Sunday, May 24, 2015

ከFIFA በቀሰምነው የጎል ቴክኖሎጂ ምርጫዉን ታዝበናል.........!!!






"ተዉ የጀማል አባት እንዳይቆጭዎት ምልክትዎን ንብ ላይ ብያደርጉ ይሻሎታል!"

"ቆንጂዬ ምንነካሽ! ስያዩሽ እንድህ አትመስይም አንቺም ክህደት ትፈፅምያለሽ?"

"ማዘር አንድ X ያድርጉ ንቡን ልቆራርጡት ነዉ ያሰቡት? ምነዉ እርሶ ትልቅ ሰዉ አይደሉም ? አንደት አንድ ንብ ላይ ሶስት X ያኖራሉ ?"


ኻዮሉማ/xayouluma

"ከፊፋ በቀሰምነዉ የጎል ቴክኖሎጂ ምርጫዉን ታዝበናል።"

"እኔም ኮኒስ ዉስጥ ሆኘ የመታዘብ ተልዕኮዬን ተወጥቻለሁ።"

ዛሬ በሰፈራችን ሀይለኛ ጉድ የተባለለት ግጥሚያ ተስተናግዷል።ቅልጥ ያሌ ጫወታ ነበር ከኛ ቡድን ግርግርበቃኝካሊሲዉኮከብዋ በረኛችን አመዷ እና የጠብቀዉ ወንድም ጮርነ ሁሉ ሳምንቱም ሙሉ ስዘጋጁበት ከርመዋል።ጮርነ ትንሽ ከኔ ጋር ፀበኛ ስለነበር እኔ በግጥሚያዉ እንዳልገባ ያደረገዉ ከፍተኝ ጥረት ተሳክቶለታል።ከላይ ሰፈር ልጆች ቺንዲላስላስ ጠንበለልንፉቲሲሬግንቤ(ስሙን ቀስ ይጥራዉና ባለፈዉ በነሱ ሜዳ ስንጫወት ባደረገዉ ኮንጎ ጫማ ቅልጥመን ብሎኛል፤ዛሬማ ብሰለፍ ኖሮ ጉዱን አሳያለሁ ብዬ የታላቅ ወንድሜን ቦቲ ጫማ አድርገ ነበር የመጣሁት።)ሆነዉ በመለያቸዉ ላይ ስማቸዉን ፀፌዉ የጋሽ ሀይሌ ሜዳ ላይ ተሰብስበዋል።በነገራችሁ ላይ የጋሽ ሀይሌ ሜዳ በኛ ሰፈር የኳስ ተንታኞች አሊያን ዛሪና የምል ቅፅል ተሰጥቶት ነበር እኛ ግን ብዙም ስላልተመቸን ሜዳዉን የጋሽ ሀይሌ ሜዳ ብለን እንጠራዋለን።በዝህ ታላቅ የሰፈራችን ደርቢ ብዙ ተመልካች ይገኝል ተብሎ ይጠበቃል።ብያንስ ከ 20-34 ሰዉ ጫዋታዉን ለማዬት ትኬት እንደቆረጠ የጫዋታዉ ትኬት ቆራጭ ሲስኮ ነግራናለች። የ'ኛ ደጋፊዎች ስለ'ኛ እየዘመሩ ነዉ እንደምታዉቁት የነ ግንቤ ቡድን ልጆች ሁሉ እረኞችና የመደበኛ ትምህርታቸዉን እንኳ ባግባቡ ያልተማሩና ያቋረጡ ናቸዉ፤የኛዎቹ ሁሉም ግን የ ፫ኛ ፬ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸዉ።

አመድ አምጥተን ሜዳዉን አስምረን በዉላችን መሰረት የጫዋታ ሜዳዉን ያሰመርነዉ ከጫዋታ ሜዳ ዉስጥና ከጫዋታ ሜዳ ዉጪ በምተገበሩ የመንደር አቀፍ ህጎች ተገዥ ለመሆን ተስማምተን ነዉ። ለኛ በረኛ ሁለት የተጫዋቾችን ልብሶች አዉልቀን ጎል ሰራን የነ ግንቤ ቡድን ተጫዋቾች ባለመስማማት ሹራባቸዉን አናወልቅም በማለት ሁለት ምን የምያካክል ድንጋዮችን ከጎንና ከጎናቸዉ አስቀምጠዉ ጨዋታ እንድጀመር ተስማማን።ይህ ጫወታ ግማሽ ፍፃሜ ነዉ፤የዝህ ጫወታ አሸናፊ ለዋንጫ ይቀርባል። ዳኛዋ የቺንዲ እህት መሽኛሽወርቅ ናት። መሽኛሽወርቅ ምንም የቺንዲ እህት ብትሆንም ለማንም አላዳላም በማለት ለሁሉም ተጫዋች እጃቸዉ ላይ መስቀል ሰርታ ምላለች።
ፊሽካ ነፋች፤ተጀመረ።

"መሽኛሽወርቅ ያሻማችዉ ኳስ በአለኝ እግር ስር ወደቀች ጠንበለልንና ካሊሲን ሸዉዶ ለጮርነ አቀበለ፤"

"ጮርነ የያዛትን ኳስ ጠለዘ። ኦ ያያያያ በረኛዉ ሲሬ ኳሷን በቀላሉ እንደ ቦንቦሊኖ ጎረሳት።"

"ሲሬ የመጀመሪያዉን ኳስ እየሸወደ ይዞት ሄደ  ሄደ ሄደ አዎ አለፈ አለፈ ሲረ ሲረ ሲረ አዎ ከጎልስር የያዛትን ኳስ ወደተቃራኒ ልያስገባ ነዉ አዎ አዎ ሲሬ ዎ ሲሬ የምገርም በረኝ ከጎል እስከጎል እየሸቃቀለ ይዟት የሄዳት ኳስ ኦ ኦ ኦ ተነጠቀ፤ ኳስ አሁን በበቃኝ እግር ስር አርፋለች።"

እያለ ኮሜንታተሩ ሙኒክ ስዘግብ ሁላችንም እየጮህን የመረጥነዉን ቡድን ደግፍን። ሙኒክ የምገርም ኮሜንታተር ነዉ ምን አስቸገራችሁ መሰ ቁጥር ፪ በሉት።

በዝህ ቀዉጥ በሆነ ጫወታ ከኛ ቡድን አመዷ ተሰብራ ወጣች። አመዷ ምርጥ በረኛችን ነበረች ከዕረፍት በፊት በ96ኛዉ ደቂቃ ላይ በደረሰባት የደረቅ ኮንጎ ጫማ ጥፊ ደም በደም ሆና ወጣች።የሰበራት ግንቤ ነዉ። ሁላችንም ሄደን ተሰብስበን ልንጠፈጥፈዉ ፈልገን ነበር ግን የግንቤ አያት ከሜዳዉ ጥግ ሆነዉ ስያዩን ፈርተን ተዉነዉ። ፈርተን ብንተወዉም ግንቤንና እናቱም እያያዝን አጫጭር ስድቦችን የኛ ደጋፊዎች አወረዱበት።በርግጥም የግንቤ እናት በይህወት የለችም ሆኖም ግን ዛሬ የሙት ዓመቷ መታሰቢያ ይመስል ስሟን እየጠሩ ከግራ በቀኝ ሁሉም የኛ ደጋፊዎች ሰደቧት።የኛ ቡድን በ፭ ተጫዋቾች የነሱ ደግሞ በ፮ ተጫዋቾች መጫወት ጀመሩ።ጫወታዉ ከመጀመሩ በፊት በአመዷ ቦታ እኔን ግባ ብሉኝም እኔ ተከላካይ እንጂ በረኛ አይደለሁም ብዬ ሙያየን አስከብረ ሳልገባ ቀረዉ።ያልገባሁበት እዉነተኝ ምክንያት ግን የግንቤ ኮንጎ ለሁለተኛ ጊዜ ከጠለዘኝ እንደሀይሌ ገ/ስላሰ ለመጨረሻ ጊዜ ከዉድድር ተሳትፎየ ልወጣ ነዉ በማለት ሰግቸ ቡድነን ዋሽች ራሰን አሳምኘ በግንቤ ጫማ ምክንያት መደገፍ መረጥኩ። በደ በል አንዴ የደመቀዉ ጫወታችን ተጫጭሷል።

ደ  በል አንዴ  ?
ደ !!
ደ  በል አንዴ ?
ደ!!
እነግንቤ ከጫካ ናቸዉ እንዴ?
እንደ!!!!!


ደ  በል አንዴ?
ደ!!
ደ  በል አንዴ?
ደ!!
የነኻዮሉማ ጉልበት ምላስ ነዉ እንደ?
እንደ!!!

ደ  በል አንዴ?
ደ!!!
ደ  በል አንዴ?
ደ!!!
ላስላስ በመግባባት አያምንም እንደ?
እንደ!!!!!!!

ደ  በል አንዴ?
ደ!!
ደ  በል አንዴ?
ደ!!
ብቃት ዉጪ ሆኖ ስያዩትና በሜዳ ስጫወቱ አንድ ነዉ እንደ?
እንደ!!!!!!!

እንድህና እንድህ የቀጠለዉ ግጥሚያችን በ110ኛዉ ደቂቃ ዕረፍት ብወጡም በሁለተኛዉ አጋማሽ ከ27 ደቂቃ በላይ አልተጫወቱም ። ያልተጫወትነዉ ምክንያት ግን በስምምነት ነበር። ጫወታዉም አንድ ላንድ ነበር የተጠናቀቀዉ።
እነግንቤ በጉልበታቸዉ እኛ ደግሞ በብቃታችን ተጫዉተን አቻ ብንወጣም ለዋንጫ የምያልፍዉ ቡድን ግን አልታወቀም። በፊፋ ህግ መሰረት ለዋንጫ ያለፈዉን ለመለየት ፍፁም ፍፁም አረመናዊ ቅጣት ምቾት እንድመቱ ተወሰነ። በምገርም ሁኔታ በጉዳት የመጣችዉ በረኛችን አመዷ ባልተጠበቀዉ ሁኔታ ስድስቱንም የግንቤን ኳሶች በማዳን ግንቤን አሳፍራ እኛን አኩርታለች።ዳሩ የኛ ተጫዋቾች በስድስቱም ጎል አላስቆጠሩም።የሆነዉ ሆኖ እኛ የአሸናፊነት ስሜት ተሰማን።በዛ ላይ የኔ ጠላት ግንቤ ስድስት ምቶቹን አመዷ እንደቦንቦሊኖ ስትጎርሳቸዉ የቀጠቀጡኩት ያህል ደስ አለኝ።
ኮሜንታተሩ ሙኒክ አሸናፊ ስላልተለየ በምርጫ እንድወሰን አድርጓል።ለሁሉም ተጫዋቾች ከጭንቀት የገላገለ ዉሳነ በኮሜንታተርነቱ አፀደቀ፤ዳኛዋም ተቀበለችና ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ሆነች።

ያዉ እንደምታዉቁት ያገራችን ፍትሐዊ ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅቱን ተጠናቋል። ቅስቀሳዉ የምርጫዉን ፍፁም ፍትሐዊነት አንፀባረቀ።ግንቤ አያቱንና ሌሎች ጓደኞቹን አሳመነ።እኛም ከነጮርነ ወንድም ጠብቀዉ ጋር ምርጫዉን የተቀላጠፈ አደረግነዉ።ኮሮጆ፣ካርድ፣ቀለም፣ምናምን አሟልተን ወድያዉኑ በደሞክራሲያዊ መንገድ ተረባረብን። ከመብራት ፖል ላይ የለቀምናቸዉን የንብ፣የዣንጥላ፣የአምስት ጣትና የ666ቶቹ ምልክት የሆነዉን የሶስት ለሁለት ጣት ምልክት አጭቀን አመጣንና ታዓማኒነቱን ለማረጋገጥ ታዛቢዎችን መደብን። ታዛቢዎቹ የምርጫ ኮሮጆዉን አፍጥጠዉ እንድያዩ ተስማማን።ይገርማችኋል ታዛቢም ተወዳዳሪም የሆኑት የነ ቺንዲ፣ላስላስ፣ንፉቲ ረሀብ እንዳንከራተተዉ ድሜት የምርጫ ኮሮጆዉን የተሰቀለ ቋንጣ መስሏቸዉ ቀኑን ሙሉ ተቁለጨለጩ።ታዲያ የነሱን አየሁና እኔም በ'ኛ ቡድን ለመታዘብ ፈልገ ዋና ምልክት የምደረግበት መጋረጃ ክፍል ከጣርያዉ ስር ገባሁና መታዘብ ጀመርኩ።እኔን ከጣርያዉ ስር ያስገባኝ ምርጫ አስፈፃሚዉ ኮሜንታተር ሙኒክና ዳኛዋ መሽኛሽወርቅ ናቸዉ።ምስጥር ነዉ እንዳታስወሩብኝ።

የምርጫ መታዘብ ስርዓቱ በፊፋ የጎል ተክኖሎጂ መሰረት ነዉ። እንደምታወቀዉ ፊፋ ላንድ ጎል አንድ የመሃል ዳኛ፣ ሁለት መስመር ዳኛ፣አንድ የጎል ዳኛ፣አንድ የማይዋሽ የጎል ቆጣሪ ሰዓት እና ሌሎች የተለመዱ ዳኞች አሉት።የምገርማችሁ ነገር ፊፋ ጎል ካስገባዉ ተጫዋች ይልቅ ጎል የምቆጥረዉ ሰዓቱን ነዉ የምያምነዉ።በዝህ መሰረት መስመር ላይ ነጥሮ የምመለስ ኳስ በፊፋ ህግ ገብቷል ማለት ነዉ።
ካስታወሳችሁት በፊፋ የጎል ህግ መሰረት ብንዳኝ የ97ቱ ምርጫ ኳሱ የጎል መስመሩን አልፎ ስለተመለሰ እንደጎል ይቆጠራል።ይህ ማለት የጫወታዉ አሸናፊ ቅንጅት ነበር ማለት ነዉ። ታዲያ ምን ያደርጋል ያነ የፊፋ የጎል ህግ ተግባራዊ ቴክኖሎጂ ስላልነበረ ኢህአዴግ ጫወታዉን አሸነፈ።

ዘንድሮ ግን ከፊፋ በቀሰምነዉ የጎል ቴክኖሎክጂ መሰረት ማንኛዉም ምርጫ እንታዘባለን።ታዲያ የኛ ምርጭ ስካሄድ እኔ ኮርኒስ ዉስጥ ሆኘ እታዘብ ነበር። ኮርኒስ ዉስጥ ተቀምጨ ማን እንደምጫወትና እንደማይጫወት ምን የገባ ኳስ እንዳመለጠዉ የማንስ እንደምመለስ ጭምር እከታተላለሁ።ለምሳሌ ለኛ ክለብ የተጣለ ድምፅ በስህተት ወደነ ግንቤ ራሱ ገብቶ ብመለስ ኮርኒስ ዉስጥ ሆኘ ማስጠንቀቂያ እሰጣለሁ። ምርጫዉ ተጀመረ። በመጀመሪያ ግንቤ ራሱ ገብቶ ካርድ ለራሳቸዉ ጣለና ወጣ።በመቀጠል ሲሬ ገባ።ሲሬ እንደገባ ወድያዉኑ ከኮርኒሱ ዉስጥ አፈር አፍሸ ባናቱ ወደታች ደፋዉበት፣ወደ ላይ ቀና ብሎ ስመለከት በምልክት ነገርኩት ሲሬም ለኛ ንብ ላይ ምልክት ስያደርግ ስመለከት ደስ አለኝ።እነሱ እንደወጡ የመሽኛሽወርቅ እህት በቀንጥ ለቺንዲ ቡድን ምልክት ስታደርግ አየውኃትና አፈር ባናቷ ላለብሳት አስበ

"ኧሬ የቺንዲ እህት ሙድ የለዉም።ምነዉ ቆንጆ አይደለሽም ስያዩሽ ግን ጎበዞችን የምታደንቂ ነዉ የመሰለኝ እንደት ወንድምሽ ብቻ ስለሆነ ለነሱ ትጥያለሽ እሱም ብሆን አሁን ከኛጋር ለመጫወት ተስማምቷል፤እንድህማ አትክጅንም።ቆንጅዬ ምን ነካሽ ስያዩሽ እንድህ አትመስይም አንቺም ክህደት ትፈፅማለሽ?"

ብዬ ፊተን በልብስ ደብቀ ስመክራት ወድያዉኑ የኛ ንብ ምልክት ላይ አስምራ XበX አድርጋ ወጣች።

በዝህ ብቃታችን በስስት ምርጫዉን በደቦክራሲያዊና ፍትሐዊ መልኩ አጠናቀቅን።ከዝያም አሸናፊዎቹ ባለንብ ምልክቶች እኛዉ ሆነን።በቃ ካርድ ለኛ ነጥሮ ወደ'ነሱ ስ ሄድ ኮርኒስ ዉስጥ ሆኘ እያስፈራራዉ ምርጫ በሰላም ተጠናቀቀ። እኛም ለዋንጫ እንዳለፍን በምርጫ ቦርዱ ሙኒክና መሽኛሽ ወርቅ ገለፁልን።

ከምንም ከምንም የምልረሳዉ የጀማል አባትን ነዉ።
በምልክት ማስፈራሪያዉ መጋረጃ ዉስጥ ስገቡ እሳቸዉ መምረጥ የፈለጉት ንፉቲን ነበር።ታድያ እንድህ አልኳቸዉ።

"ተዉ የጀማር አባት! በኋላ እንዳይቆጮት !ምልክትዎን ንብ ላይ ብያደርጉ ይሻሎታል! ዋ!"

ስላቸዉ አልበገረዉ የጀማል አባት እኛ በሰጠነዉ የይምረጡኝ መብት ማለቴ ደሞክራሲያዊ መብት እኛን አልመርጥም ብሉን በቆርቆሮዉ ያስገባሁት የኛ ቡድን ልጆች ሽንት ባናታቸዉ አዘቅዝቀ ደፋዉዉባቸዉ።ምንም ማድረግ አልችልም ይህ የድርጅታችን ተልዕኮ ነዉ። እኔም እንደቡድናችን አሰራር ሽንት ደፋዉባቸዉ።ከኋላ ቀዉጢ በቀዉጢ አድርገዉ ብቀዉጡ የምሰማቸዉ የለም። ኮርኒስ ዉስጥ ሰዉ የለም ብለዉ የምርጫ ቦርዶቹን ሙኒክና መሽኛሽወርቅ አፀደቁት።

ሌላኛዋ የገረመችኝ ቀልቃላ አሮጊት ጉድ ሰርታን ነበር።
እኔ ሁሌ መልክት የምላላክላት

"ለልጄ ኻዮሉማ/xayouluma ይሁንለት "

እያለች ገባችና አንድ የንብ ምልክት ላይ የጥላቻ የምመስል ሶስት XXX አኖረችበት።

"ማዘር ምንነካዎት? አንድ X ያድርጉበት ንቡን ልቆራርጡት ነዉ ያሰቡት? ምነዉ እርሶ ትልቅ ሰዉ አይደሉም ? እንደ እንደት አንድ ንብ ላይ ሶስት X ምልክት ያስቀምጣሉ?"

አልኳቸዉና ስያባርቅባቸዉ ወረቀቱን እንድቀይርላቸዉ ባቀረቡልኝ ጥያቀ መሰረት ወዲያዉኑ ለቅያር ከተቀመጠዉ ወረቀት አንስቸ ሰጠዋቸዉ።

በጠቅላላ ምርጭዉ በሃይል የተሞላ ተፅዕኖ አደረግን እንጂ ምርጫዉ ደሞክራሲያዊ ነዉ።
በመጠኑ የድምፅ ስርቆት አደረግን እንጂ ምርጫዉ እጅግ ታዓማኒ ነዉ።
ምልክት ማድረግ ለማይችሉት ታዛቢዎቻችን ንብ ላይ አደረጉበት እንጂ የኛ ምርጫ ፍፁም ፍትሐዊ ነዉ።
መራጮቹን ለመወገር ድንጋይ የሰፈር ልጆችን አስይዘን ቆምን እንጂ በሰላም ነዉ ያጠናቀቅነዉ።

እኔ ኻዮሉማ/xayouluma በተመደብኩበት የኮርኒስ ዉስጥ ታዛቢነቴ በአግባቡ ሀገሬን አገልግያለሁ ማለቴ ቡድነን አገልግያለዉ።
ይሄዉ ከFIFA በቀሰምነዉ የጎል ቴክኖሎጂ ምርጫዉን ታዝበናል።

ኻዮሉማ/xayouluma
ግንቦት 16 ልመሽ ስል የፃፍኩት 2007

No comments: