Wednesday, April 3, 2013

የድምፅ ብክለት

የድምፅ ብክለት የአየር ብክለትን ተከትሎ ያለ በዓለም ሁለተኛው ግዙፍ የአካባቢያችን ብክለት

ይህንን የብክለት ዓይነት የሚፈጥረው ድምፅ ያልተፈለገና በሰው መረበሽን የሚፈጥር ማንኛውም ዓይነት ድምፅ ነው፡፡

እንዲህ ዓይነት ድምፆች መደበኛውን የሕይወታችንን እንቅስቃሴ ይጎዳሉ፤ ያስተጓጉላሉ፣ እንቅልፍ ይነሱናል፤ ውይይቶቻችንንና መደማመጣችንን ይቀንሣሉ፤ በአጠቃላይ የአኗኗራችን ሁኔታ የተረበሸ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡

ዓይነት ነው፡፡


የድምፅ ብክለት

የድምፅ ብክለት የሚፈጥረው መረበሽና የኑሮ መስተጓጎል ከሚያደርሣቸው የበረቱ የጤና ችግሮች መካከል ከጭንቀት ጋር የተያያዘ የበረታ የደም ግፊት፣ የአንደበት መንተባተብና የንግግር ስክነት ማጣት፣ የመስማት ችሎታ መጥፋት፣ እንቅልፍ ማጣት፣ የልብና የደም ዝውውር ሥርዓት መስተጓጎልና መመሣቀል ይገኙበታል፡፡

የድምፅ ብክለት በጤና ላይ በቀጥታ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ የምርታማነት መቀነስ፣ የትፊክ አደጋዎች መበራከት፣ የማኅበራዊ ሕይወት መደፍረስ፣ የቤተሰቦች መመሳቀል፣ የልጆች አዕምሮ መድከም፣ በውጤቱም የትውልድ ጉዳት ይከተላል፡፡
የድምፅ ብክለት
የድምፅ ብክለት

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የድምፅ ብክለት ለመቀነስና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት “ባለድርሻ” ከሚባሉ የንግድና የግንባታ ድርጅቶችን፣ የዕምነት ተቋማትን፣ የሕዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ሰጭዎችን የመሣሰሉ አካላት ጋር በክልልና በፌደራል ደረጃ እየተሠራ መሆኑን የፌደራሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የኮምዩኒኬሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አያሌው ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

No comments: