"ለብሔራዊ ደህንነት ስባል መራጩ የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ እስክያልፍና ዉጠቱ እስክነገር ቡና እንዳይጠጣ።"
ኢፌዴሪ መንግስት
"አንዳንድ አልቧልተኞች ባልተፈቀደላቸዉ ቡና ቤቶች የሽብር ወሬን ስለምነዙና ሰላማዊዉን ህዝብ ስለምያሸብሩ የመንግስት ዉሳኔ ፓርቲያችን ተገቢ ነዉ ስል አምኖ በመቀበል እንደፓርቲ ተግብሯል።"
የኢህአዴግ አፌ ቀላጠ ሬድዋን ሁሴን
"መንግስት በህብረተሰቡ ላይ እያደረገ ያለዉ አምባገነናዊ ተፅዕኖ ፫ ሺ ዓመት ቡና የመጠጣት ባህላችን አያስቀረዉም።"
ኢንዢነር ይልቃል ጌትነት
"ኢህአዴግ ሰፊዉ ህዝብ ስለምርጫ መረጃ እንዳይለዋወጥ የወሰደዉ እርምጃ አግባብነት የጎደለዉ ቢሆንም የመንግስትን ዉሳኔ እንደፓርቲ በፀጋ ተቀብለናል።"
የቅንዥቱ አየለ ጫሚሶ
"ወያኔ አፋኝ ስርዓቱን ስር በሰደደ ህዝባዊ ጥላቻ ላይ በማድረግ በነፃነት የመናገር፣የመወያየትና ጎረበት ጠራርቶ ቡና የመጠጣትና የማማት ሰብዓዊ መብቱን የምጥሰዉን ልያቆም ይገባል።"
የጉንቦት ፯ቱ ነጋ ብርሃኑ
"የኦሮሞ ህዝብና ሌላዉ የሃገርቱ ህዝብ ቡና ከጂማ ከተገኘበት ጊዘ ጀምሮ 'kotta buna dhuuge 'እየተባባለ ዛሬ የደረሰበትን ቡና በዘመናዊ መልክ የማፍላትና የመጠጣት መብቱ ለቦለቲካ ግብዓትነት በማሰብ ማቆም የለበትም።"
ዶር መራራ ጉዲና( ገነትን ያለማዕረገ አትጥርኝ ነበር ያላት)
ይህ ከላይ የተዘረዘረዉ የአንዳንድ መንግስቶችና ፓርቲዎች አቋም ለሰፊዉ ህዝብ ያስፈልጉታል የተባሉት አማራጮች ናቸዉ። ይህ አዋጅ ከግንቦት ፯ እስከ ሰኔ ፴ የምተገበር ጊዛዊ የቡና አለመጠጣትና አላማጠጣት ረቂቅ አዋጅ ነዉ።ይህ መረጃ ከታማኝ ምንጮች የማይገኝ ተራ መረጃ ነዉ።ዳሩ ግን የእያንዳንዱን ፓርቲ አቋም ፊንቲዉ አድርጎ ያንፀባርቃል የምል እምነት አለኝ። በ አሁኑ ሰዓት ዳጉን የመሰለ አንጋፋ የአፋር መረጃ መለዋወጫ ዜደ ባለባት ሃገር ከ፪ኛ እስከ ፬ኛ ትዉልድ ያለዉን የመረጃ መረብ መዝጋት ምን ይሉት ፉክክር ነዉ።ዜጋዉ ሃሳቡን እንዳያንሸራሽር ማድረግ የጭንቅላት መቅላት ስርዓት ያንገት መቀላት ስርዓት ጋር እኩል ነዉ የምመለከተዉ።ተፎካካሪዎቹ ከፍርሀታቸዉ የተነሳ ይሄዉ የት ምን እየሰሩ እንደሆነ ከህዝብ ጆሮና ዓይን ከተሰወሩ ቀናት አለፉ። የሁለትና ከዝያ በላይ ዘግነት ያላቸዉ ደሃስፖራዎች በፈጠሩት ጫና መንግስታችን ከ1G በቀጥታ 4Gየተባለ የወሬ ቴክኖሎጂ ላይ ደርሷል። ሆኖም ነባሩ የኢትዮጵያ ህዝብ እስከዛሬ ድረስ 1G(የመጀመሪያዉ ትዉልድ) የወሬ ቴክኖሎጂ ላይ ዘጭ ብሎ ነዉ የምኖረዉ።ይገርማችኋል ባለ፬ኛ ትዉልዱ የወሬ ቴክኖሎጅ በዉስን ሰዎች ካርድ ላይ ብቻ የምሰራዉ ብታምኑም ደጋግማችሁ ብታምኑም 90 ሚሊየን የሃገረ ህዝብ አሁንም የወሬ ፈጠራ ላይ ነዉ። መንግስት ግን ወደ ፴ ሚሊየን ኢትዮጵያ የ2G ( የሁለተኛ ትዉልድ) የወሬ ቴክኖሎጅ ተጠቃሚ ነዉ ብልም አብዛኛዉ ህብረተሰብ መንግስትን ዉሸት !!!! እያለ በአፉ ላይ ማድረግ ከጀመረ ይሀዉ የኢሳት ቴሌቭዥን ሁለተ ተዘግቶ ተከፈተ።
በሁሉም የሃገራችን ከተሞች የወሬ መግላሊቶች እንደመስቀል ደመራ ቆመዉ ከተገተሩት ዛሬ ሁለተኛ የምርጫ ዘመን መጣላቸዉ። ባለ 65 ሜትሮቹ የወሬ መስቀያ ቆጦች በየቀበሌዉ ተገትረዉ ካናታቸዉ ላይ ቦግ ብልጭ የምትል ቀይ መብራት ማብራት ከጀመሩ ስንት ቀን እንዳለፈዉ ቆጥራችሁ ድረሱ።
የሙከራ ስራ ከጀመሩ ዓመት ያልሞላቸዉ 3G እና 4G በናንተ አገላለፅ 3ጂብ ና 4ጂል የእዉነቱን ከሰዉ ጂብ በተጨማሪ የገንዘብ ጂብ እንደተለቀቀብን አንዳንድ የማህበረሰብ ሳይንስ ተንታኞች በ1G ገልፀዉልናል።
እናቶቻችንና ታላላቆቻችን በአንድነት ተሰብስበዉ አብረዉ የምወያዩበት ወሬ የምቀያየሩበትና የምበዳደሩበት የመጀመሪያዉ ትዉልድ ማለት የ1G የወሬ ስልጣነ 'ኑ ቡና ጠጡ !!' በምለዉ የነፃ መስመር በመጠቀም ላለፉ ፫ሺ ዓመታት መረጃ ስቀያየሩ መቆየታቸዉን የማያዉቅ የለም።
ታዲያ ከዝህ ቀደም ስዋርድ ስዋረድ የመጣነዉን ወሬ ባህላችን ዛሬ በአጋጣሚ በተወሰኑ የምርጫ ተሳታፊ ወላጆችና ቤተሰቦች ፍላጎት ይሄዉ በነፃነት እንዳንጠቀም የምከለክል አዋጅ የወጣ ይመስል ተሰብስቦ ቡና መጠጣት የለ፤ መወያየት የለ።
ለምንድን ነዉ? ብትሉኝ ከላይ ያነበባችሁትን አቋም የያዘ የመንግስት ሃሳብ ባንዳንድ የቡና ጠላት በምያስመሰላቸዉ ሰዎች ይነግረናል።
በሰፈራችን አንጋፋዋ የቡና ጥበብ ባለቤት ወይዘሮ ጀሚላ ከድር
"ኻዮሉማ/xayouluma እናትህን ቡና ጠጭ በላትና አንተም አብርሃት ና !!!"
የምለዉ ቴክኖሎጅያዊ ትዕዛዟ አሁን አይቀጥልም።
በደህንነት ሰበብ የወይዘሮ ጀሚላ ቡና ለ፶ ተከታታይ ቀናት ተቋርጧል። በቃ ቀኑ እንደት እንደምያዝግ የምናዉቀዉ እኛ የጀሚላ ጎረበቶች ነን።
በዝህ በተረገመና በተጭበረበረ ምርጫ ሰበብ ስንቱን እንጣ
ምርጫ ስመጣ ዱላ መረጣ !!
ምርጫ ስመጣ ፖሊስ እኛኑ ቅጥቀጣ!!
ምርጭ ስመጣ እስር መጣ!!
ምርጫ ስመጣ አድስ አስቸኳይ አዋጅ ወጣ!!
ምርጭ ስመጣ በቡና አቅም የት ሄደን እንጠጣ።(እነዴ ቡና ለመጠጣትም በዉጪ ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት እንጠይቅ)
ምርጫ ስመጣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክህደት ዓይን አወጣ።(የፓርቲ መሪዎች የከዱት የምክዱበት ወር መጣ።)
"አንተ ኻዮሉማ/xayouluma ጄሚላ ዛሬ ቡና አላፈላችም ?" የእናቴ ጥያቀ ነዉ።
የኔእናት ቡና እንዳይጠጣ የምል ጊዜያዊ አዋጅ እንደወጣ አልሰማችም። በቃ በጠቅላላ ኻዮሉማ/xayouluma ምን ዓይነት ሰፈር ነዉ ያላችሁ? ለምትሉኝ ፣ የኛ ሰፈር ነዋሪዎች በሙሉ ከሃገራዊ ምርጭዉ ይልቅ የጄሚላ ቡና ይናፍቀዋል። በ5 ዓመት አንደ ከምመጣዉ ምርጭ የጀሚላ ዕለታዊ ቡናን ይመርጣል። ለምን ይህን የመረጠ ይመስላችኋል ?
መልሷን ከታች ባለችዉ ባዶ ሳጥን ሙሏት።
የኔ ግምት ግን
ምርጫዉ ስለተጭበረበረ ይሁን ?
ምርጫዉ የኛ ሰፈርን ስለማይወክል ይሁን ?
አልያም ምርጫዉ ቀድሞዉኑ ዉጠቱ ስለምታወቅ ይሁን?
ያም ሆነ ይህ በምርጫ ምክንያት ኔዎርኩ አይቆራረጥብን!!
መንግስት ያሰራቸዉን ኔትዎርኮች ይፈቱልን!!!
ኻዮሉማ/xayouluma
No comments:
Post a Comment