብለዉኛል አልፈልግም ከዛሬ ወዲያ ስጋ፣ እንቁላልና አይብ አልበላም " እኔ ት/ቤት ከመሄደ በፊት ከናቴ ጋር እየተከራከርኩ
"በቃ ትቸዋለሁ ከዛሬ ጀምሮ ምንም የበግ ስጋ አላበላህም ሃኪምም የፍየል ስጋ እንዳትበላ ብሎሃል አይደል ልጄ? " ጉምጨን እየሳመችኝ ለማማባበል እየቃጣት በሌላ ዕቃ ትንሽ ፒዛና ብዙ በርገር አረገችልኝ በምሳ ዕቃዬ ዉስጥ
"እምቢ!! እምቢ!! እሱን ከሰጠሽኝ ከማይክ ጋር ነዉ የምበላዉ"
ማይክ ዉድ ዉሻዬ ነዉ። ማይክ ከምንም በላይ በርገር ነዉ የምወደዉ።
"ባቢዬ ለዛሬ ብቻ ነገ በጠዋቱ የምትወደዉን ጣፋጭ ነገር አመጣልሃለሁ " እናቴ።
እኔና እናቴ ይህን ትያትር እያጠናን ነዉ። እሷም የዝህች የዉሸት ዓለም ተዋናይ ነች። ይህን ትያትር መሰል መራር ሀቅ የምናጠናዉ ችግራችንን ለመርሳት ነዉ።ያች ሁላችሁም የምታዉቋት የኛ ቤት ሁሉ የተሟላላት ናት፤ ማዘር ስራ የላትም እነማ ከነጭራሹ ስለ ስራ አላስብም ምክንያቱም እንደማያሰሩኝ አዉቃለሁ ይህን ስል ይገባችኋል አይደል የድርጅት አባል አይደለሁም።ሆኖም በቤታችን ምንም የጎደለብን ነገር የለም በቤታችን ባለ 60 ሻማ አራት አምፑል አለ፤ በምያሳዝን ሁኔታ እኝህ አምፑሎች ባንድ ጊዜ የምያበራ የማብራት ሀይል በእኛ ቀበለ የለም። ዳሩ ግን የቀበሌያችን ሊቀመንበር እንደነገረኝ ከሆነ ቻይናም በስፋት ስለተካፋፈለ የማብራት አገልግሎቱ እንደኛዉ ቤት ነዉ አሉ። ይህን ለእኛ ይበቃናል ድሮ ፋኖስ ሰቅለን ነዳጅ አንዳልጠበቅን ዘንድሮ በተራዉ አምፑል ገዝተን ለሃይሉ ደግሞ ተመዝግበናል፤የት ነዉ ምዝገባዉ እንዳትሉኝ እኛ ሰፈር አንድ ባለ ፲በ፳ የማብራት ቆጣሪ ለ፳ የቀበሌያችን አባና እማ ወራዎች ነዉ የተከፋፈለዉ።ጋሽ በትሩ እንደነገረን ከሆነ
"ይገርምሃል xayouluma/ኻዮሉማ በደርግ ጊዜ አንድ ቆጣሪ ለ፶ መኖሪያና ማሰርያ ቤቶች ነበር አሁን ያሁኑ ግን ለ፳ ቤቶች አንድ የማብራት ቆጣሪ ነዉ"
ብለዉኝ ነበር።
አይ ስወር እኛ ቤት የጎደለን ምንም የለም። ባለፈዉ አንድ ሌት ዘይት አትወስዱም ተብለን በቀበሌ ፩ለ፭ ህዋስ ላይ ተገምግመናል። በዕለቱ እናቴ ጉዳዩን ለማስተባበል ለህዋሱ አባላት እያለሳለሰች እንድህ አለች
"አይ እኛ ቤት ዘይት አለ።"
ይገርማችኋል ተንኮለኛዉ የቀበሌያችን ህሳብ ሹም ወዲያዉኑ መዝገብ አገላብጦ
"የኻዮሉማ/xayouluma እናት አንቺ ዘይት ከወሰድሽ ዛሬ ሶስት አመት ከስድስት ወር ነዉ።ይህ ደግሞ የምያሳየን የቀበለያችን ገቢ እየቀነሰ ነዉ።"
እያለ ብዙ ዘባረቀ።
በርግጥ እኛ ቤት አንድ ቢኮለ ዘይት ከገባ ዛሬ ይሀዉ 24 ወራት አለፉት። እማዬ ግን አሁንም ዘይቱ አለ ብላቸዋለች። ፈጣሪ በተዓምሩ ካልሆነ በቀር ይህን ሁሉ ጊዜ የበላነዉ ምግብ ያለ ዘይት እጥረት ይሄዉ ዘመን አለፈዉ። እማዬ'ኮ ዘይት መሸጫ መካዚኑን አታዉቀዉም።ያነ አንድ ዘመዳችን ነበር ሶስት ሊትር ዘይት ገዝቶ የምይዝበት እቃ ስላነሰበት አንዱን ቢኮለ ለኛ ቤት የሰጠዉ( ማለተ ተመልሽ ወስዳለዉ ያለዉ)እማዮ'ኮ የሰዉዬዉን ቃል አክብራ አልነበረም ዘይቱን ያልበላችዉ።ሰርታ የምትበላበት ምግብ ስላጣች እንጅ። የምር ዘይት ጠልታ ይመስላችኋል ይህን ያህል ጊዜ ዘይት ያልገዛችዉ? እኛ ቤት ዘይት ከተገዛ በኋላ ሀገራችን ብዙ የዘይት ፋብሪካዎችን ተክላለች፣ያረጁትን ነቅላለች፣ የሰሊጥ ምርትም ወደ ዉጪ ልካለች።
ምክንያቱ አንድና አንድ ነዉ፤ ዘይቱን የምንበላበት ምግብ በቤታችን ዝር ብሎ አያዉቅም!!!!!
ታድያ እንድህም ሆኖ እኛ መችች ተከፋን እናንተ ስትበሉ ይሄዉ እኛም ዘይቱን እንደሚካኤል ፀበል ለነፍስ ማዳኛነት ግድግዳ ላይ ሰቅለነዋል።
እናላችሁ ከላይ የነገርኳችሁ ትያትር እኔና እናቴ የምናጠናዉ ለብሄራዊ ትያትር አይደለም። ላንባሳደርም አይምሰላችሁ። ከእንቅልፍ ተነስተን የምንሄድበት ስለሌለ ነዉ የቁርስ ሰዓት ስደርስ በማይሰለቸን ትያትር ለምሳ እንነሳለን።የትያትሩ ርዝመት ከሁለት ሰዓት እስከ ሶስት ሰዓት ነዉ። እንደየቀኑ ሁኔታ ይለያያል።
በነገራችሁ ላይ እኛ ቤት ብዙ ትያትር አዘጋጅተን ለጓዳ አብቅተናል። ለምሳሌ ከዝህ ቀደም ጠሚኒስተሩ ስሞቱ ከሰራናቸዉ ዉስጥ አንድ ሁለት ዳይሎጎችን እናስነብባች ሁ። በዝህኛዉ ትያትር እናቴ አዜብ መስፍንን ሆና ነዉ እኔ ደግሞ በረከት ስምዖንን ሆኘ ነዉ የሰራነዉ። ተዋናይ እማዬ እንደ አዜብ ኻዮሉማ/xayouluma እንደበረከት
"በረ እነ በጣም ፈርቻለሁ እንደት ያለመሌ እኖራለሁ? እሱ'ኮ ለኔ ሁሉ ነገር ነዉ። ስራብ የምራብልኝ ስጠማ የምጠማልኝ ስታረዝ(እንደዉ አዜብ መቸ ታረዘች ለምትሉኝ ድሮ ድሮ ደሃ ነበረች ስባል ስለሰማሁ ነዉ) የምታረዝልኝ እሱ ማለት'ኮ ለኔ ሁሉ ነገር ነዉ።በሱ ነዉ መፈጠረ፣እኔ ብቻ ሳልሆን ልጆቸም በሱ ነዉ የተፈጠሩት " እያነባች የበረከት አንገት ስር ተወሽቃ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች
"አዜብ ምን ነካሽ መለስ'ኮ ለ፻ ሚሊየን ኢትዮጵያዊ አባቱ ነዉ እናቱም ነዉ፤ላንች ብቻ ሳይሆን ለመላዉ አፍሪቃ መለስ አባታችን ነዉ። ምንድን ነዉ እንደዝህ የራስሽ ብቻ አድርገሽ የምታስቢዉ በመለስ ራዕይ ስንቱ የኔ(ይህ የበረከት ሳይሆን የኻዮሉማ/xayouluma ብጤ ለማለት ታስቦ ነዉ)ብጤ መናጢ ድሀ አለፈለት፣ ይሄዉ እንደምታይዉ በየመንገድ ላይ አንጥፎ የምለምን የቀበሌ መታወቂያ ብቻ በመያዝ የሚሊየኖች ብር ግምት ያለዉ ቤት የሰጠዉ ማን ነዉ። ስንት ሺ አርሶ አደር ነዉ ሚሊንየር የሆነዉ ። እሱ ማለት ለመላዉ ሃበሻ የደረሰ መላዕክት ነዉ ይገባሻል።መላዕክት ነዉ እስራኤላዊዉ ነብዩ ኤሊያስን በቁራ ስጋ የመገበዉ መላዕክት ታዉቃለሽ። እንደዛ ነዉ ............."
እንባዋን በሶፍት እየጠራረግኩ ጉንጮቿን እየደባበስኩ ተቆጧት።
"በረ ይገባኛል ለ'ኔ ግን ካልካቸዉ ሁሉ በላይ ነዉ። አንተ እንደምትለዉ አደገኛ ቦዘነዉን ድንጋይ ከመወርወር ወደ ድንጋይ መደርደር፣ ታክሲ ከመጠበቅ ወደ ታክሲ መቀጥቀጥ.............."
እያለች ተንሰቅስቃ እያለቀሰች የሰራነዉን የቤታችን ትያትር አስታዉሳለሁ።(ደግሞ ለላ ለማሰራት ጋብዙን ብለናል አሉ )
በዝክ ባሁኑ ትያትር ላይ የመለስን ስልጣን ከመካፈል እስከ ማከፋፈል ያለዉን ታሪክ ባጭር ቀናት ዉስጥ ለኛ ቤት ትያትር ጓዳ አብቅተናል።አስተዉላችሁ ከሆነ መለስ ለባለቤቱ ስትራብ ተርቦላታል ስትጠማ ተጠምቶላታል ስትታረዝስ ታርሶላታል ይህ ማንኛዉም መልካም ባል ለምስቱ የምያበረክተዉ የፍቅር ስጦታ ነዉ።( ይህን መግለፅ ለምን አስፈለገ ለምትሉ ሃገራዊ ዉለታዉን ከኢቢኮ ማገኘት ትችላላች ሁ)እማዬ ግን ለዝህ ፍቅር አልታደለችም።
ለምን ይመስላችኋል ያልታደለችዉ ?
ባል ስለለላት?
ባሏ ስለማይወዳት?
ከባሏ ስለተፋታች?
ከባሏ ተስማምታ መኖር ስላቃታት?
አትሳሳቱ እናቴ ባሏን ያጣችዉ ባሏ ምንም ስላልነበረዉ ነዉ። ባሏ ምንም ስለሌለዉ ነዉ። ባሏ ሰርቶ ላበላት ስለተሳነዉ ነዉ። አባቴ አካለ ስንኩል ይመስላችኋል?
ይገርማችኋል የድሮ 11ኛ ክፍል ተማሪ ነዉ። እሱ የከዳት ለመስራት የምያስፈልገዉን የድርጅት ቅድሜ ሟሟያ ስለምጠይቁት ነዉ። 'እንዳያማህ ጥራዉ እንዳይበላ ግፋዉ አልተባለም ? በቃ ለዛ ነዉ። አባቴ ምስቱን አሁንም ይወዳታል ግን ምንም ማድረግ አልቻለም። ቤተሰብ ለማስተዳደር ፍቅር ወሳኝ ቢሆንም አብሮ ለመኖር ግን ማስተዳደር መቻል አለበት። እናቴና አባቴ የተፋቱት ምንም የምላስ የምቀመስ ስለለላቸዉ ነዉ። ከየት ያምጣ??
እዉነት እዉነት እላችኋለዉ አባቴ ሚንስተር ብሆን እመኑኝ ለናንተ ቤተሰብ አባት ይሆንላችኋል።አባቴ ካቢኔ ብሆን በየቢሮዉ የደረጃ እድገት ላስጨነቃችሁ በፍትህ ይዳኛል።የምረን ነዉ የ'ኔ አባት ሚንስተር ብሆን ለያንዳንድሽ የፈለግሽዉን የቴሌቪዥንና የሬድዮ ጣቢያ እንድታዳሚጭ ብቻ ሳይሆን እንድታወሪበትም ይፈቅዳል።
በርግጥ በረከት እንዳወራዉ ከጉሊት ቸርቻሪነት ባንደ ወደ አስመጪና ላኪነት የተቀየራችሁ የፓርቲዉ አባላት እንኳን ደስ ያላችሁ። እኛም በጣም ደስብሎናል ደስ ስላላችሁ።በ1997 ምርጫ እና ባለፈዉ ለአይ ኤስ ተቃዉሞ በወጣዉ ህዝብ ላይ ድንጋይ የወረወራችዉ ዛሬ በስትራተጅዉ መሰረት የወረወራችሁትን ድንጋይ ለደረደራችሁ ለቁርጥ ቀን ልጆች የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።እኔ የምለዉ የወረወራችሁት ድንጊያ ሰዉ ለመምታት ነዉ ወይስ ሳይት ለማድረስ ነበር ? ጎሽ ወደ ሳይት ነዉ? ይሁን !!አንዳንድ አልቧልተኞች በሰዉ ላይ ነዉ ብለዉ ስላስወሩባችሁ ነዉ የጠየኳች ሁ።
ይሁን!!
እኔና ቤቴ በቁራ እየተመገብን ነዉ!!
ይህ የምታዩት ፎቶ እዉነተኛ ታሪክ ነዉ። የነ ምስል ግን የለበትም፤ለምን ለምትሉኝ ፎቶ አንሽዉ እኔ ስለነበርኩ ብቻ ነዉ።
አመጋገባችን በቡፈ ስታይል ነዉ።ይገርማችሁ ግን ከሰዓት ከአላሙራ ሆተል አንዲት ጥቁር የሰማይ አሸባሪ ከሆተሉ በፈስታል የተጠቀለለ ቡሌ አምጥታ ስትጥልልን አንስተን እየበላን ነዉ(እንብላ )።ከዝያም የተወሰነ ሰዓት እንጠብቅና የምላስ የምቀመስ ስናጣ ካምፓስ ጓሮ ሄደን ቡሌ እንጠገርራለን። አበት!!!!!
በቦለቲካ ክርክሩ ስለ ትምህርት የተከራከራችሁት ፓርቲዎች በሙሉ አፈር ብሉ ሁላችሁም ለይምሰለ ነዉ የምታደነቁሩን። በርግጥ አሁን እያንዳንድሽ ቦልቲከኛ ወንድ ከሆንሽ መረጃና ጥናት አለኝ የምትይ በኢትዮጵያ ዩንቬረሲትዎች ስር ስንት ቡሌ ተጠቃሚ አለን? ሚሊካርድ ባይሰጠንም ቲከሮቻችን ግን በዓይን ያዉቁናል። ባሉን 34 ዩንቬረስቲዎች ዉስጥ ስንት የኛ አይነት ቤተሰብ አለን? መልሱዋ!!
አታዉቁትም ከየት ትመልሱት!!
ስለማይመለከተን ነገር ስትከራከሩ ትዉላላችሁ እኛን ረሃብ ልደፋን ነዉ፤እናንተ ስለትምህርት ጥራት ትከራከራላች ሁ። በጥራት የተማረዉ ስሰደድ ዓይናች ሁ ታዉሯል?
በጥራት የተማረዉ ያለዕዉቀቱ ስባዝን አታስተዉሉም? የማትረቢ ሁላ!!
የት/ት ጥራት ኖረ አልኖረ እኛ የምንፈልገዉ ቡሌዉን ብቻ ነዉ።ይህን ያህል ተርበናል ለምን አትረዱንም የማይገባሽ ሁላ!!
መጀመሪያ ስጋ ስያድር ነዉ ለነፍስ የምፀልየዉ!!
ስጋ ሳይኖርህ ለነፍስ ህ በምንም አትፀልይም!!
ይህን ያያችሁት ፎቶ በሃዋሳ ከተማ የነሳ ነዉ። ሙሉ ፎቶዉን ሰርተን ለመጨረስ ፭ ወራትን ፈጅቶብናል። ያዉ እንደምታዉቁት ምግቡን ስናገኝ ተመጋቢዉ ይጓደላል፤ተመጋቢዉን ስናገኝ ሞባይሉ ይጠፋል፤ ሞባይሉን ስናገኝ ባትሪ ያልቅበትና ማብራት ይጠፋል፤ ማብራቱ ስመጣ ለናንተ የምናደርስበት ኔትዎርቅ ይጠፋል፤ኔትዎርኩ በስቃይ ስገኝ ፈጣኑ የቴሌ ካርድ ያገልግሎት ዘመኑ ያበቃል እያለ በተለያዩ ምክንያቶች ድፍን 150 ቀናት ፈጅቶብናል። ሃዋሳ አላሙራ ቆጪ ገበያዉ ላይ ነዉ የፎቶዉ መቼት የተጠናቀቀዉ።
ያም ሆነ ይህ ግን ዛሬ ሁላችንም ተሻሽለን ተለዉጠን ከካምፓስ ከሆተልና ከጠገቡት ቤት በምገኝ ቡሌ በቀን ሶስቴ እየተመገብን ነዉ።
ከዝህ በላይ ለተሻለ ለዉጥ በድጋሚ ኢህአዴግን ይምረጡ!!!
በበላነዉ ቡሌ ላይ ዉሃ እንድሰጡ
ኢ ህ አ ዴ ግን ይምረጡ!!!
No comments:
Post a Comment