Wednesday, May 13, 2015

እጠጣዋለሁመጠጥን ጎጅ ነዉ አትበሉኝ
መረነ ቢስ ምክራችሁን በከንቱ አትለግሱኝ
ጠጥቸ ነዉ ሁሉን የረሳሁት
ጨልጨ ነዉ መከራዬን ያለፍኩት
ባልጠጣ ኖሮ የትናንቱን ረሃብ እንዴት እረሳለሁ?
የዛሬንስ ጥጋብ በምን አከስማለሁ?

አልኮል ነዉ አትበሉኝ
መርዝ ነው አትበሉኝ
ገዳይ ነዉ አትበሉኝ

ጠዋት ማታ ባልጠጣ እንደት እኖራለሁ
እሷን ባልጨጣት በምን እከርማለሁ


መልክ ታጥቦ አይጠጣም
 ለምትል ድንፋታም
መልኳን አጥበህ አምጣልኝ
ከመራራ ኑሮ እጣቢዋ ነዉ የምሻለኝ

እያልኩ የፎከርኩት
በብዕር የገጠምኩት
ሆድየ ላንች ነዉ
ከጸሐይ ፸ ዕጥፍ በላይ ለደመቀዉ
የመላዕክትን ሁሉ ዉበታቸዉን ላስናቀዉ

ያ ያንቺ መልክ  ጨልጨ ጠጣለሁ
አጥበዉ ጨምቀዉ ጠዋት ማታ ጠጣለሁ
በጠጣሁት መልክሽ ዘላለም ኖራለሁ
አጥበዉሽ ያምጡልኝ አሁንም ጠጣለሁ።

ማክሰኞ ግንቦት ፬ 2007

ኻዮሉማ/xayouluma/xamnxallee

No comments: