በደቡብ ምስራቅ አዲሳባ ስሟን በማልጠራት ብጠራትም እንኳን ማንም በማያዉቃት አንዲት በማደግ ላይ ያለች ሃገር አለች።ሀገሪቷ ከቅርብ ጊዜ ወድህ ባለሁለት አሃዝ እድገት ማስመዝገቧን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተሰሚነት ክፍ እያለ እየመጣላት እንደሆነ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ይናገራሉ።ሃገርቷ በመልካም አስተዳደርና በደሞክራሲ መሰረት ላይ ከነ አሜሪካና አዉሮጳ ሀገሮችም ጋር ስነፃፀር የተሻለ አፈፃፀም ታይቶባታል።ይህች በመልክዓ ምድር ያነሰች በዓለም ላይ የገዘፈች ሀገር አብዛኛው የሀገሪቷ ህዝብ የገቢ ምንጩ ወሬ በማዉራትና በማስወራት ላይ የተመሰረተ ነዉ። በዳታ ስሰላ 60 ከመቶ የአጠቃላይ ገቢዋ የምገኘዉ ወደ ዉጪ በምትልከዉ ወሬ ላይ ነዉ። የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ኻዮሉማ/xayouluma እንደምናገሩት ከሆነ የህዝቧ ወሬኛነትና ከመቸዉም ጊዜ በላይ ስላደገ ፈጣኑን የኢንፎርሜሽን መረብ በመዘርጋት ካለም አንደኛ ነች። ሀገሪቷ በተለያዩ ወሬ ብቻ በምያዘዋዉሩ ወሬኞች ብዛትም ካለም አንደኝ ነች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በአፍሪቃ አህጉርና በሌሎች ዓለማት በምገኙ መንግስታት ስር ብዙ ወሬ አቀባይ ዜጋዎቿን በማስቀጠር ካለም አንደኝ ነች።በየፖለቲካ ፓርቲዉ ፣ በየሀይማኖት ድርጅቱ፣ በየንግድ ማህበራቱ፣ በየሙያ ማህበራቱና በየመደቡ የተሰገሰጉት የዝህች አገር ነዋሪዎች በሰባቱም አህጉር በመበተን ወሬ በማፈትለክ ስራ ተጠበዋል።አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገሪቷ ለስራ ቦታ የለላት ሀገር ብሏትም እሷ ግን ገቢዋን አጠናክራ ጉዞዋን ቀጥላለች።በሌላ ሀገር ያሉ ዜጎቿ የሀገሪቱን መሪዎች አቋሜ ቢስ ብሉም እነሱም ካንዳንድ የፖለቲካ ካባዎች ስሞቁ ተስተዉሏል።
በዝህች ሀገር ነፃ ፍትሐዊ፣ወቅታዊና ታዓማንነት ያለዉ ምርጫ በየጊዘዉ ይደረጋል። ሀገሪቷ በምርጫ ላይ ባላት ተዓማንነት እነሂዉማንስ ርይት ዎች የመሳሰሉ ቀንደኛ ድርጅቶች ሁሉ ያምኗታል። እንደዉ አንደ በሆነ የፈረንጆች ዓመት ላይ 'ለምን የአሜሪካን ምርጫ አልታዘብም ?'ብላ ጠይቃም ነበር አሉ። የካርድ ቆጠራዉ በሙሉ በፕሬዝዳንቱ ምሪትና ምራቅ ስለምካሄድ የገዘፈ ታዓማንነት አግኝታለች። ታድያ በዝህ በያዝነዉ ዓመት ግን ከተለመደዉ ዉጪ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የምርጭ ማጭበርበር ክስተት ገጥሟታል። ምርጫዉ የተጭበረበረዉ ሆድ በተባለዉ ብሔራዊ ክልሏ ስሆን ክስተቱም እንድህ ነበር።
በሆድ ብሔራዊ ክልል ጨጓራ በተባለ ምርጭ ክልልና ጉሮሮ በተባለ የምርጫ ክልል የተወዳደሩ ዕጩዎች ነበሩ።
ዕጩዎቹ
የፓርቲዉ ስም ምልክት
ሽሮ ዝንብ
ጎመን በስጋ አረንጓደ ቅጠል
በርገር ሹካ
ፒዛ ሁለት ጣት
ፎሰሰ አምስት ጣት
በምርጭ ክልል ጨጓራ የተመዘገቡ ስሆን የምርጫ ክልል ጉሮሮ የተመዘገቡት ሶስት ናቸዉ። እነሱም
የፓርቲዉ ስም ምልክት
ፓስታ ጦርና ጋሻ
ቮድካ አበባ
ቦርደ ማጭድ ናቸዉ።
ግንቦት 16 2007 ላይ ለምካሄደዉ ምርጫ ከፍተኛ ምላስና የፈጣሪን ሀይል ይዘዋል። በሀገሪቱ የፉርኖ ዳቦን ለብዙ ዓመታት በመታገል ስልጣን ያስለቀቀዉ ባለዝንብ ምልክቱ ሽሮ ሳሻዉ ደሞክራሲ መብት ስጥቻችኋለሁ ይልና ስደብረዉ ጠብመንጃ ታጥቃችሁ ጨጓራ ገብታችሁ ታገሉ ይላቸዋል።
"ጎመን በስጋ የአብዛኛዉን የሆድ ጥያቀ አይመልስም ሁሉም የሀገሪቱ ሰዉ አይመገበዉም ስለዝህ የሙስሊሙ ምግብ ስለሆነ በሆዳችን ላይ የበላይነት ልሰጠዉ አይገባም ይህ ከሆነ በሁላችንም ሆድ ዉስጥ አሜባና ተዛማች በሽታዎችን ስለምጥል ባትመርጡት መልካም ነዉ። ፎሰሰም ብሆን ለሃገራችን ተጨንቆ ሳይሆን በተወሰኑ አከባቢ ላይ ብቻ ያተኮረ ረሀብ ተኮር ፓርቲ ነዉ።በርግጥ በአምስት ጣት ፎሰሰ መብላት አስፈላጊ ቢሆንም ለመመገብ ከበድ ይላል። በተጨማሪም በበቆሎና በቆሎ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነዉ። በርገርና ፒዛ መመገብ ሌሎች ሆዳችን የማይችላቸዉ ተጨማሪ ምግቦችን ይጠይቁናል፤ ይህ ማለት ደግሞ ለአላስፈላጊ ወጪ እንዳረጋለን ስለዝህ በሹካ መመገብ ባህላችን ባይሆንም በሁለት ጣት የምንመገብበት የቀንጥ አመጋገብ ኢኮኖሚ ስለሌለን ፓርቲዎች በአጠቃላይ በዉጪዉ ዓለም ላይ ጥገኝ ያደርጉናል። ፓስታ ፓርቲም በጉሮሮ አከባቢ እየተንዘላዘለ ብወርድ የ፫ ሺ ዓመት ታሪክ ያላትን ሃገራችን ዛሬዉኑ ለዉጠናት ፓስታ እናብላት ማለት ከዝህ ቀደም ስንመገብ የነበረዉን ስራስርና አታክልት ማናናቅና ያለፈዉን አለማመስገን ስለምሆንብንና ስለሆነብን ለዉድ ድሩ ብቁ የሆነ የአሳተሳሰብ ብቃት የላቸዉም ብለን እናምናለን። ቮድካና ቦርዴ አይደለም ሃገር ልመሩ ራሳቸዉን በወጉ ልያደራጁ አልቻሉም። ለነዝህ መጠጦች ሀገራችንን ብናስረክባቸዉ የህዳሴዉን ዳቦና ሌማት ከነ መሶቡ ያፈራርሱታል።"
እያለ ባለዝንብ ምልክቱ ሽሮ ፓርቲ በቴሌቭዥን ፣ በሬድዮ፣ በቪድዮ፣ በጋዘጣ ፣ በገበጣ፣ በፌስቡክና በፌስ ቀዳዳ ሁሉ ቱልቱላዉን ነፋ፤አስነፋ።
በከፍተኛ ፍጥነት ከተመሰረተ ፭ ዓመት ያማይሞላዉ ወጣቱ ፓርቲ እንደጎመን በስጋነቱ የገዥዉን ሽሮ ፓርቲ ፖለቲካ ትችት ወደ ጎን በመተዉ ህብረተሰቡን መቀስቀሱ አላቋረጠም ነበር።
"እኛ'ኮ ጎመን በስጋዎች ሆዳችን ለምን አዘዉትሮ ሽሮ ብቻ ይበላል ? በርገር፣ ፒዛ፣ ፎሰሰ፣ ፓስታና ሌሎችንም መመገብ አለብን ብለን እናምናለን።ሁሉም የሃገራችን ሰዉ ሽሮ ብቻ መብላት ሰልችቶታል፤ በቅቶታልም፤አቅለስልሶታል ስለዝህ የሀገሬ ሰዉ ሆይ እንደከዝክ ቀደሙ ቀይ ወጥ፣ጥብስ፣ዱለት፣ምንቸት የማንበላዉ ለምንድን ነዉ?
እነሱ ብሔር ቶከር አመጋገብ ብቻ ይዘዉ ለምን ይንቁኑናል፤ ጨጨብሳ፣ ጩኮ፣
ቡርሳሜ፣ ሙሳብኽና ሌሎችን ለምን አንመገብም። በ፩ ጎሳ ላይ የተመሰረተዉ የሽሮ ፓርቲ ስርዓት ያዉ በአተርና በባቄላ ብሔረሰብ ነዉ የምመራዉ። ሽሮ፣ ሽሮ ፈሰስ፣ተጋቢኖ፣ ቡዘና፣ምስር ወጥና ሌሎች የምንመገባቸዉ በሙሉ ያተርና የባቄላ ብሔር አባላት ናቸዉ። ከዝህ በኋላ ሀገራችን የተለያዩ ምግቦችን አማርጣ መመገብ አለባት። ስለዝህ በኻዮሉማ/xayouluma የምመራዉ የሽሮ ፓርቲ ስልጣኑን መልቀቅ አለበት።"
በምል ቁጭት ለምርጫ ይሰናዳሉ። ታዲያ ብልሀተኛዉ ሽሮ ፓርቲ፣በምርጫ ቅስቀሳዉ ሰሞን ሁሉም ሌሎች ምግቦች ላይ ዝንብ እየላከ የሆድን አፕታይት ይዘጋል። ለምርጭዉ ፩ ቀን ስቀረዉ ቦርዴ እና ቮድካ ፓርቲን በአንድነት አጣምሮ ወደ ሆድ ይከታቸዋል። ትኩረት ያለገኘዉም ፎሰሰንም በላያቸዉ ላይ ይጨምራል።በዝህ አጋጣሚ ሆድ ዉስጥ የምኖሩ ህዝቦች በነዝህ ፓርቲዎች በመስከርና ቁንጣን በቁንጣን በመሆን
"ከማናዉቀዉ መላክ የምናቀዉ ሰይጣን ይሻላል "በማለት ዝም አሉ።
ተስፋ ያልቆረጠዉ ጎመን በስጋ ፓርቲም ዕጩዎቹ በሙሉ በዝንብ ብበከሉም የተረፉትን 139 ዕጩዎችን በመያዝ ለዉድድር ይቀርባል።
አወዳዳሪዉና ተወዳዳሪዉ የሽሮ ፓርቲ በታዛቢነትና በተወዳዳሪነት ላይ በመቀመጥ ካርድ የምጥለዉን ህዝብ በመገላመጥ ከጎመን በስጋ ፓርቲ የተወሰኑ ድምፆችን በመስረቅ ለ፭ ጊዜ የ አሸናፊነት እወጃዉን በጉሮሮ አማካይነት ይናገራል።
በዝህ መሰረስ የኻዮሉማ/xayouluma ሽሮ ፓርቲ በማሸነፍ ሀገሪቱን በሙሉ በዝንብ ያስወርራል።
ባለ አረንጓዴ ምልክቱ ፓርቲም ምርጭዉ እንደተጭበረበረ እሮሮዉን ለጉሮሮ ማድረስ ጀምሯል።
ኻዮሉማ/xayouluma
No comments:
Post a Comment