የኣበሾች ሁሉ የኩራት ምንጭ
የኣክሱም ስርወ መንግስት በኣፍሪቃ ሰሜናዊ ምስራቅ የሚገኝ እጀግ ጠቃሚ
የንግድ ብሔር ነበር፡ ፡ ስርወ መንግስቱ በ300 ዓ.ዓ. ኣከባቢ ኣብቦ በ 300 ዓ.ም. ኣከባቢ ከፍተኛ የስልጣኔ
ድረጃ የደረሰ ስርወ መንግስት ነበር፡ ፡ ከሮማ ስርወ መንግስትና ከጥንታዊዋ ሕንድ ጋር የንግድ ግንኝነት የነበረው
ስርወ መንግስት የራሱ የመገበያያ ገንዘብ ነበረው፡ ፡ የኣክሱም ስርወ መንግስት በደቡባዊ የኩሽ ግዛት ላይ
የበላይነትን ይዞ የቆየ ከመሆኑም በላይ የኣረቡን የባሕር ሰላጤ በከፊል በፖሊቲካ መቆጣጠር የቻለ ስርወ መንግስት
ነበር፡ ፡
የኣክሱም ስርወ መንግስት በኣፍሪቃ ሰሜናዊ ምስራቅ የሚገኝ እጀግ ጠቃሚ የንግድ ብሔር ነበር፡ ፡ ስርወ
መንግስቱ በ300 ዓ.ዓ. ኣከባቢ ኣብቦ በ 300 ዓ.ም. ኣከባቢ ከፍተኛ የስልጣኔ ድረጃ የደረሰ ስርወ መንግስት
ነበር፡ ፡ ከሮማ ስርወ መንግስትና ከጥንታዊዋ ሕንድ ጋር የንግድ ግንኝነት የነበረው ስርወ መንግስት የራሱ
የመገበያያ ገንዘብ ነበረው፡ ፡ የኣክሱም ስርወ መንግስት በደቡባዊ የኩሽ ግዛት ላይ የበላይነትን ይዞ የቆየ
ከመሆኑም በላይ የኣረቡን የባሕር ሰላጤ በከፊል በፖሊቲካ መቆጣጠር የቻለ ስርወ መንግስት ነበር፡ ፡የሂምያ ስርወ መንግስት (የመን) ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ቆይቷል፡ ፡ ኣክሱም በዋናነት ኣይሁዳዊ ስርወ መንግስት ነበር፡ ፡ በ ስርወ መንግስቱ ስር የነበሩ ሊሎች ነገዶች ግን ከ ኣሃዱ ኣምላክ እምነት ዉጭ ብዝሃ ኣምላክነት መከተል ይችሉ ነበር፡ ፡ የኣክሱም ነገስታትየዘር ሓረግ ከንግስት ሳባ ከንጉስ ሰሎሞንና ከ ቀዳማዊ ምኒልክ የሚመዘዝ ነው፡ ፡ ኣክሱም በ ዳግማዊ ኤዛና ዘመን በ ዓለም የመጀመርያዋ ክርስትያናዊት ብሔር ሆነች፡ ፡ የ ኣክሱም መንግስት ከታላላቆቹ የ ፋርስ የሮም ክቻይና ስልጣኔ ጋር የሚስተካከል ስልጣኔ እንደነበረው ነብዩ ማኒ ኣስፍሮታል፡
በ 600-ዎቹ ሙስሊሞች በ መካ ከ ቑረይሲ ጎሳ ይደርስባቸው ከነበረዉ ጥቃት ለማምለጥ ተሰደው የተጠለሉበት ስርወ መንግስት ኣክሱም ነበር፡ ፡ ወደ ሃበሻ ምድር ስደት በ እስልምና ታሪክ የመጀመርያው "ሒጅራ" ተብሎ ይጠቀሳል፡ ፡ የኣክሱም ስርወ መንግስት ዋና ከተማ ኣክሱም ኣሁን በትግራይ ክልል የማእከላዊ ዞን ዋና ከተማ ነች፡ ፡
ኣክሱም ስለ ባሕረ ኤርትራ በሚያትተው ድንቁ መጽሓፍ ፐሪፕሉስ ማሪስ ኤሪትረኡ Periplus Maris Erythraei የዝሆን ጥርስ የሚገኝባት የንግድ እምብርት እንደሆነች ተጠቅሳለች፡ ፡ በዚህ መጽሓፍ በ 100 ዓ.ም. የኣክሱም ገዚዎች የነበሩት ሃጸይ ዞስካለስ ኣሁን በ ኤርትራ የሚገኙትን የቀይ ባሕር ወደቦች ኣዱሊስ (ምጽዋ ኣጠገብ) ኣቫሊተስ ( ኣሰብ) ይቆጣጠር እንደነበር ተጠቅሷል፡ ሃጸይ ዞስካለስ በ ግሪክ ሰነጽሑፍ የተካነ እንደንበር ይኸው መጽሓፍ ይገልጻል፡ ፡ ኣክሱም ስንል ግን መታወቅ ያለበት ኣሁንም 95 ፕርሰንት ኣካልዋ በ ኣሁንዋ የኣክሱም ከተማ ከርሰ ምድር ስር ተቀብሮ እንደሚገኝ ነው፡ ፡ የ ምዕራቡ ዓለም ተመራማሪዎች ከ ግብጽ ጋር ሲወዳደር ትኩረት ያልሰጡቷም ከከርሰ ምድሯ በላይ ለ ምስክርነት ያቆመችው 5 በመቶውን ብቻ ስለሆነ ነው፡ ፡ ፍትሓ ነገስትና ክብረ ነገስት በተባሉት መጽሕፎችዋ የተወሰነዉን ታሪክ ማስፈር በመቻሉ እስካለንበት ዘመን ድረስ የኣበሾች ሁሉ የኩራት ምንጭ ሆኗል፡ ፡ ወጣት ኣበሾት ከጥንታዊ ታሪካችሁ ትቁደሱ ዘንድም እነዚህ ድረገጾች እንድትጎበኙ ጋብዘናል፡
http://www.fordham.edu/halsall/ancient/periplus.asp
No comments:
Post a Comment