Wednesday, April 3, 2013

መድረክ ማኒፌስቶ ኣወጣ



መድረክ ‹‹የኢትዮጵያ ወቅታዊና መሠረታዊ ችግሮች የመፍቻ አቅጣጫዎች ማኒፌስቶ›› የሚል ስያሜ የሰጠውን ሰነድ ማክሰኞ ዕለት ይፋ አደረገ፡፡ኦነግ ኣንጋፋ ኣባላት " ለ እዉነተኛ ፈዴራሊዝም" የሚታገል ኣዲስ ድርጅት ማቋቋማቸውን ይፋ ኣድረገዋል፡ ፡

 ማኒፌስቶው አገሪቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች፡፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት የበለጠ ኣደጋ ተደቅኗል ይላል፡፡
ማኒፌስቶውን ለማስተዋወቅ ከቀረቡት የፓርቲው አመራሮች መካከል ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ ‹‹የመለስ ራዕይ ለኢትዮጵያ የውድቀት መንገድ ነው›› በማለት በአሁኑ ወቅት የገዥው ፓርቲ አመራሮች እየተከተሉ የሚገኙትን በመለስ አስተምህሮ የአገሪቱን ሁለንተናዊ ዕድገት የማስቀጠል መርህን ወቅሰዋል፡፡

ማኒፌስቶው የተዘጋጀው ላለፉት 21 ዓመታት በኢሕአዴግ አገዛዝ የታዩ ችግሮችን ለማንፀባረቅና የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን የተናገሩት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ በዚህ የተነሳ የተቀመጡት ችግሮች መደጋገማቸው ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ሀቁ ግን አሁንም በዚሁ ችግር ውስጥ አገሪቱ መጓዟ ከሕዝብ የትዕግሥት መጠን በላይ ሆኖ የከፋ ችግር ይከሰታል፣ ለዚህም ነው በዚህ መልኩ ሥርዓት ለማስያዝ መንቀሳቀስ በመድረክ በኩል የታሰበው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የመፍትሔ አቅጣጫ ተብለው የተቀመጡት ሐሳቦችም ገዥው ፓርቲ ከተቃዋሚዎች ጋር ድርድር መጀመርና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ማድረግ እንደሚገባው የሚጠቁሙ፣ እንደ ፀረ ሽብር ሕጉ ያሉ አፋኝ አዋጆች ይሰረዙ አልያም ማሻሻያ ይደረግባቸው፣ የመደራጀት መብት ይከበር፣ የሕግ የበላይነት ይስፋ፣ የገዥው ፓርቲ ንብረት የሆኑ ተቋማት ወደ ገበያ ኢኮኖሚ አካልነት ይሸጋገሩ የሚሉ ይገኙበታል፡፡የአገሪቱን ጥቅሞችና መብቶች ለሌላ ወገን አሳልፈው የሰጡ ስምምነቶችን በሚመለከት፣ በተለይም የአልጀርስ ስምምነትንና የባህር በር ባለቤትነትን ጉዳይ እንደገና መደራደር ሌላው በሰነዱ ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን ለማስከበር የተቀመጠ የመፍትሔ አቅጣጫ ነው፡፡ የመፍትሔ ሐሳቦቹ በመድረክ የሚተገበሩ ሳይሆን በሥልጣን ላይ ያለው ኢሕአዴግ በአፋጣኝ ሊተገብራቸው  የሚገቡ ናቸው፡፡ ይህ ሊሆን ካልቻለ የመድረክ ቀጣይ የመፍትሔ ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል ተብለው የተጠየቁት የፓርቲው አመራሮች እዚህ ላይ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡ ይህ በቀጣይነት በፓርቲው በሚደረግ ውይይት የሚወሰን ጉዳይ በመሆኑ ነውየሚል ምክንያት አቅርበዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በ ዲያስፖራዉ ደግሞ ከ ኢህኣዴግ ጋር የሽግግር መንግስት መስርቶ የነበረው ኦነግ ኣንጋፋ ኣባላት " ለ እዉነተኛ ፈዴራሊዝም" የሚታገል ኣዲስ ድርጅት ማቋቋማቸውን ይፋ ኣድረገዋል፡ ፡
በዚህ ኣዲስ ድርጅት ዉስጥ ለንጮ ለታን ጨምሮ በህገሪቷ ፖሊቲካ ትግል ታሪክ ታዋቂ የሆኑ የኦሮሞ ብሒር ትወላጆች ኣባላት ናቸው፡ ፡ 
ድርጅቱ ኢህኣዴግን ጨምሮ ከሌሎች ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ኣስታዉቋል፡ ፡

No comments: