Tuesday, May 19, 2015

ስገባኝ

ድንዛዘ በወሬ
ያለጥቅም ያለፍሬ
ድንዛዘ በጭፈራ
ያለ ዓላማ ያለስራ
ድንዛዘ በከተማ
ሰዉ የሰዉን ብቻ እየሰማ
እንፎርሜሽን ጠዋት ማታ
አዕምሮዉን ፈታ ፈታ
(xayouluma)
ከክፍል ፩ የቀጠለ
ገፅ/ልጥፍ ፪

ባለመፅሃፌ ጋዘጠኛ ስናገር አዳም የመጀመሪያዉ ኢትዮጵያዊ መሪ መሆኑን ሳይቃወም የራሱን ሃሳብ ግን የራሱን ሃሳብ በኖህ መሪነት ላይ ያተኩራል። እኔን የምጨንቀኝ አዳም ሆነ ኖህ ቅደም ተከተሉ አያስጨንቀኝም፤ እነኝህ ኢትዮጵያዊያን በዘመናቸዉና በህይወት ተዋረዳቸዉ ለሀገሬ ምን አበረከቱ የምለዉ ነዉ። ይህን ስላች ሁ የጥንታዊ ታሪክ ፈልፋይ እንዳልመስላችሁ በርግጥ እንደማልሆንም አዉቃለሁ ጎኑ ግን የዘመኑ ትዉልድ አባል እና የቤተሰቦቼ የቦርድ ሰብሳቢ ነኝና በዘመን ታሪካችን ምን እንስራ ጉዳይን አንስቶ መጫርና መፈርፈር ነዉ።

ጫፉ ግን ወደ ኋላ ልመለስና ኖህ ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ጋዘጠኛዉ ታኖሩትን ማስታወሻ እንመልከት

"ኖህ በዝህች አገር እየኖሬ ሣለ ባለበቱ እሜቴ አይከል ሞቱበት።የሞቱትም ከጎንደር በስቴ ምዕራብ በኩል በምትገኘዉና ከከተማዉ 37 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ባለችዉ 'ጭልጋ' ተብላ በምትጠራዉ ምድር ነበር። ጭልጋ ዉስጥ እሜቴ አይከል የተቀበሩበት መቃብር እንደሆነ በሚታወቀዉ ቦታ ላይም ትልቅ ዛፍ በቅሎበት እስከዛሬ ድረስ የቅማንት ብሄረሰቦች ፀሎታቸዉን ያደርሱበታል። የመቃብራቸዉ ሀዉልትም ዛሬ ድረስ ጭልጋ(አይከል)ዉስጥ ይገኛል።"

በማለት በገፅ 23 ላይ አስፍሯል።
ዋቢዬ እንደምንጠቅስልኝ ከሆነ እግር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ ገነትን የዓለም ህዝብ በሰሜናዊዉ ኢትዮጵያና ባካባቢዉ እንደኖረ ልያሳምነኝ ሞክሯል።

በወቅቱ ዓለምን ይመሩ የነበሩት አፄ አዳምና ንግስተ ሄዋን በኢትዮጵያ ብሎም ላለም የእፅዋትና የእንስሳት ክብካቤና ቁጥጥር እንደተጠመዱ የተቀበልነዉ ጉዳይ ነዉ። ይህም የዘመኑ ምርጥ የምባል የታሪክ አሻራ ነዉ።አሻራዉ በታሪክነት ብቻ አልቀረም ዛሬም እየተሰራበት ነዉ።በርግጥ የወቅቱ መሪዎች ፖሊሲና ስትራቴጂ ባለመንደፋቸዉ አልፀፀትም ምክንያቱም እነሱ የዘመናቸዉ የስልጣነ ጫፍ ላይ ነበሩና። ኖህም በሰሜን ኢትዮጵያ በጣና ሐይቅ አካባቢ አራራት ተራራ ላይ ከዳግመ ፍጥረት በኋላ በርግብ ሰላይነት ያካባቢዉን ደህንነት አረጋግጦ በመጀመሪያነት ኢትዮጵያን በድጋሚ ረገጣት። ለልጆቹም በመርከቧ ዉስጥ የነበሩትን የእፅዋት ዘርና ጥንድ እንስሳት አከፋፈለላቸዉ። ሴምና ያፌት ወደምስራቅ ተሹመዉ በአምባሳደርነትና ባኗኗሪነት ተመደቡ። ዛሬ በምስራቃዊያንና በምዕራባዊያን ብቻ የምገኙ ብርቅዬ የምሏቸዉን እንስሳት እፅዋት ይዘዉ ተንከባከቡ( ለምሳሌ ፓንዳ፣ ካንጋሮ  ወዘተ)በሃገር ዉስጥም የቀረዉ ካም ለመላዉ አፍሪቃና ኢትዮጵያ ብሎ የለያቸዉን በራሱ ግዛት ስር አሰፈረ። ዋሊያ፣ ኒያላ፣ ጭላዳ ዝንጆሮ እና ለሌሎችንም 31 ጡት አጥቢ የዱር እንስሳት 24 አዕዋፋትና መሰሎችን በኢትዮጵያ ብቻ እንድሆኑ መራቸዉ።
ዋቢዬ ኖህ የቤተሰቡአለቃ ነዉ ይለኛል። በዝህ ሳይገደብ ካራት መቶ ዓመት በፊት የተገነባዉ የአፄ ፋስለደስ ህንፃም የኖህ መቃብር እንደሆነ አብራርቶልኛል።
የኢትዮጵያዊያን ጉልህ አስተዋፅዖ በዝህ አስተዋፅዖ ብቻም አልተገደበም እንደ አባይ ጅረት ከምፈሰዉ ታሪካችን በድሮፕለት እያንጥባጠብኩ የልጅነት ልምሻን የምከላከሉበት ባለሁለት ጠብታ የመቋቋሚያ መድሃንት መሰረት እነም ከነ ጋር እንድትቆዩ አደርጋለሁ።

ድንዛዘ በቸልታ
ቀንም ሌትም በመኝታ
ተክኖሎጂ በላይ በላይ
ሰዉ ከራሱ እንዳይተያይ
ድንዛዘ በቁሳቁስ
ደግሞ ፍቅር ወድቆ በሱስ
ድንዛዘ በጫጫታ
በግርግር በሁካታ
(xayouluma)

No comments: