Thursday, May 14, 2015

ስገባኝ

 ልጥፍ/ገፅ ፩

xayouluma

ጊዜ በዘመን ባለስትራነት ላይ የተገጠመ ተሽከርካሪ ጎማ ነዉ።የሰከንድ ስነ ተዋልዶ ዑደት በተገቢዉ መጥን እየተፀነሰ ከምጠበቀዉ በላይ እየተራባ ደቂቃ ሰዓት ቀን እያለ የልጅ ልጆችን እየተተካ የዘመን የዘር መነሻ ሆኖ ያገለግላል። ተሽከርካሪ ጎማ የምድርን ህዋስ ከቀኝ በግራ ከፊት በኋላ እያዋዛ ዛረ ላይ የምድርን ልብ በመቆጣጠር የደም ዝዉዉሯን ተቆጣጥሮ ሰንበት ብሏል።የዝህችኛዋንና የምትመጣዋን ዓለም የደም ዝዉዉር የምመራዉ በጊዘ ተሽከርካሪነት ላይ በመነጨ ጎማዊ ደም መሆኑ ሳይታመን ያለጥርጥር የምንቀበለዉ የመካኒክና የስነ ህይወት ፈለግ ነዉ።
ከዝህ ተሽከርካሪ ቅፅበት( ሰከንድ)በዘመን ላይ የምያኖረዉ ታርካዊ አሻራ በየዕለቱ እየተመዘገበ በፈጣሪ ቤቴ መዛግብት በመረጃ ደስክ መላዕክት እንደምቀመጥ አያጠራጥርም የፅህፈት አሰፋፈሩ በሁለት መልኩ ነዉ የመጀመሪያዉ ፈጣሪ በዝህች ምድር የምያከናወነዉ ሁሉ ሰማይና ምድር ከመፈጠሩ በፊት የተፃፈና ሁሉ በርሱ እንደምሆን በመፅሀፍ ቅዱስ አስፍሮልናል ሁለተኛዉ አሰራር እግዝአብሔር ከፈቀደላቸዉ መንገድ ዉጪ እንደ ራሳቸዉ ፍላጎት የምኖሩትን ፍጥረታት ያኗኗር ዑደት በማስተዋል በሁለት መንገድ ባንድ መዝገብ ይመዘግባል። የምናነሳዉ ዋናዉ ነጥብ በዝህ ግዙፍ ዓለም የእያንዳንዱ ፍጥረት እንቅስቃሴና ትግበራ ካለን ጊዜ አንፃር ስንመለከት ዓለም ከጊዜዉ ጋር ባንድ ፍጥነት ለመገስገስ ተስኗታል። የኛም ምድር ካሉን ተቀሪ ሳይንሳዊ ዓለማት አንፃር ስስተያይ በተሻለ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች ብሎ መገመት በህግና በህሊና አያስጠይቅም። በነዝ ህ ሰባቱ አህጉራት አሁን ከምንፀባረቁ አዕምሮአዊ ምጥቀት በተጨማሪ በየወቅቱ የምጎበኙን አስደናቂና አሳቃቂ የተፈጥሮ አደጋዎቹም አይዘነጋም።አይስተዋሉምም። ጉዱ ግን ማን ነው ጊዘን ባግባቡ እየተጥቀመ ያለዉ ብለን ሰዉን መጠየቅ አለብን።

"አልበዛም ወይ  መፋዘዙ ነቃ በሉ
አልበዛም ወይ  ማንቀላፋት
ሀላፊነትን መዘንጋት
አልበዛም ወይ ግድ ማጣት
ሀላፊነትን መዘንጋት .........."


ሳስነብባችሁ በሙዚቃ ዜና ፈታ እንድትሉልኝ የዘሪቱን  አርተፊሻል እያቀነቀንኩላችሁ ስለዝህ ዘመን ያለንን እዉቀት እንከፋፈል።

ባንድ ደቂቃ የተደረደሩት ስድሳ የምያህሉ ቅፅበቶች የያንዳንዱ ፍጥረት ታሪክ ይጨምራል፣ ታሪክ ይቀንሳል።ጨመረም ቀነሰም መቀየሩ ግን ግድ ነዉ። እኛስ በምን ያህል ፍጥነትታሪክ እየቀነስን አልያም እየጨመርን እንደሆነ ምላሻችን ለየቅል ነዉ የሆነዉ ሆኖ ከሁለቱ አንዱ መሆኑ ግድ ነዉ።
ወደ ኋላ  መለስ ብለን ባላቸዉ የኮንትራት ዘመን ኢትዮጵያዊያን ለሀገራ ያበረከቱት ጉልህ አስተዋፅዖ እንመልከት።

"ኖህ ከነ ቤተሰቦቹ በመትረፉ ተደስቶ ለፈጣሪዉ መስዋዕትን አቀረበ። ፈጣሪም በኖህ መስዋዕት ተደስቶ ላዳምና ለሄዋን የነሳቸዉን ምድር እንድወርስ ወደደ። 'የሰዉንም ልጅን ከእንግድህ በዉሀ አላጠፋም'  የሚል ቃል ኪዳኑን ገብቶ ለቃሉ ማረጋገጫ በደመና ቀስቱን አኑሮ በማመላከት ወደ ግዮን መነሻ አበሜሌክ  ማለትም ጣና ሃይቅ አዳምና ሄዋን ባጠፋፉት ጥፋት ተባረዉ ኢየሩሳለም ቀድም ብሎ ይኖሩባት እንደነበር በሚታመነዉ ቦታ እንድሄድ አዘዘዉ። ኖህም ሴም ሴምንና ያፈትን ትቶ ካምን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ(አፍሪቃ) መጣ።"

ብሎ ያሬድ ግርማ ሃይሌ  የጎንደር ታሪክ  በምል ርዕስ 1999 ዓ/ም ያሳተመዉን በማጣቀስ አንድ አርብ ሌት ለቅሶ ስ ሄድ በመንገድ በተነጠፈ የመፅሀፍት መሸጫ የገዛሁት የጋዘጠኛ ፍሰሐ ያዜ ካሳ  "የኢትዮጵያ ፭ ሺ ዓመት ታሪክ ከኖህ እስከ ኢህአዴግ መፅሀፍ ፩ " በተሰኘዉ በገፅ 21-22  ላይ አስፍሯል።

የዘሪቱ ሙዚቃ ድንዛዜ የምለዉ ፈሊጥ ያንን ወቅት ያካለለና ለጥንት ኢትዮጵያዊያን ባለታሪክ የምጋበዝ ባይሆንም እነ ግን ስፅፍ እያደመጥኩት ስለነበር እናንተም በየመሃሉ እያስነበብኳችሁ ጭሬትን ልቀጥል...............?

No comments: