Thursday, February 27, 2014

የአፍሪካ መሪዎችና አማፅያን በሩሲያዊው የክላሺንኮቭ ፈጣሪ ህልፈት አዝነዋል!




    ክላሺንኮቭ (AK-47) የተባለውን ለሁሉም ሥፍራ ተስማሚና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ  የጦር መሣሪያ በመፈልሰፍ፣ ለመላው ዓለም “እነሆ በረከት” ያሉት ሩሲያዊው “ጀግና” ሚካሄል ክላሺንኮቭ፤ ባለፈው ሰኞ በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ማዘኔ አልቀረም፡፡ (የአፍሪካ መሪዎችና አማፅያን ባለውለታ መሆናቸውን እንዳትረሱት!) በነገራችሁ ላይ ሰውየው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በልብ ችግር ሲሰቃዩ የቆዩ ሲሆን ለአንድ ወር ያህል በሆስፒታል ተኝተው የህክምና ክትትል ቢደረግላቸውም ከመሞት አልዳኑም፡፡ እሳቸውስ የእድሜ ባለፀጋ ናቸው - በ94 ዓመታቸው ነው የሞቱት፡፡ እሳቸው በሰሩት ክላሺንኮቭ ሲጠዛጠዙ በለጋ እድሜያቸው የተቀጩ አፍሪካውያንን ራሷ አፍሪካ ትቁጥረው!!  ሚኻኤል ክላሺንኮቭ በለጋ እድሜያቸው የእርሻ መሣሪያ የመሥራት ህልም ነበራቸው፡፡ (ህልሙ ነፍስ ሳይዘራ ቀረ እንጂ!) የማታ ማታም በዝነኛው ክላሺንኮቫቸው በዓለም ላይ እህል ሳይሆን ምስቅልቅል ቀውስ ዘሩበት፡፡ በህይወት ሳሉ የጦር መሣሪያ በመስራት ለህዝቦች ደም መፋሰስ ያበረከቱት አስተዋፅኦ ሰላም ይነሳቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ የተጠየቁት ሚኻኤል ክላሺንኮቭ “እኔ እንቅልፌን ስለጥጥ ነው የማድረው፡፡ መስማማት አቅቷቸው የጦርነት አማራጭን የሚወስዱት ፖለቲከኞች ናቸው ተጠያቂዎቹ” በማለት ራሳቸውን ነፃ አድርገዋል (ከደሙ ንፁህ ነኝ እንደማለት!)

    የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሰራር ፈተና ላይ ወድቋል!

    ከተመሰረተ ስልሳ አምስት አመቱን ያስቆጠረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ አለምአቀፋዊ ተቋምነቱ እና የብዙዎችን ይሁንታ ያገኘበት ሀላፊነቱ በተግባር በሚያከናውነው ስራ አንፃር ሲመዘን ጥያቄ ላይ የወደቀ ድርጅት ነው፡፡ አሁን በሀላፊነት ላይ ያሉት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ ባን ኪ ሙን የመንግስታቱን ድርጅት የመለወጥ ሀሳብ በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡ ነገር ግን፣ ድርጅቱን በዋና ፀሀፊነት ካገለገሉ ስምንት ሰዎች ውስጥ አንዱ ብቻ ናቸው ስለ ለውጥ ምንም ተናግረው የማያውቁት፡፡ የተወሰኑ ለውጦች በተለያዩ ጊዜዎች የተደረጉ ቢሆንም፣ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ግን ምንም አይነት ለውጥ አለመደረጉ ጥያቄዎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲበረቱ አድርጓል፡፡
    በድርጅቱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች የአባል አገሮቹን ያህል የበዛ እና የተወሳሰበ ቢሆንም፣ በማሻሻያዎቹ ላይ ጥናት ያደረገው ዛክ ቱከር፣ ጥያቄዎቹን በሶስት ዋና ዋና ምድቦች ይከፍላቸዋል።

    “የህወኀት ዓላማ ግቡን አልመታም”

    አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ፤ ከህወኀት መስራቾች አንዱ)
    የካቲት 11 ይዛችሁ የተነሳችሁት አላማ ምን ነበር?
    እኛ በዛን ወቅት ይዘነው የተነሳነው አላማ፣ ደርግን በሰላማዊ መንገድ መጣል ስለማይቻል፣ በትጥቅ ትግል ገርስሰን እንደ መሬት ላራሹ ያሉ የህዝብ ጥያቄዎችን መመለስ ነበር፡፡ የመጀመሪያ አቋማችን የዘውዳዊውንና የደርግን ህገመንግስት መቀየር የሚል ሲሆን አቋሙ በማኒፌስቶ ፅንሰ ሀሳብ ላይ የተነደፈ አልነበረም፡፡ በቁርጥራጭ ወረቀትና በቃል ነበር የተያዘው፡፡ በሶስትና አራት ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ስልሳ ሰባት ሰው ትግሉን ተቀላቀለ፡፡ መጀመሪያ ላይ ሃገራዊ፣ ብሄራዊና መደባዊ ትግል በማካሄድ ህዝባዊ መንግስት መመስረት የሚል ዓላማ የነበረ ሲሆን ከአመራሩ አካባቢ ደግሞ “እኛ የምንታገለው ከአማራ ቅኝ ገዢዎች ነፃ ለመውጣት ነው፤ ስለዚህ ዓላማችን ነፃ ሪፐብሊክ ትግራይን መመስረት ነው” የሚሉ ሀሳቦች መፍለቅ ጀመሩ። ከአንድ ዓመት በኋላ ሃሳቡ በህወኀት መሪዎችና ለእነሱ ቅርበት በነበራቸው ታጋዮች ተረቀቀና በማኒፌስቶ ወጣ፡፡ አቶ ስዩም መስፍን ሱዳን ውስጥ አሳትመው አመጡት፡፡

    የአርሲ ጉዞዬ አስደናቂ ማስታወሻ

                                                                                                  Written by  ነቢይ መኮንን

     ከ38 ዓመት በኋላ ከመቃብር የወጣው አስከሬን ትርዒት

    የፊዚክስ ባለሙያው የዶ/ር ሙሉጌታ በቀለ አባት የፊታውራሪ በቀለ ኦገቶ አስከሬን እንዴት ተገኘ? ዝርዝሩ ብዙ ነው፤ ጉዳዩ ግን ተዓምር ተባለ!

    ወደ አርሲ አሰላ - ሳጉሬ መንገድ የጀመርነው ቅዳሜ የካቲት 8 ቀን 2006 ዓ.ም ከንጋቱ ለአንድ ሩብ ጉዳይ ነው፡፡
    ከናዝሬት .. ወደ ሶደሬ አቅጣጫ … መልካሰዲ ስንደርስ ወደ ቀኝ ዞረን ዴራ፣ ኢቲያን አልፈን በብቅል ፋብሪካ አድርገን አሰላ ገባን፡፡ ከዚያ ወዲያ እንግዲህ ከ 23 ኪ.ሜ በኋላ ሳጉሬ ወረዳ ልንሄድ ነው፡፡
    ወደ ሳጉሬ ከመሄዳችን በፊት ወደ አሰላ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መሄድ ዋንኛው የመርሀ-ግብሩ መነሻ ነው፡፡ ለምን? ታሪኩ እዚህ ጋ ይጀምራላ፡፡
    38 ዓመት የፈጀው አስከሬን ለምን ይሄን ያህል ጊዜ ፈጀ? ሂደቱ ምን ይመስላል? ከመጨረሻው ትርዒት ጀምረን ወደ ኋላ 38 ዓመት እንጓዛለን፡፡

    Saturday, September 28, 2013

    ከአስር ሺ ካድሬዎች አንድ ጀግና አትሌት ይሻለኛል!

    የፌዴሬሽን ነገር አልተሳካልንም!
    ሩጫ እንደ አፍ አይቀናም (ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽን!)
    .የዛሬውን ፖለቲካዊ ወጌን የምጀምረው በአትሌቲክስ ነው፡፡ አትሌቲክስና ፖለቲካ ምን አገናኛቸው እንዳትሉኝ ብቻ! (ቀላል ይገናኛሉ!) ወዳጆቼ … አትሌቲክስ ስፖርትነቱ ለጀግኖች አትሌቶቻችን ነው እንጂ ወደ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሲገባ መልኩን ይቀይራል፡፡ (የቀለጠ ፖለቲካ ይሆናል!) ይሄ እኮ ሃሜት አይደለም፡፡ በመረጃም በማስረጃም የተደገፈ ሃቅ ነው (ፍ/ቤት የመሄድ ፍላጐት ግን የለኝም!) ለነገሩ ፍ/ቤትም ለካ እረፍት ላይ ነው፡፡ እናንተዬ … ፍ/ቤት በክረምት የሚዘጋው (የሚያርፈው) ድሮ ወንዝ እየሞላ መሻገሪያ ስለሚጠፋ ነው የሚባለው እውነት ነው እንዴ? አሁን ታዲያ የትኛው ወንዝ አስቸግሮን ይሆን? (የልማድ እስረኞች እኮ ነን!) 
    ይሄውላችሁ … ስለ ፌዴሬሽኑ ፖለቲካ ከማውጋታችን በፊት ትንሽ “ሰለብሬት” ማድረግ አለብን - ስለ አትሌቶቻችን ድል!! እናንተ … የጦቢያ አትሌቶች እንዴት አንጀት አርስ ናቸው ባካችሁ! (ኧረ ሺ ጊዜ ይመቻቸው!) ለዓለማችን ኮከብ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ (እውነትም ነገር የገባት ሰጐን!) እጅ ነስቻለሁ! ለ800 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ባለድሉ ለመሃመድ አማንም እጅ ነስቼአለሁ - በአዲስ ርቀት ላስመዘገበው ድንቅ ውጤት! ነሐስን ጨምሮ ሌሎች ድሎችን (ከ4-10 ለወጡትም) ላገኙም እጅ ነስቼአለሁ፡፡ ለደረጃ ባይበቁም ጦቢያን አደባባይ ወክለው ለሮጡልን ምርጥ የአገሬ ልጆችም እጅ ነስቼአለሁ፡፡ በሴቶች ማራቶን በገጠማቸው አንዳንድ እክሎች ውድድሩን አቋርጠው ለወጡት የጦቢያ ጀግና አትሌቶችም እጅ ነስቼአለሁ (ፌዴሬሽኑ ደብዳቤ ፃፉ ቢልም) አንዳንዴ ምን እንደማስብ ታውቃላችሁ? ኢትዮጵያን የሚመሯት ምነው አትሌቶች በሆኑ እላለሁ (የድል አርማ ናቸዋ!)

    ሙዝ!

    የግል ሐኪምዎ የሆነው ሙዝ!
    በስትሮክ የመሞት አደጋን ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል
    ለስኳር ህመምና ለደም ማነስ ሙዝን መመገብ ይመከራል
    በኢትዮጵያ እንደተገኘ የሚነገርለትና በዓለማችን በስፋት እየተመረተ ለምግብነት የሚውለው ሙዝ እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ሙዝ ከምግብ ይዘቱ በተጨማሪ ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስ ሊያስገኙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም አካቶ ይዟል። እነዚህ ንጥረነገሮች ለበርካታ በሽታዎች ፈውስ ከመሆናቸውም በላይ፣ በሽታው ከመከሰቱም በፊት ለመከላከል የሚያስችለንን አቅም ያጐናጽፉናል፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጠቅላላ ህክምና ክፍል ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ታዬ አለማየሁ እንደሚናገሩት፤ ሙዝ በስትሮክ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን ሞት በግማሽ መቀነስ ይችላል፡፡

    የጀግና አሟሟት

    ምዕራፍ አንድ፡- አጼ ቴዎድሮስ እና ሞት
    አትጠገብ የምትባል ሴት ከ195 አመታት በፊት ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ ወይዘሮ አትጠገብ ሀይለ ጊዮርጊስ ከሚባል ውድ ባለቤቷ ካሣ የሚባል ልጅ ወለደች፡፡ ልጁ ካሣ ሀይሉ ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ ካሣ ሲያድግ ንጉስ መሆን አማረው፡፡ ካሣ በተወለደበት ዘመን ተራ ሠው አይነግስም፡፡ ነገሥታት የሚሆኑት የሠለሞን ዝርያ ያላቸው፣ በእግዚአብሔር የተመረጡ እና የተሰየሙ እናም የነዚህ ሠዎች ዝርያዎች ነበሩ፡፡ ካሣ ግን ንጉሥ መሆን አማረው፡፡ ሲያስብ እንዲህ እያለ ነበር ፡- “የነገስታቱ ዝርያ አይደለሁም፡፡” “እና ባልሆንስ?!” “አትቆጣ?!” “መቆጣት አይደለም፡፡” “እና ታዲያ;!” “ንጉሥ መሆን አምሮኛል!” “እና ንጉሥ መሆን የምችል ይመስልሃል?!” “Yes, I can” ብሎ ተነሳ፡፡ የአሜሪካው ንጉስ ባራክ ኦባማ `Yes, we can` የሚለውን የምርጫ መወዳደሪያ መፈክር የኮረጀው ከካሳ ሀይሉ ነው፡፡ የምናውቅ እናውቃለን፡፡

    አ ገ ሬ

    አገሬ ውበት ነው፣
    ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት፣
    ፀሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
    አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ፣
    እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ እስኪነጋ።
    አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ፣
    አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፣
    ውበት ነው በበጋ ፀሃይ አትፋጅም፣
    ክረምቱም አይበርድም፣
    አይበርድም፣ አይበርድም።
    አገሬ ጫካ ነው፣
    እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት፣
    በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።

    ከሠማይ ወረደ በተባለው መስቀል ላይ ቅዱስ ሲኖዶሡ ውሣኔ ይሰጣል

    በአቃቂ ቃሊቲ ገላን ጉራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ከሠማይ ወረደ ስለተባለው መስቀል ቅዱስ ሲኖዶስ ውሣኔ እስኪያስተላልፍ ህዝቡ በትዕግስት እንዲጠባበቅ የአዲስ አበባና የጅማ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አሣሠቡ፡፡ “መስቀል ከሠማይ ወርዷል አልወረደም? ትክክለኛ ነው አይደለም?” የሚለውን ለመመለስ የግድ ቅዱስ ሲኖዶሡ ጉዳዩን መርምሮ ውሣኔ ሊያስተላልፍበት ይገባል ያሉት ብፁዕነታቸው፤ ይህን ለማድረግም ጉዳዩን ለቅዱስ ሲኖዶሱ ቋሚ አባላት እንዳሣወቁ ተናግረዋል፡፡ መስቀሉ እንደተባለው ከሠማይ የወረደ አለመሆኑ ከተረጋገጠም የቤተክርስቲያኒቱ ሃላፊዎች ይጠየቁበታል ብለዋል-ብፁዕነታቸው፡፡
    መስቀሉ ከሠማይ ወረደ በተባለ በ4ኛው ቀን ነሐሴ 27 ቀን 2005 ከሠአት በኋላ ወደ ስፍራው በማቅናት ተገቢውን የፀሎት ስርአት ከካህናቱና ከቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ጋር ካደረሡ በኋላ መስቀሉን ከወደቀበት መሬት አንስተው ወደ ቤተመቅደሡ እንዲገባ ማድረጋቸውን የገለፁት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፤ መስቀሉ ከሠማይ ስለመውረዱ በአይናችን አይተናል ካሉት የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች እንደማንኛውም ሠው መስማታቸውን ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
    መስቀሉን ከወደቀበት መሬት ያነሱት ብፁዕነታቸው፤ “መስቀሉ ያቃጥላል፤ ብርሃናማ ነፀብራቅ አለው” የሚባለውን አለማስተዋላቸውን ጠቁመው፤ “መስቀል የሚያቃጥል ሣይሆን የድህነት ሃይል ነው ያለው፣ የሚያቃጥል ቢሆን ኖሮ ከመሬት ላይ ማንሣት ባልተቻለ ነበር” ብለዋል፡፡ ወረደ የተባለውን መስቀል ለመመልከት ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ምዕመናን ለምን እንዳይመለከቱት ተከለከለ የሚል ጥያቄ ያነሣንላቸው ብፁዕነታቸው፤ ጉዳዩ በቅዱስ ሲኖዶሡ ተጣርቶ ውሣኔ እስኪያገኝ ድረስ ህዝበ ክርስቲያኑ ጉዳዩን በጥሞና እንዲያጤነው በማሠብ ነው” ብለዋል፡፡

    Tuesday, April 16, 2013

    የተንቀሳቃሽ ስልክ 40ኛ ዓመት

    እ ጎ አ በ 1875፣ የድምጽ ሞገድ በሽቦ ወደ ኤሌክትሪክ ሞገድ ተለውጦ እንዲተላለፍና ፤ ምልክቱ፤ በድምፅ ፤ በቃላት እንዲሰማ ያበቃውን ፤ ስልክ የተባለውን መሣሪያ ፣አለክሳንደር ግርሃም ቤል ከሠራ ወዲህ፤እ ጎ አ በ 1876 በተሽከርካሪ « ዲስክ»
    እ ጎ አ በ 1875፣ የድምጽ ሞገድ በሽቦ ወደ ኤሌክትሪክ ሞገድ ተለውጦ እንዲተላለፍና ፤ ምልክቱ፤ በድምፅ ፤ በቃላት እንዲሰማ ያበቃውን ፤ ስልክ የተባለውን መሣሪያ ፣አለክሳንደር ግርሃም ቤል ከሠራ ወዲህ፤እ ጎ አ በ 1876 በተሽከርካሪ « ዲስክ» ላይ በኤሌክትሪክ ርዳታ፣ ምስል ማሳየት እንደሚቻል ጀርመናዊው Paul Gottlieb Nipkow ካሳወቀና እስኮትላንዳዊው ጆን ሎጊ ቤርድ፣ ራሱ በተናጠል ባካሄደው ተመሳሳይ ምርምር የቴሌቭዥንን ምሥጢር ለህዝብ ካሳዬ በኋላ፣በሩሲያዊ አሜሪካዊው ቭላዲሚር ዝቮሪኪን ፣ እ ጎ በ 1933 ኛዎቹ ዓመታት ፤ በ 1940ኛዎቹ ዓመታት ይበልጥ እስኪሻሻል ድረስ፤ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች እንዲሠራጩ ለማድረግ ማብቃቱ ተረጋገጠ። በኋላም እንደገና BAIRD ባለቀለም ምስሎችን በቴሌቭዥን ማሠራጨት የሚቻልበትን አብነት አግኝቶ ማሠራጨት እንደሚቻል
    ሞቶሮላ RAZR
    ካመላከበት ዘመን አንስቶ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ በመስታውት ሣጥን የሚታይበት አስደናቂ የሥነ ቴክኒክ ግኝት በዓለም ውስጥ መዛመቱ አልቀረም። ከዚያም የኮምፒዩተር ዘመን ከተተካ በኋላ፤ ውሎ አድሮ ፤ መዳፍ በሚያክል የሥነ ቴክኒክ ውጤት ያለሽቦ ድምጽንም ምስልንም የሚያቀብሉም የሚያሠራጩም መሣሪያዎች ቀርበዋል።

    የመታሰቢያ ድርጅቶች (ፋውንዴሽን) ከአፄ ምኒልክ እስከ መለስ

     የመታሰቢያ እና በጐ አድራጐት ድርጅቶች የ85 ዓመታት ጉዞ
    ከመላው ዓለም በፊዚክስና ኬሚስትሪ፣ በሕክምናና በሥነ ፅሁፍ እንዲሁም በሰላም ዙርያ የላቀ አስተዋፅኦ ያደረጉ ሰዎች ተመርጠው የሚሸለሙበት የኖቤል በጐ አድራጐት ድርጅት በተመሰረተ በ10ኛ ዓመቱ በኢትዮጵያም ተቀራራቢ ዓላማ ያለው “መታሰቢያ ድርጅት” ተቋቁሟል፡፡ አፄ ምኒልክ ከሞቱ ከአራት ዓመት በኋላ ልጃቸው ንግሥት ዘውዲቱ በ1910 ዓ.ም ለአባታቸው መታሰቢያነት አራት ኪሎ የሚገኘውን የበአታ ለማርያም ገዳም ቤተክርስቲያንን ማሰራት ጀመሩ፡፡
    በግዛው ኃይለማርያም ተዘጋጅቶ የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ድርጅት በ1956 ዓ.ም ባሳተመው “ዳግማዊ ምኒልክ” የተሰኘ መፅሃፍ፤ የበጐ አድራጐት ሥራዎች በሦስት ዘርፎች ተከፍለው እንደሚከናወኑ ያመለክታል፡፡ የመጀመሪያው መታሰቢያቱን ማዕከል ያደረገው ነው፡፡ ግንባታው በተጀመረ በአስረኛ ዓመቱ በ1920 ዓ.ም የተጠናቀቀው የበአታ ለማርያም ገዳም ቤተክርስቲያን፤ የአፄ ምኒልክ፣ የእቴጌ ጣይቱ፣ የንግሥት ዘውዲቱ፣ የብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ የልዕልት ፀሐይ ኃይለሥላሴ አስከሬንና የተለያዩ ታሪካዊ ቅርሶች መቀመጫ ሆኗል፡፡ መታሰቢያ ድርጅቱ፤ በሁለተኛ ደረጃ ተግባራዊ ያደረገው መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ማቋቋም ሲሆን በ1925 ዓ.ም የተመሰረተው የአብነት ትምህርት ቤት፤ አገልግሎቱን ሳያቋርጥ እስካሁን በመቀጠል 80 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡

    የማይቃወሙ ተቃዋሚዎች በባትሪ ይፈለጋሉ!

    *ኢህአዴግ - “ቀፎ ከእኔ፤ ማር ከእናንተ!” እያለ ነው
    *መንገድ ትራንስፖርት - “መንገድ ከእኔ፤ ትራንስፖርት ከናንተ!” ይላል
    ሁልጊዜ ምን እንደሚገርመኝ ታውቃላችሁ? የኢህአዴግ ነገር! አልሳካ ብሎት እንጂ ሁላችንንም እንደቀለበት መንገድ ጥፍጥፍ አድርጐ በአንድ ቅርፅ ቢሰራን ደስታውን አይችለውም፡፡ (ከፍቅሩ የተነሳ እኮ ነው!) በተለይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንማ---ሁሉንም በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ርዕዮተ ዓለም ቢያጠምቃቸው እፎይ ብሎ እንቅልፉን በለጠጠ ነበር፡፡ ግን እኮ አምባገነንነት አምሮት አይደለም (ኧረ ሲያልፍም አይነካው!) በነገራችሁ ላይ … በአምባገነኖች ላይ ባደረግሁት Formal ያልሆነ “ባህላዊ ጥናት”፤ አብዛኞቹ አምባገነኖች የእግዚአብሔርን ስም ደጋግመው መጥራት እንደሚወዱ አረጋግጬአለሁ፡፡ (ማጭበርበርያ እኮ ነው!) ለምሳሌ ባለፈው ሳምንት በካንሰር ህመም የሞቱት የቬንዝዌላው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሁጎ ቻቬዝና የቀድሞው የኡጋንዳ ፕሬዚደንት ኢዲ አሚን ተጠቃሽ ናቸው - የፈጣሪን ስም በመጥራት፡፡ አሚንማ ከእግዚአብሔር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አደርጋለሁ ባይ ነበሩ፡፡

    ለኢቴቪ ዓመቱን ሙሉ “April the fool” ነው!

    ሰሞኑን የተከሰተ ዜና ነው - እዚህ ሳይሆን ፈረንጆቹ አገር፡፡ ሁለት ታዳጊ ፍቅረኛሞች ናቸው አሉ፡፡ የፍቅር ጓደኝነት ከመሰረቱ ብዙ አልቆዩም፡፡ ግን ሲዋደዱ ለጉድ ነው፡፡ (እንደ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች እንዳትሉኝ!) ባለፈው ሰኞ ግን በጨዋታ መሃል በተፈጠረ አለመግባባት እሷ እሱን አንገቱ ላይ በስለት ወግታው ወህኒ ወረደች አሉ (የአፍሪካ ፖለቲካ አይመስልም?) አያችሁ እንዲህ በጨዋታ መሃል ያልተጠበቀ አደጋ ሊከሰት ይችላል፡፡ አንዳንዴ ዓይን ሊጠፋ ወይም እግር ሊሰበር ይችላል፡፡ ባስ ሲል ህይወትም ይጠፋል፡፡ በፍቅር ጨዋታ እንዲህ ካጋጠመ በፖለቲካ ጨዋታ ምን ሊያጋጥም እንደሚችል አስቡት፡፡
    እቺን እቺንማ ከእኛ በላይ ማን ያውቃታል? ምንም ቢሆን እኮ የአፍሪካ ልጆች ነን! (የአራዳ ልጅ እንዲሉ) የጨዋታው አባቶች የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ከሆኑ ደግሞ ነገርዬው የከፋ ይሆናል - የመረረ!! ለምን መሰላችሁ? መቼ እንደሚያመሩ፤ መቼ ከፍቅር ወደ ጥላቻ እንደሚሸጋገሩ ፈጽሞ አታውቁም፡፡ ኳስ ይዞ የነበረው እጃቸው በምን ቅጽበት ጠብመንጃውን አፈፍ እንዳደረገ ፈጣሪያቸው ብቻ ነው (የራሳቸው ፈጣሪ ይኖራቸዋል ብዬ እኮ ነው!) የሚያውቀው (“አድነነ ከመዓቱ” ማለት ይሄኔ ነው!) ይኸውላችሁ የእኔ ነገር የፍቅረኞቹን ሳልጨርስላችሁ ፖለቲካ ውስጥ መሰስ ብዬ ገባሁላችሁ፡፡ (ፖለቲካ አሳሳች እኮ ነው!) እናላችሁ.. ሁለቱ ፍቅረኛሞች ሲገናኙ ሁሉም ነገር አማን ነበር፡፡ በተለይ እሱ ፍቅር እንጂ ሌላ አልጠበቀም፡፡

    የካፒታሊዝም የኑሮ ፍልስፍና!

    በዓለማችን ውስጥ የሚገኘው አጠቃላይ የምግብ ክምችት በዓለም ላይ ያሉ ሰዎችን በሙሉ ማጥገብ ይችል ነበር፤ ነገር ግን አብዛኛው የዓለማችን ሃብት በጥቂት ግለሰቦች ቁጥጥር ስር በመውደቁ ጥቂቶቹ የቅንጦት ኑሮ ሲኖሩ አብዛኛው ደሃ ህዝብ ግን በረሃብ አለንጋ ይገረፋል፤ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ባለመኖሩ፤ በማለት ማርክሲስቶች እኩልነት ደሃና ሃብታምን እኩል በማድረግ ማረጋገጥ እንደሚቻል ያስተምራሉ፡፡ በሌላ በኩል የካፒታሊዝም መስራቾች የግል ሃብት የማፍራት መብትን በማረጋገጥ የሃብታሞችና የድሆች መደቦችን በመፍጠር፣ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን ማስፈን እንደሚቻል ወይም እኩልነትን በሃብት መበላለጥ ማምጣት እንደሚቻል ይሞግታሉ፡፡ የካፒታሊዝም ሆነ የሶሻሊዝም መስራቾች ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልንና እኩልነትን ይሰብካሉ፡፡

    ያልተጠናው የኢትዮጵያውያን ፍልስፍና

    ሀገራችን ኢትዮጵያ ገና ያልተጠኑ የበርካታ ጥንታዊ ሥነጽሁፎች ባለቤት ናት፤ ማጥናት አቅቶን ሌሎች አጥንተው የቅጂ መብቱን ከመውሰዳቸውና የታሪክ ክፍትት ተፈጥሮ በመጪው ትውልድ ተወቃሾች ከመሆናችን በፊት የዘርፉ ምሁራን ጥናትና ምርምር በማካሄድ፣ ዩኒቨርስቲዎች ጉዳዩን የምርምር አቅጣጫቸው ውስጥ በማስገባት፣ ዜጎችም ጥንታዊ የጽሁፍ ሃብታችንን አስፈላጊነት ተገንዝበን ከዘራፊዎች በመጠበቅ ሃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ ዘመናትን ያስቆጠሩ ሥነቃላዊና የጽሁፍ ፍልስፍናዎች ባለቤት ናት፡፡ ከአስራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት ከሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች በተለየ መልኩ በርከት ያሉ የፍልስፍና ስራዎችን በመስራት በቀዳሚነት የምትጠቀሰው ኢትዮጵያ፤ በጥንታዊው የግእዝ ቋንቋ ከተጻፉት የፍልስፍና ስራዎቿ መካከል ከፊሎቹን በትውልድ ካናዳዊ፣ በምርጫ ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሆነው ፕሮፌሰር ክላውድ ሰምነር ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ በመተርጎም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቁ ሲያደርግ፤ ሌሎች በርካታ በግዕዝና በአረብኛ ቋንቋዎች የተጻፉ የጽሁፍ ስራዎች በጥንታዊ ቤተእምነቶችና ቤተመዛግብት ውስጥ ተቀምጠው ክላውድ ሰምነርን የመሰሉ ፈላስፎችንና የጥንታዊ ጽሁፎች ተመራማሪዎችን (philologists) እይታ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

    “ወሬ ይሮጣል!” - የበአሉ ነገር!


    • ፊያሜታ
    አነበብኩት፡፡ ደግሜ አነበብኩት፡፡ መላልሼ አነበብኩት፡፡ ለምን እንደሆነ አላውቅም ያነበብኩትን ነገር ለማመን አቃተኝ፡፡ ሉጫ ፀጉራቸው እርስ በርሱ ተገማምዶ ጀርባቸው ላይ የወደቀ፣ ወዝ የጠገበ ላመነት ያገለደሙ፣ እህል የራቀው አንጀታቸውን በሰንሰለት ሸብ ያደረጉ፣ ፂማቸውን ያንዠረገጉ፣ ከአለም ተነጥለው በራቸውን የዘጉ…እንዲህ ያሉ መናኝ ---- በአሉ ግርማን ማሰብ አቃተኝ፡፡ “አበቃ” ብሎ በዘጋው ጦሰኛ ስራው ሰበብ፣ የእሱም ነገር እንዳበቃ ከተነገረለት፤ ከዚያኛው በአሉ የቀጠለ ሌላ በአሉ አልመጣልህ አለኝ፡፡ ከተቋጨ ደራሲነትና ጋዜጠኝነት የቀጠለውን የበአሉ መናኝነት ማሰብ ተሳነኝ፡፡ ባለፈው ሰኞ ምሽት አንድ ወዳጄ በፌስቡክ የላከልኝ “ጉድ” “በአሉ ግርማ በጣና ደሴት ገዳማት የመናኝ ህይወት እየገፋ ተገኘ” የሚል ነበር፡፡ ይህን “ጉድ” ለማመን ቸግሮኝ ጥቂት እንደተወዛገብኩ፣ ነገርዬው “የሚያዝያ ልግጥ” (April the fool) ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ፡፡

    Wednesday, April 3, 2013

    ከሚድሮክ ኢትዮጵያ ከ632 ሚሊዮን ብር በላይ የግብር ዕዳ ይፈለጋል

    ሚድሮክ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከንግድ ትርፍ ግብርና ከተጨማሪ እሴት ታክስ ከ632 ሚሊዮን ብር በላይ ዕዳ በመንግሥት እንደሚፈለግበት የኩባንያው ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡
    ሚድሮክ ይህንን ክፍያ እንዲፈጽም የተነገረው ለባለኮከብ ሆቴሎቹ መሆኑ ታውቋል፡፡

    የኩባንያው ምንጮች እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ ለሚድሮክ ኢትዮጵያ በላካቸው ሦስት የትርፍ ግብር ውሳኔ ማስታወቂያዎች የተጠቀሰው ገንዘብ እንዲከፈል ጠይቋል፡፡

    የድምፅ ብክለት

    የድምፅ ብክለት የአየር ብክለትን ተከትሎ ያለ በዓለም ሁለተኛው ግዙፍ የአካባቢያችን ብክለት

    ይህንን የብክለት ዓይነት የሚፈጥረው ድምፅ ያልተፈለገና በሰው መረበሽን የሚፈጥር ማንኛውም ዓይነት ድምፅ ነው፡፡

    እንዲህ ዓይነት ድምፆች መደበኛውን የሕይወታችንን እንቅስቃሴ ይጎዳሉ፤ ያስተጓጉላሉ፣ እንቅልፍ ይነሱናል፤ ውይይቶቻችንንና መደማመጣችንን ይቀንሣሉ፤ በአጠቃላይ የአኗኗራችን ሁኔታ የተረበሸ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡

    ዓይነት ነው፡፡

    የኣበሾች ሁሉ የኩራት ምንጭ






    የኣበሾች ሁሉ የኩራት ምንጭ
    የኣክሱም ስርወ መንግስት በኣፍሪቃ ሰሜናዊ ምስራቅ የሚገኝ እጀግ ጠቃሚ የንግድ ብሔር ነበር፡ ፡ ስርወ መንግስቱ በ300 ዓ.ዓ. ኣከባቢ ኣብቦ በ 300 ዓ.ም. ኣከባቢ ከፍተኛ የስልጣኔ ድረጃ የደረሰ ስርወ መንግስት ነበር፡ ፡ ከሮማ ስርወ መንግስትና ከጥንታዊዋ ሕንድ ጋር የንግድ ግንኝነት የነበረው ስርወ መንግስት የራሱ የመገበያያ ገንዘብ ነበረው፡ ፡ የኣክሱም ስርወ መንግስት በደቡባዊ የኩሽ ግዛት ላይ የበላይነትን ይዞ የቆየ ከመሆኑም በላይ የኣረቡን የባሕር ሰላጤ በከፊል በፖሊቲካ መቆጣጠር የቻለ ስርወ መንግስት ነበር፡ ፡
    የኣክሱም ስርወ መንግስት በኣፍሪቃ ሰሜናዊ ምስራቅ የሚገኝ እጀግ ጠቃሚ የንግድ ብሔር ነበር፡ ፡ ስርወ መንግስቱ በ300 ዓ.ዓ. ኣከባቢ ኣብቦ በ 300 ዓ.ም. ኣከባቢ ከፍተኛ የስልጣኔ ድረጃ የደረሰ ስርወ መንግስት ነበር፡ ፡ ከሮማ ስርወ መንግስትና ከጥንታዊዋ ሕንድ ጋር የንግድ ግንኝነት የነበረው ስርወ መንግስት የራሱ የመገበያያ ገንዘብ ነበረው፡ ፡ የኣክሱም ስርወ መንግስት በደቡባዊ የኩሽ ግዛት ላይ የበላይነትን ይዞ የቆየ ከመሆኑም በላይ የኣረቡን የባሕር ሰላጤ በከፊል በፖሊቲካ መቆጣጠር የቻለ ስርወ መንግስት ነበር፡ ፡

    መድረክ ማኒፌስቶ ኣወጣ



    መድረክ ‹‹የኢትዮጵያ ወቅታዊና መሠረታዊ ችግሮች የመፍቻ አቅጣጫዎች ማኒፌስቶ›› የሚል ስያሜ የሰጠውን ሰነድ ማክሰኞ ዕለት ይፋ አደረገ፡፡ኦነግ ኣንጋፋ ኣባላት " ለ እዉነተኛ ፈዴራሊዝም" የሚታገል ኣዲስ ድርጅት ማቋቋማቸውን ይፋ ኣድረገዋል፡ ፡

     ማኒፌስቶው አገሪቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች፡፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት የበለጠ ኣደጋ ተደቅኗል ይላል፡፡
    ማኒፌስቶውን ለማስተዋወቅ ከቀረቡት የፓርቲው አመራሮች መካከል ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ ‹‹የመለስ ራዕይ ለኢትዮጵያ የውድቀት መንገድ ነው›› በማለት በአሁኑ ወቅት የገዥው ፓርቲ አመራሮች እየተከተሉ የሚገኙትን በመለስ አስተምህሮ የአገሪቱን ሁለንተናዊ ዕድገት የማስቀጠል መርህን ወቅሰዋል፡፡