Wednesday, May 20, 2015

የሰማያዊ ነገር


ልጅ ሆኘ ህፃን ሳለሁ የዓመት በዓል በመጣ ቁጥር ካባቴ ጋር ሙግት ገጥማለሁ። የሙግቴ መነሻ የኔ ምርጫና ያባቴ ምርጫ ነበር። አባቴ በተፈጥሮዉ ድያብሎስ ስመርቀዉ የኔን ምርጫ ይጠላል። በየእንቁጣጣሹ ሰማያዊ ፋንት በ፲ ብር፣ሰማያዊ ካልሲ በ ፲ብር፣ ሰማያዊ ጫማ በ፶ ብር፣ ሰማያዊ ሱሪ 45 ብር ፣ ሰማያዊ ሸሚዝ በ37 ብር ፣ ሰማያዊ መነፅር በ 12 ብር፣ ሰማያዊ ኮፊያ በ22 ብር፣ ሰማያዊ ሻማ በ ፶ ሳንቲም፣ ሰማያዊ ፊኛ እና ት/ቤት ስሄድ ከፀሃይና ከሰቆቃ የምታደገኝን ሰማያዊ ዣንጥላ በ17 ብር ይገዛልኝ ነበር።

ጥሎበት ያባቴ ምርጫ ሰማያዊ ባይሆንም ከብጫና መሰሎቹ ይሻለኛል ብየ ነበር የምያለቅሰዉ። አድገም ት/ት ስጀምር በት/ቤት ዉስጥ ከሰማያዊ እስክሪብቶ ሌላ ተጠቅሜ አላዉቅም።መምህራችን

"ኻዮሉማ/xayouluma ላንዳንድ ጠቃሚ ማስታወሻዎች ቀይ እስክሪብቶ ተጠቅም "

ብለኝም እኔም እንደ ሪዮት ዓለም ቀይ እስክሪብቶ ፈራለሁ።

ይሄዉ አድጌ በፍቅረኞች ቀን እንኳን ለፍቅረኛዬ ሰማያዊ ፋንትና ጡት ማነቂያ ነበር የገዛሁላት። ምን ላግርግ ትሉኛላችሁ DSTV ስገባ ባለሰማያዊ ባንድራዎቹን ቸልሲን ነዉ የምደግፈዉ ወደሃገር በት ስመለስ ፕሪሜሪሊግ ባለሰማያዊዉን ዴደቢትን ነዉ የምያደንቀዉ። ፈጣሪዬ የምን ልክፍት ነዉ ብዬ ወደላይ ብያንጋጥጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ በሰማይ ዙፋኑ ላይ ሰማያዊ ሱፍና አክሊል ደፍቶ አየሁት። እንዴ ምን ዓይነት ፍርጃ ነዉ ብዬ ዘወር እንዳልኩ እናንተ ጓደኞቸን ስፈልጋችሁ በፌስቡክ/www.facebook.com ሳሻኝ በሊንክድ ኢን/www.Linkid In.com ካስጠላኝ በቲዊተር/www.twitter.com ሳገኝችሁ ሰላማዊ  ግኑኝነተን በባለ ሰማያዊ አርማዎቹ አካዉንቶቼ አገኛችኋለሁ።
ታዲያ ይሄ ሰማያዊ ተብዬዉ ቀለም የለከፈኝ ስልባቦት እመስል ሰማያዊ ነገር ባይሁ ቁጥር ሰላም ይሰማኛል፤ ልቤ ጮቤ ይረግጣል። እላችሁ ሰሞኑን የደረሰበት ማግለል ግርም ብሎኛል። እኔ'ኮ ሰማያዊን መምረጥ ከጀመርኩ ድፍን 22 ዓመት አለፈኝ። አንዳንድ Bluephobia (አላርጅከ ዘሰማያዊ )ያለባቸዉ አክራሪ ፖለቲከኞች በከንቱ ልፍለፋና በከንቱ ዉዳሴ አቅለን ያጠፋሉ።
ገዥዉ ፓርቲም ለዝህ ምላሽ ለመስጠት ከዝህ ቀደም ሰማያዊ ቀለም የተቀቡትን የመንግስት ተሽከርካሪዎችን ስራ እንድያቆሙ እየተንደረደረ ነወ አሉ። ታድያ ዉሳነዉ ከፀና በመላዉ ኢትዮጵያ የነገሱት ሰማያዊ ባጃጆች፣ሰማያዊ ሚኒባሶች፣በያዝነዉ ዓመት የተገዙት ያድሳባ ህዝባዊ ትራንስፖርት አገልጋይ ባሶች(ባለ ሰማያዊ ቀለሞቹ) እና ሌሎች ባንደ ስራ ያቆሙ ይሆናል። ለዝህም ነበር አሉ አዲሱ ባቡር ሰማያዊ ልቀባ ስል ታማኙና ንፁሁ ፓርቲ ያስከለከለዉ።
ድሮ ድሮ በየስብሰባዉ ሰማያዊ አምባሳደር፣ሸሚዝና ከራቫት የምያዘወትሩ ካድሬዎቻችን በሙሉ ልብሱን ከጭፍን ጥላቻ የተነሳ በኢህአዴግ አስገዳጅነት አዉልቀዉታል። ኧረ ምን ይሄ ብቻ ሰማያዊ ትሸርት የለበሱትንም ደብድቧል አሉ።
ይግረማችሁ አሁን የመጀመሪያ ዴቦክራሲያዊ መብቴን በመጠቀም ልመርጥም አይደል?
አዎ ልመርጥ ነዉ!!

የተማርኩት በሰማያዊ ብዕር!
ያደግኩት በሰማያዊ ሚኒባስና ባጃጅ እየተመላለስኩ!
ቁርስ የበላሁት በሰማያዊ ማቅረብያ!
በምርጫዉ ዕለት ያዉራ ጣቴን በሰማያዊ ጅቢ አይደል የምቀባዉ!
ክረምት በጋ ስመጣ የምጠለልበት




ዣንጥላ ነዉ ምርጫዬ!!!!!
http://semayawiparty.org/

ኻዮሉማ/xayouluma

No comments: