Sunday, June 7, 2015

እስረኛ ብሎገሮች ቁጥር ወደ መቶ 3 እየተጠጋ ነዉ.......




ዘላለም፣ኤዶም እና በሱፍቃድ በእስር ላይ ያሉ የቮይስ ስ ኦፍ ግሎባል ኮሚንት በኢትዮጵያ ፀሐፊዎች












“በየእስር ቤቱ ያሉ የድሬ ገፅ ወትዋቾች፣የሚዲያ ባለሙዮችና ጦማሪዎች የየሀገራቸዉ መንግስታት በአጭር ጊዜ ዉስጥ ከየማጎሪያዎቹ እንድፈቱልን በጥብቅ እናስገነዝባለን።”
250 ያልታሰሩ ነገር ግን ስጋት የከበባቸዉ የዓለማችን ድምፆች ማህበርሰብ አባላት

“ስለኢትዮጵያ የፖለቲካ ሐቅ በሀገሪቱ ዉስጥ እየኖሩ የፃፉት በሙሉ የመታሰር እድል ፋንታ ገጥሟቸዋል።’

ጦምዋሪ፣ደራሲ፣ገጣሚና ወትዋች   በሱፍቃድ ሐይሉ


“ጦማሪዎች ልማታዊ መሆን አለባቸዉ።”

የኢትዮጵያ ሚዲያዎች

“ጦሙን እያደረ ለምጦምር ሰዉ ምስጋናዉ ሸበ የሆነዉ ከመቼ ጀምሮ ነዉ?”

ኻዮሉማ/xayouluma


Saturday, June 6, 2015

የሩዋንዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነባሩ ፕሬዝዴንት ሶስተኛ ዙር የምወዳደሩበት የህገ መንግስት ጥሰት ለመፈፀም ተስማሙ።



"ይህ ህዝቤ ዉሳኔ የሩዋንዳ ህዝብ በራሱ መብት የመምረጥና የመወሰን መብቱን መጠቀሙን የምያሳይ አስተማሪ ዉሳነ ነው።"
ፓዉል ካጋሜ(የሩዋንዳ አርበኝች ግንባር ሊቀ መንበር )

"እኛ እንደፓርቲያችን ትናንቱኑ ለሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፕረዝዳንቱ ፈር የለቀቀ የስልጣን ጥማት የሀገሪቱ ህገ መንግስት አንቀፅ 101 የምጣረስ መሆኑን ጠቅሰን አመልክተናል።"
ፍራንክ ሀበንዛ(የአረንጓዴ ፓርቲ ፕሬዝዴንት ለ ኤ ኤፍ ፒ ከተናገሩት)

"የሃምሳ ሰባት አመቱ ፕሬዝዴንት የወሰኑት ዉሳነን ሊያጠኑት ይገባል።"
የአሜሪካ መንግስት

እንዴ እኝህ የአፍሪቃ መሪ ተብዬዎች ወንበር ላይ ከተቀመጡ መነሳት ያስጠላቸዋል ወይ?

ኻዮሉማ/xayouluma

Friday, June 5, 2015

ማህበራዊ ድሬ ገፆች ማህበራዊ ህይወታችን እያደናቀፉ ነዉ ?



ከቅርብ ጊዜ ወድህ የዓለማችን ወጣትና አዛዉንት ሳይቀሩ የርስ በርስ ግንኙነታቸዉን በየማህበራዊ ድሬ ገፁ አድርገዋል። 71 በመቶ ወጣት የፌስ ቡክ ደምበኛ ፣ 23 በመቶዉ የቲዊተር ተጠቃሚ ስሆን ቀሪዉ የተለያዩ ድሬ ገፆች አሳዳጅ ነዉ፤ እንደ ፐዉ የምርምር ማዕከል(Pew Research Center) ሪፖርት መሰረት። በነገራችን ላይ ማህበራዊ ድሬ ገፆች ማህበራዊ ህይወታችን እያቃወሱት ነው ስንል በጎ በጎ ጠቃሚ ጎኖቹን አልዘነጋናቸዉም።ዳሩ ግን የማህበራዊ ድሬ ገፆች በጤናችን ላይ የተወሰነ የድብርትና የመደበት ክስተቶችን ያስከትላሉ ለማለት ነዉ።

የፌስ ቡክ ፋንክ(በጥቁሮች ዘንድ የተለመደ ባህላዊ ዳንኪራ ነዉ)መሆን ይሻሉ?

ይህ የጥናት ዉጠት እንደት ማህበራዊ ድረ ገፆች የአኗኗር ሁኔታችን ይቀይራሉ ባከባቢያችን ላይ ያለዉንም የኑሮ ዘይበ ያስረሱናል ይላል።

ኻዮሉማ/xayouluma

በርግጥ ሁሉን የፈጠራ ዉጤቶች ላይ እምነት መጣል ተገቢ አይደለም !!

ዉርጃ

በመጀመርያዉ ሰኮንድ
የሆነ ፒንሳ የምነስል መቁረጫ ፊቷ በማትታይ ሴት ብልት ይገባል።በዓይነ የምታየኝ አንድ ፅንስ ለማስወረድ የተዘጋጀ የሴት ልጅ ብልት እና ትሉቁ ፅንስ ማጨናገፊያ፤ዓይነን ልጨፍን ፈልገ ነገር ግን መጨከን እንዳለብኝ ራሴን አሳመንኩ ምስለ ቀረፃ ቀጠለ
በኢየሱስ ስም !!!!
ብረቱ በሴትዬዋ እምስ ገባ
ዉ !!! የገባዉ ብረት የሆነ የተቀጣጠለ ነገር ስቦ አወጣ ቪዲዮዉ ደም በደም ሆነ...
መዓት የሰዉ ስጋ የማይመስሉ ነገሮችን አጨናጋፊዉ ሃኪም አወጣ...

ኻዮሉማ/xayouluma
በጌታ ስም !!
በሃያ ስምንተኛዉ ስኮንድ የሆነ ህፃን ልጅ እጅ አየሁ።
ወይነ የሰዉ ልጅ አንድህ ነበር እንደ የምፈጠረዉ? ወድያዉኑ የ'ኔን እጅ ተመለከትኩ አክሱምንና ላሊበላን ያነፁ እጆችንም አሰብኩ ሃኪም ተብየዉን ረገምኩት፤ረግመዉ ሳልቆይ የዶክርተሩን እጅ አየሁ ላመስግነዉ ወይስ ልርገመው ግራ ተጋባው
ምን ብከፋት ነው ሴትዬዋስ እንድህ የምታደርገው የማን ዉሳነ ይሁን
እያጨናገፉት ያለው አዶልፍ ሂትለር ይሁን?
አይ መሶሎኒ ይሆናል!

ሴተኛ አዳሪነት ህጋዊ ልሆን ይገባል


"አምስት መቶ ሴተኛ አዳሪዎች ጩሄታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ አሰሙ......"

"እኛ እንደማንኛዉ ዜጎች ሰርተን እንከፍላለን ስለዝክ ለምን መንግስት ከለላዉ በተለየ መልኩ ይጮቅነናል?"

"በርግጥ እኛ ስጋችን እየሸጥን መተዳደር ባንፈልግም ሰርተን እንዳንበላ ሁነታዎች አልተመቻቹልንም ለዝክ ነዉ እንደመንግስት ጉበኞች ሰርቀን ከምንበላ ሰርተን መብላት አማራጫችን አድርገናል!"

ኻዮሉማ/xayouluma

በባለፈው ወሬዬ እንድህ ብየ ነበር

የአቡጃ አከባቢ ጥበቃ ቢሮ ባለፉት ዘጠና ቀናት ዉስጥ በርከት ያሉ ለከተማችን ዉበት አያስፈልጉም በማለት ለእስር ዳረግናቸዉ ይለናል።
2,534 የጎዳና ተዳዳሪዎች
3000 ሴተኛ አዳሪዎች
102 ህገ ወጥ እንስ ሳት እና
6000 ለሎች ህገ ወጥ ተሽከርካሪዎች

http://nigeriacamera.net/3000-sex-workers-arrested-in-abuja/

Thursday, June 4, 2015

ስገባኝ



ከዉቅያኖሱ ታርክ ጠብታ ስደግምላችሁ ማን ነዉ የደነዘዘዉ ወደ ምለዉ እንሄዳለን።በታርክ መፅሐፍት የበላይነት የምንጠቅሳቸዉ ታሪኮች ምን ያህል አሳማኝ እንደሆኑ ስለምያምን ነዉ።አንድ ታሪክ በሶስት ሰዎች ተሰርቶ ይቆያል፤የመጀመሪያዉ ታሪክ ስሰራ፣ሁለተኛዉ ታሪክ ስያወራ፣ሶስተኛዉ በህይዎቱ ላይ ታሪክ ይሰራበታል።ዳሩ ከዝህ ቀደም እንደጠቀስኩት ሰዉዬዉ ታሪክ ላይ ታሪክ ይጨምራል አልያም ይቀንሳል።

ከክፍል ፪ የቀጠለ
ገፅ/ልጥፍ ፫

ኻዮሉማ/xayouluma

ዋቢዬ ፀሐፊ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደ ስላሴ 1921 ዓ/ም የፃፉትን መፅሐፍ ጠቅሶ በመፅሐፍ ፩ ገፅ 61-62 ባስቀመጠዉ ሰንጠረዥ በ5ኛ፣በ28ኛዉና በ29ኛዉ ተራ ቁጥር ላይ ኢትዮጵስ ፩ኛ ከ1856-1800 ቅ.ል.ክ. ለ56 ዓመታት፣አንጋቦስ ፩ኛ ከ1408-1350 ቅ.ል.ክ. እና ሚአሙር በ1358 ቅ.ል.ክ. ለ፪ ቀናት ብቻ ኢትዮጵያን በአጋዝያን ዘመን ገዝቶአቸዋል ብሎ ፅፏል።በገፅ 95-97 በሠፈረዉ ሠንጠረዥ 16 ኛ ተራ ቁጥር  ላይ 'አጭር የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ' ብለዉ የፃፉትን አለቃ ታዬን በማጣቀስ በ 665 ቅ.ል.ክ. ንጉስ ገስዮ ለ6 ሰዓታት ኢትዮጵያን እንደመሩ ይመሰክራል።
በእኝህ አራቱ የኢትዮጵያ ታላላቅ መንግስታት ላይ የምያደንቀዉ ያልታወቀና ያልተፃፈ ያልተነበበም አኩሪና ድንቅ ታሪክ ይኖራቸዋል። በ'ኔና በዋቢዬ ግምት ትላልቅ ታሪካዊ ክንዉኖችን አንዳከናወኑ እናምናለም።
ዛሬ ላይ ሁላችንም የታሪክ አንባቢ ከመሆን ለጥቀን ታሪክ የምንሰራበት ዘመን ላይ እንዳለን አምናለሁ አልያም ታሪክ ሳናዛንፍ መፃፍ ይጠበቅብናል። 515 ቶን ክብደት ይመዝናል ተብሎ  የምገመተዉና ባስገራሚነቱ በ1972 እ አ አ UNESCO የተመዘገበዉ የአክሱም ሀዉልትም የአንድ ወቅት የኛ ብጠዎቹ የሌት ጊዜያቸዉን በመቆጠብ ለትዉልድ አዉርሰዋል።ገድለ ላሊበላ ዘቅዱስ መድሐኒዓለም 1157-1197 የተገነባዉ ዉቅር አብያቴ ክርስትያናት በ20 ዓመት ዉስጥ የተጠናቀቀዉ የኢትዮጵያዊያን አኩሪ ትዉፊት ነዉ።ጎኑ ዛሬስ ትዉልዳችን ምን እየሰራ ነዉ የምለዉ ነዉ ዋናዉ ጥያቀዬ ።

Tuesday, June 2, 2015

መንግስት ግንቦት 16 ስራ ያስፈታቸዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ካሳ ልከፍልለት ይገባል!


እሁድ ግንቦት 16/2007 ዓ/ም ላይ በመንግስት አዋጅና ንግርት መሰረት የተወደደዉ የሀገሬ ህዝብ ስራ ለፈታበት ካሳ ልከፈለዉ ይገባል።
ኻዮሉማ/xayouluma

ኑሮ የዝሆን ክብደት ያክል የተጫነበት ህዝቤ ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት በሰልፍ ያባከነዉን የትግል ጊዜዉን የቆመረበት መንግስት ይህን 40 ሚሊየን ህዝብ ልክሰዉ ይገባል።አሃ ምርጫ ቦርድ 38 ሚሊየን መራጮችን ነበር የመዘገበዉ፤ይሁና የምርጫ ታዛቢዉ፣አጨብጫቢዉ፣ተወዳዳሪዉ( እነ ዶ/ር መራራን ጨምሮ)እና ዳኛዉ ባጠቃላይ ሁለት ሚሊየን አይሞላም?
ከጉሊቲ እስከ ጉልበት ሰራተኛ፣ከታካሚ እስከ አካሚ፣ከገዢ እስከ ተገዢ፣ከደላላ እስከ ደሀስፖራ፣ ከስደተኝ(በሀገር ዉስጥ የተሰደዱት)እስከ አሳዳጅ እና ሌሎች ብዙ ብዙ ሚሊየን ህዝብ ከተፈፀመበት ክህደት ጋር የምስተካከል ባይሆንም ተገቢ ካሳ ልከፍለዉ ይገባል ባይ ነኝ። መብቴ መሰለኝ
ኑሮ ሱሪ ባንገት ለሆነበት ዜጋ ካርድ ካልጣልክልኝ ወየዉልህ የተባለዉ ወገን በቴሌቪዥን፣በሬድዮ፣በጋዜጣ እና በየሞባይሉ የተደረጉ ቅስቀሳዎች ለኑሮ ግብዓታችን የጠብታ ያህል ባይጨምርም ለመምረጥ ተገደናል።ተወዳዳሪዎቹስ ብሆኑ ራሳቸዉንም የካዱ ባስመስለዉ ዉድድር የህዝብ ድምፅን እንደ አየር ሁኔታ የተተነበየዉ ፭ኛ ዙር ምርጫ በሰላም ተጠናቋል። የምገርመዉ ነገር  አወዳዳሪዉ፣ተወዳዳሪዉ፣ታዛቢዉና አሸናፊዉ ፓርቲ ለዉድድሩ ድምቀት የተጠቀማቸዉ ኢትዮጵያን ለራሳቸዉ እንኳን ከኢህአዴግ በላይ ቦታ የሌላቸዉ በማስመሰል የለጠፋቸዉ ዉጠቶች አስገርሞኛል።

Monday, May 25, 2015

ይድረስ ለኢትዮጵያ............

ዲዮጋን

ሰዉ ፍለጋ ከቤት ወጥቶ
እጅግ ብዙ ተንከራቶ
ተመለሰ ከቤቱ
ሰዉ ጠፍቶ ባገሪቱ።
                አዘርግ(2003 e.c)

ሌቱን ሙሉ ኣሰብኩ፣በጣም አሰብኩ፣ በመጨረሻም፣ከቤቴ ወጣሁ፣አዲስ አበባን በእግሬ እየኳተንኩ ቃኘዉ  አእምሮዬ ላይ የጥያቄ ክምር ተከማችቷል።መጠየቅ የምፈልገዉ ደግሞ ኢትዮጵያን ነዉ እናም ጀመርኩ.............

እኔማ ሰምቸ ነበር ይህች ኢትዮጵያ የምትባል ምድር እንኳን ለህዝቦችዋ በግዛትዋ የሚያልፍ አዉሮፕላኖች ይባረካሉ!

እኔማ ሰምቸ ነበር ዓለም ባንድ መሪ የምትመራበት ዘመን ይመጣል ! ያኔ በዓለም ላይ የበዛ ሰላም፣ የበዛ ጤና፣ የበዛ መተሳሰብ፣ የበዛ ፍቅር፣የበዛ አንድነት ይሆናል ጦርነት ፣ጥል ፣ጥላቻ ፣ዘረኝነት ፣ርሀብ ምቀኝነት ፣መነቋቆር  ይወገዳል!  ያ መሪ ደግሞ ከኢትዮጵያ ነዉ!

አስራ ሁለቱ አጋንንቶች ይዉረዱ



መጋቢት ፬ ቀን 1910 የሀገሬ ሰዉ የመንግስት ሹመኞች እንድወርዱለት ያቀረበዉ ጥያቀ በደጃዝማች ከበደ ተሰማ የታሪክ ማስታወሻ በተባለዉ መፅሐፋቸዉ የምከተለዉን ፅፈዋል።


ቃሉም ይህ ነዉ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ዓለም ፈጥሮ 12 ሐዋርያትን አገር ከፍሎ እንድያስተምሩ ያሰማራቸዉ ለመምሰል ላገሩና ለመንግስቱ ልማት በእዉነት እንድመሰክሩና እንድሰሩ 12ቱን ሚንስትሮች ደጉ ጌታችን አፄ ምንልክ መርጠዉ ቢሾሟቸዉ ለአገር ልማት ለህዝብ አንድነት በመምከር ፋንታ አንዱ ላንዱ ለየራሳቸዉ ጥቅም በመመልከት አገሩን አበላሹት እንጂ ለመንግስት የጠቀሙትና የሰሩለት ጉዳይ የለም።
12ቱ ሐዋሪያት በማየት የተሾሙት ሚንስትሮች 12 አጋንንት ስለሆኑብን እንድሻሩ እንፈልጋለን፤ለምሳሌ የሥራ ሚንስተሩ ተብሎ የተሾመዉ የራሱን ቤት ለመስራትና በቤት ላይ ቤት እየቀጠለ ወደ ሰማይ ለመዉጣት ይገሰግሳል።እንድሁም የገቢ ሚንስተር የተባለዉ የራሱን ሃብት ብቻ በማደራጀቱ ምንልክ ቤት ለግብር የምሆን መሰናዶ ታጥቶ ባለፈዉ ሰሞን ከርሱ ቤት ዱቀት ተግዞ ተሰናዳ። ይህ ምን ያሳያል ሁሉም የየራሱን ጥቅም ለማደራጀት መዘጋጀቱን ነዉ፤

ደጃዝማች ከበደ ተሰማ
በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሰ የህይወት ታርክ በምለዉ መጽሐፍ
ዮሐንስ አድማሱ ጽፎት ዶ/ር ዮናስ አድማሱ እንዳቀናበረዉ
አ አ ዩ አሳትሞት ኻዮሉማ/xayouluma እንዳስነበባችሁ
ከገጽ ፳ የተቀነጨበ

ይህ ጥያቀ ዛረስ አያስፈልግም ?

Sunday, May 24, 2015

ከFIFA በቀሰምነው የጎል ቴክኖሎጂ ምርጫዉን ታዝበናል.........!!!






"ተዉ የጀማል አባት እንዳይቆጭዎት ምልክትዎን ንብ ላይ ብያደርጉ ይሻሎታል!"

"ቆንጂዬ ምንነካሽ! ስያዩሽ እንድህ አትመስይም አንቺም ክህደት ትፈፅምያለሽ?"

"ማዘር አንድ X ያድርጉ ንቡን ልቆራርጡት ነዉ ያሰቡት? ምነዉ እርሶ ትልቅ ሰዉ አይደሉም ? አንደት አንድ ንብ ላይ ሶስት X ያኖራሉ ?"


ኻዮሉማ/xayouluma

"ከፊፋ በቀሰምነዉ የጎል ቴክኖሎጂ ምርጫዉን ታዝበናል።"

"እኔም ኮኒስ ዉስጥ ሆኘ የመታዘብ ተልዕኮዬን ተወጥቻለሁ።"

ዛሬ በሰፈራችን ሀይለኛ ጉድ የተባለለት ግጥሚያ ተስተናግዷል።ቅልጥ ያሌ ጫወታ ነበር ከኛ ቡድን ግርግርበቃኝካሊሲዉኮከብዋ በረኛችን አመዷ እና የጠብቀዉ ወንድም ጮርነ ሁሉ ሳምንቱም ሙሉ ስዘጋጁበት ከርመዋል።ጮርነ ትንሽ ከኔ ጋር ፀበኛ ስለነበር እኔ በግጥሚያዉ እንዳልገባ ያደረገዉ ከፍተኝ ጥረት ተሳክቶለታል።ከላይ ሰፈር ልጆች ቺንዲላስላስ ጠንበለልንፉቲሲሬግንቤ(ስሙን ቀስ ይጥራዉና ባለፈዉ በነሱ ሜዳ ስንጫወት ባደረገዉ ኮንጎ ጫማ ቅልጥመን ብሎኛል፤ዛሬማ ብሰለፍ ኖሮ ጉዱን አሳያለሁ ብዬ የታላቅ ወንድሜን ቦቲ ጫማ አድርገ ነበር የመጣሁት።)ሆነዉ በመለያቸዉ ላይ ስማቸዉን ፀፌዉ የጋሽ ሀይሌ ሜዳ ላይ ተሰብስበዋል።በነገራችሁ ላይ የጋሽ ሀይሌ ሜዳ በኛ ሰፈር የኳስ ተንታኞች አሊያን ዛሪና የምል ቅፅል ተሰጥቶት ነበር እኛ ግን ብዙም ስላልተመቸን ሜዳዉን የጋሽ ሀይሌ ሜዳ ብለን እንጠራዋለን።በዝህ ታላቅ የሰፈራችን ደርቢ ብዙ ተመልካች ይገኝል ተብሎ ይጠበቃል።ብያንስ ከ 20-34 ሰዉ ጫዋታዉን ለማዬት ትኬት እንደቆረጠ የጫዋታዉ ትኬት ቆራጭ ሲስኮ ነግራናለች። የ'ኛ ደጋፊዎች ስለ'ኛ እየዘመሩ ነዉ እንደምታዉቁት የነ ግንቤ ቡድን ልጆች ሁሉ እረኞችና የመደበኛ ትምህርታቸዉን እንኳ ባግባቡ ያልተማሩና ያቋረጡ ናቸዉ፤የኛዎቹ ሁሉም ግን የ ፫ኛ ፬ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸዉ።

Saturday, May 23, 2015

ምርጫዉ ተጭበርብሯል..............!!!




በደቡብ ምስራቅ አዲሳባ ስሟን በማልጠራት ብጠራትም እንኳን ማንም በማያዉቃት አንዲት በማደግ ላይ ያለች ሃገር አለች።ሀገሪቷ ከቅርብ ጊዜ ወድህ ባለሁለት አሃዝ እድገት ማስመዝገቧን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተሰሚነት ክፍ እያለ እየመጣላት እንደሆነ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ይናገራሉ።ሃገርቷ በመልካም አስተዳደርና በደሞክራሲ መሰረት ላይ ከነ አሜሪካና አዉሮጳ ሀገሮችም ጋር ስነፃፀር የተሻለ አፈፃፀም ታይቶባታል።ይህች በመልክዓ ምድር ያነሰች በዓለም ላይ የገዘፈች ሀገር አብዛኛው የሀገሪቷ ህዝብ የገቢ ምንጩ ወሬ በማዉራትና በማስወራት ላይ የተመሰረተ ነዉ። በዳታ ስሰላ 60 ከመቶ የአጠቃላይ ገቢዋ የምገኘዉ ወደ ዉጪ በምትልከዉ ወሬ ላይ ነዉ። የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ኻዮሉማ/xayouluma እንደምናገሩት ከሆነ የህዝቧ ወሬኛነትና ከመቸዉም ጊዜ በላይ ስላደገ ፈጣኑን የኢንፎርሜሽን መረብ በመዘርጋት ካለም አንደኛ ነች። ሀገሪቷ በተለያዩ ወሬ ብቻ በምያዘዋዉሩ ወሬኞች ብዛትም ካለም አንደኝ ነች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በአፍሪቃ አህጉርና በሌሎች ዓለማት በምገኙ መንግስታት ስር ብዙ ወሬ አቀባይ ዜጋዎቿን በማስቀጠር ካለም አንደኝ ነች።በየፖለቲካ ፓርቲዉ ፣ በየሀይማኖት ድርጅቱ፣ በየንግድ ማህበራቱ፣ በየሙያ ማህበራቱና በየመደቡ የተሰገሰጉት የዝህች አገር ነዋሪዎች በሰባቱም አህጉር በመበተን ወሬ በማፈትለክ ስራ ተጠበዋል።አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገሪቷ ለስራ ቦታ የለላት ሀገር ብሏትም እሷ ግን ገቢዋን አጠናክራ ጉዞዋን ቀጥላለች።በሌላ ሀገር ያሉ ዜጎቿ የሀገሪቱን መሪዎች አቋሜ ቢስ ብሉም እነሱም ካንዳንድ የፖለቲካ ካባዎች ስሞቁ ተስተዉሏል።
በዝህች ሀገር ነፃ ፍትሐዊ፣ወቅታዊና ታዓማንነት ያለዉ ምርጫ በየጊዘዉ ይደረጋል። ሀገሪቷ በምርጫ ላይ ባላት ተዓማንነት እነሂዉማንስ ርይት ዎች የመሳሰሉ ቀንደኛ ድርጅቶች ሁሉ ያምኗታል። እንደዉ አንደ በሆነ የፈረንጆች ዓመት ላይ 'ለምን የአሜሪካን ምርጫ አልታዘብም ?'ብላ ጠይቃም ነበር አሉ። የካርድ ቆጠራዉ በሙሉ በፕሬዝዳንቱ ምሪትና ምራቅ ስለምካሄድ የገዘፈ ታዓማንነት አግኝታለች። ታድያ በዝህ በያዝነዉ ዓመት ግን ከተለመደዉ ዉጪ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የምርጭ ማጭበርበር ክስተት ገጥሟታል። ምርጫዉ የተጭበረበረዉ ሆድ በተባለዉ ብሔራዊ ክልሏ ስሆን ክስተቱም እንድህ ነበር።

Thursday, May 21, 2015

መንግስት ያሰራቸዉ ኔትዎርኮች ይፈቱልን ?





"ለብሔራዊ ደህንነት ስባል መራጩ የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ እስክያልፍና ዉጠቱ እስክነገር ቡና እንዳይጠጣ።"
                   ኢፌዴሪ መንግስት

"አንዳንድ አልቧልተኞች ባልተፈቀደላቸዉ ቡና ቤቶች የሽብር ወሬን ስለምነዙና ሰላማዊዉን ህዝብ ስለምያሸብሩ የመንግስት ዉሳኔ ፓርቲያችን ተገቢ ነዉ ስል አምኖ በመቀበል እንደፓርቲ ተግብሯል።"
                 የኢህአዴግ አፌ ቀላጠ ሬድዋን ሁሴን

"መንግስት በህብረተሰቡ ላይ እያደረገ ያለዉ አምባገነናዊ ተፅዕኖ ፫ ሺ ዓመት ቡና የመጠጣት ባህላችን አያስቀረዉም።"
                   ኢንዢነር ይልቃል ጌትነት

"ኢህአዴግ ሰፊዉ ህዝብ ስለምርጫ መረጃ እንዳይለዋወጥ የወሰደዉ እርምጃ አግባብነት የጎደለዉ ቢሆንም የመንግስትን ዉሳኔ እንደፓርቲ በፀጋ ተቀብለናል።"
                 የቅንዥቱ አየለ ጫሚሶ

"ወያኔ አፋኝ ስርዓቱን ስር በሰደደ ህዝባዊ ጥላቻ ላይ በማድረግ በነፃነት የመናገር፣የመወያየትና ጎረበት ጠራርቶ ቡና የመጠጣትና የማማት ሰብዓዊ መብቱን የምጥሰዉን ልያቆም ይገባል።"
               የጉንቦት ፯ቱ ነጋ ብርሃኑ

"የኦሮሞ ህዝብና ሌላዉ የሃገርቱ ህዝብ ቡና ከጂማ ከተገኘበት ጊዘ ጀምሮ 'kotta buna dhuuge 'እየተባባለ ዛሬ የደረሰበትን ቡና በዘመናዊ መልክ የማፍላትና የመጠጣት መብቱ ለቦለቲካ ግብዓትነት በማሰብ ማቆም የለበትም።"
                  ዶር መራራ ጉዲና( ገነትን ያለማዕረገ አትጥርኝ ነበር ያላት)

Wednesday, May 20, 2015

አወዛጋቢዉ የካምፓስ ምርጫ


ከሰፊዉ የእንቅልፍ ጊዜዬ መስዋዕት በመክፈል ከመኝታዬ ተነስቸ ወደ አዳራሽ ገባሁ። ባዳራሹ የምርጫ ቦርድ ተወካይ ተማሪዎችና የተወሰኑ የምርጫ እንግዶች በየወንበሩ ተሰካክተዋል፤ አብዛኞቹ ዉቃቢ የነገራቸዉ ይመስል በስፍራዉ ዝር አላሉም።እኔም የመጀመሪያዬ ስለነበር ጓጉቼ ከዝክ ቀደም እናት አባቴ የወሰዱትን የቅድሜ ምርጫ ስርዓቴ ሂደት ተከታትዬ አዉራ ጣቴን ለሰማያዊ ጂቢ አሰናድቸ ወንበር ሳብኩኝ።
የኮለጁ የምርጫ ቦርድ ተወካይ ተማሪ ስለምርጫ ብዙ ያወራል።ሌላዉ በዝምታና በግርምት ይሰማል።እኔም በዕለተ ሰንበቱ የምመርጠዉን ፓርቲ እያሰብኩ ተፎካካሪዎቹን እያነፃፀርኩ ነዉ፤ በኔ የምርጫ ክልል የምፎካከሩት አንድ ጠሚንስተር፣ አንድ አርሶ አደርና አንድ የባህል ሙዚቃ ቡድን መሪ ይፎካከራሉ። በነሱ የግል ብቃት ሳልገታ በፓርቲያቸዉ አቋምና አመለካከት የተወዳዳሪዎቹ ምስል እስክለጠፍ እየተጠባበኩ ነዉ።
የምርጫ ሁኔታዉ አዲስና ለገዥዉ ፓርቲ ግብዓት እንድሆን ከታሰቡት የምርጫ ክልሎች ዉስጥ የዩኒቬርሲስቲ የምርጫ ክልል፣ የታላላቅ ፕሮጀክቶች ምርጫ ክልልና ሌሎች አዳዲስ ኢህአዴጋዊ ታክትኮችንም አካቷል። ታድያላችሁ በዩኒቬርስቲ ደረጃ ባንድ ካምፓስ ብያንስ ፩ የምርጫ ጣቢያ ይኖራል ከበዛም በየ፯ መቶ ተማሪ ብዛት የተለያየ ጣብያ ይኖራል ተባልን ከዝያም ለጥቆ ለምሳሌ ያድሳባ ዩኒቬርስቲ 14 ቅርንጫፎችና ኮለጆች ስላሉት በየኮለጁና በየግቢዉ እንደየተማሪዉ ብዛት ይለያያል ተማሪ በብዛበት በ፮ ኪሎ ካምፓስ የምርጫ ጣቢያዎቹ እንደፌደራሉ ምርጫ ክልሎች የተከፋፈሉ ስሆኑ አነስተኛ ተማሪ ባለበት የምርጫ ጣቢያዉ እንደፌደራሉ የምርጫ ቦርድ ያስፈፅማል። ይህ ስተነተን ከላይ የጠቀስኳቸዉ ሶስቱ ዕጩዎች ሳይገለጹ ለፌደራሉ ም/ቤት የምወዳደሩ 25 ፓርቲዎች ስማቸዉ ይለጠፋል ከዝያ ባለፈ የእያንዳንዱ ምርጫ እጩዎች አይለጠፍም ማለት ነዉ።
ምኑ ነዉ ያወዛገበህ አትሉኝም
ያወዛገበኝማ በኛ የምርጭ ጣቢያ ተማሪዉ የፈለገዉን ፓርቲ ብመርጥ ዉጠቱ ወደ ዋናዉ ጣቢያ ክልል አይሄድም፤ ወደ ዋናዉ ጣቢያ የምሄደዉ የምርጫ ቦርዱ ራሱ አዲስ በምያዘጋጀዉ ቅፅ ላይ የተሞላዉ መረጃ ነዉ። ይህ ማለት በኔ አረዳድ ተማሪዉና የግቢዉ ማህበረሰብ የምጥለዉ ካርድ ለይሱሙላ ይቀመጣል(ለ ኤግዝብሽን ይሆናል እንዴምርጫ ጣቢያችን የቦርድ ተወካይ አገላለፅ)ስለዝክ ተማሪ የምጥለዉ ካርድ በና ግቢ ምርጫ ጣቢያ መሰረት ከዜሮ በታች ክብደት ያዘለ ወረቀት እንጅ ድምፅ አይደለም።
ይህች የምርጫ መላኛዉ ዉጥን ከተሳትፎ የዘለለ ምንም ፈይዳ የለዉም ማለት አትመስላች ሁም
ታዛቢዎቻችንም በስሜ ገለልተኛ በጎ መልዕክተኛ ማህበር ስም እየተቀያየሩ ይመጡብናል። ይመስገን በኛ ግቢ ግን ምንም አይታሰብም የምታዘበንና እዉነቱን የምገልጥልን የሰራዊ ጌታ የሰማዩ ንጉስ የሰማያዊ ርስት ባለቤት እግዝአብሄር ብቻ ነዉ።

ኻዮሉማ/xayouluma

የሰማያዊ ነገር


ልጅ ሆኘ ህፃን ሳለሁ የዓመት በዓል በመጣ ቁጥር ካባቴ ጋር ሙግት ገጥማለሁ። የሙግቴ መነሻ የኔ ምርጫና ያባቴ ምርጫ ነበር። አባቴ በተፈጥሮዉ ድያብሎስ ስመርቀዉ የኔን ምርጫ ይጠላል። በየእንቁጣጣሹ ሰማያዊ ፋንት በ፲ ብር፣ሰማያዊ ካልሲ በ ፲ብር፣ ሰማያዊ ጫማ በ፶ ብር፣ ሰማያዊ ሱሪ 45 ብር ፣ ሰማያዊ ሸሚዝ በ37 ብር ፣ ሰማያዊ መነፅር በ 12 ብር፣ ሰማያዊ ኮፊያ በ22 ብር፣ ሰማያዊ ሻማ በ ፶ ሳንቲም፣ ሰማያዊ ፊኛ እና ት/ቤት ስሄድ ከፀሃይና ከሰቆቃ የምታደገኝን ሰማያዊ ዣንጥላ በ17 ብር ይገዛልኝ ነበር።

ጥሎበት ያባቴ ምርጫ ሰማያዊ ባይሆንም ከብጫና መሰሎቹ ይሻለኛል ብየ ነበር የምያለቅሰዉ። አድገም ት/ት ስጀምር በት/ቤት ዉስጥ ከሰማያዊ እስክሪብቶ ሌላ ተጠቅሜ አላዉቅም።መምህራችን

"ኻዮሉማ/xayouluma ላንዳንድ ጠቃሚ ማስታወሻዎች ቀይ እስክሪብቶ ተጠቅም "

ብለኝም እኔም እንደ ሪዮት ዓለም ቀይ እስክሪብቶ ፈራለሁ።

Tuesday, May 19, 2015

በቀን ሶስተ እየበላሁ ነዉ።




"ባቢ ና ግባ ቁርህን በልተህ በምሳ ዕቃ ያስቀመጥኩልህን ይዘክ ት/ቤት አትሄድም?"   እናቴ ነች

"እምቢዮ አልበላም ደግሞም ምሳ ዕቃዬ ዉስጥ እንደትናንቱ የእንቁላል ጥብስ ከጨመርሽ አልወስድልሽም እምቢዮ ትናንት የነ አቡላ ሰፈር ልጆች ተሰብስበዉ ስቀዉብኛል የናንተ ቤት ቄረ ነዉ እንዴ ሁልጊዜ የስጋ ወጥ የምታመጣዉ ብለዉኛል አልፈልግም ከዛሬ ወዲያ ስጋ፣ እንቁላልና አይብ አልበላም "   እኔ ት/ቤት ከመሄደ በፊት ከናቴ ጋር እየተከራከርኩ

"በቃ ትቸዋለሁ ከዛሬ ጀምሮ ምንም የበግ ስጋ አላበላህም  ሃኪምም የፍየል ስጋ እንዳትበላ ብሎሃል አይደል ልጄ? " ጉምጨን እየሳመችኝ ለማማባበል እየቃጣት በሌላ ዕቃ ትንሽ ፒዛና ብዙ በርገር አረገችልኝ በምሳ ዕቃዬ ዉስጥ

"እምቢ!! እምቢ!! እሱን ከሰጠሽኝ ከማይክ ጋር ነዉ የምበላዉ"

ማይክ ዉድ ዉሻዬ ነዉ። ማይክ ከምንም በላይ በርገር ነዉ የምወደዉ።
"ባቢዬ ለዛሬ ብቻ ነገ በጠዋቱ የምትወደዉን ጣፋጭ ነገር አመጣልሃለሁ "  እናቴ።

ስገባኝ

ድንዛዘ በወሬ
ያለጥቅም ያለፍሬ
ድንዛዘ በጭፈራ
ያለ ዓላማ ያለስራ
ድንዛዘ በከተማ
ሰዉ የሰዉን ብቻ እየሰማ
እንፎርሜሽን ጠዋት ማታ
አዕምሮዉን ፈታ ፈታ
(xayouluma)
ከክፍል ፩ የቀጠለ
ገፅ/ልጥፍ ፪

ባለመፅሃፌ ጋዘጠኛ ስናገር አዳም የመጀመሪያዉ ኢትዮጵያዊ መሪ መሆኑን ሳይቃወም የራሱን ሃሳብ ግን የራሱን ሃሳብ በኖህ መሪነት ላይ ያተኩራል። እኔን የምጨንቀኝ አዳም ሆነ ኖህ ቅደም ተከተሉ አያስጨንቀኝም፤ እነኝህ ኢትዮጵያዊያን በዘመናቸዉና በህይወት ተዋረዳቸዉ ለሀገሬ ምን አበረከቱ የምለዉ ነዉ። ይህን ስላች ሁ የጥንታዊ ታሪክ ፈልፋይ እንዳልመስላችሁ በርግጥ እንደማልሆንም አዉቃለሁ ጎኑ ግን የዘመኑ ትዉልድ አባል እና የቤተሰቦቼ የቦርድ ሰብሳቢ ነኝና በዘመን ታሪካችን ምን እንስራ ጉዳይን አንስቶ መጫርና መፈርፈር ነዉ።

Thursday, May 14, 2015

ስገባኝ

 ልጥፍ/ገፅ ፩

xayouluma

ጊዜ በዘመን ባለስትራነት ላይ የተገጠመ ተሽከርካሪ ጎማ ነዉ።የሰከንድ ስነ ተዋልዶ ዑደት በተገቢዉ መጥን እየተፀነሰ ከምጠበቀዉ በላይ እየተራባ ደቂቃ ሰዓት ቀን እያለ የልጅ ልጆችን እየተተካ የዘመን የዘር መነሻ ሆኖ ያገለግላል። ተሽከርካሪ ጎማ የምድርን ህዋስ ከቀኝ በግራ ከፊት በኋላ እያዋዛ ዛረ ላይ የምድርን ልብ በመቆጣጠር የደም ዝዉዉሯን ተቆጣጥሮ ሰንበት ብሏል።የዝህችኛዋንና የምትመጣዋን ዓለም የደም ዝዉዉር የምመራዉ በጊዘ ተሽከርካሪነት ላይ በመነጨ ጎማዊ ደም መሆኑ ሳይታመን ያለጥርጥር የምንቀበለዉ የመካኒክና የስነ ህይወት ፈለግ ነዉ።
ከዝህ ተሽከርካሪ ቅፅበት( ሰከንድ)በዘመን ላይ የምያኖረዉ ታርካዊ አሻራ በየዕለቱ እየተመዘገበ በፈጣሪ ቤቴ መዛግብት በመረጃ ደስክ መላዕክት እንደምቀመጥ አያጠራጥርም የፅህፈት አሰፋፈሩ በሁለት መልኩ ነዉ የመጀመሪያዉ ፈጣሪ በዝህች ምድር የምያከናወነዉ ሁሉ ሰማይና ምድር ከመፈጠሩ በፊት የተፃፈና ሁሉ በርሱ እንደምሆን በመፅሀፍ ቅዱስ አስፍሮልናል ሁለተኛዉ አሰራር እግዝአብሔር ከፈቀደላቸዉ መንገድ ዉጪ እንደ ራሳቸዉ ፍላጎት የምኖሩትን ፍጥረታት ያኗኗር ዑደት በማስተዋል በሁለት መንገድ ባንድ መዝገብ ይመዘግባል። የምናነሳዉ ዋናዉ ነጥብ በዝህ ግዙፍ ዓለም የእያንዳንዱ ፍጥረት እንቅስቃሴና ትግበራ ካለን ጊዜ አንፃር ስንመለከት ዓለም ከጊዜዉ ጋር ባንድ ፍጥነት ለመገስገስ ተስኗታል። የኛም ምድር ካሉን ተቀሪ ሳይንሳዊ ዓለማት አንፃር ስስተያይ በተሻለ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች ብሎ መገመት በህግና በህሊና አያስጠይቅም። በነዝ ህ ሰባቱ አህጉራት አሁን ከምንፀባረቁ አዕምሮአዊ ምጥቀት በተጨማሪ በየወቅቱ የምጎበኙን አስደናቂና አሳቃቂ የተፈጥሮ አደጋዎቹም አይዘነጋም።አይስተዋሉምም። ጉዱ ግን ማን ነው ጊዘን ባግባቡ እየተጥቀመ ያለዉ ብለን ሰዉን መጠየቅ አለብን።

"አልበዛም ወይ  መፋዘዙ ነቃ በሉ
አልበዛም ወይ  ማንቀላፋት
ሀላፊነትን መዘንጋት
አልበዛም ወይ ግድ ማጣት
ሀላፊነትን መዘንጋት .........."

ፀሬ አጨብጫቢ ኬምካል ያላችሁ ድረሱልን?


.
.
.
.
ባሳለፍነዉ ነባርዊ ሁነታ እያንዳንዳችን ቤት የተለያዩ ተባዮችን በፀሬ ተባይ ማጥፊያ፣ አረሞችን በፀሬ አረም ማጥፊያ፣ አደናጋሪዎችን በፀሬ አደናጋሪ ኬምካል በመርጨት ከወባ ትንኝና ከቱሃን ጋር እነ DDTን እነ ሮች killer ን ተጠቅመን አጥፍተናል። ያሁኑ ግን አቅቶናል። ልወረን ነዉ።









ኡ የሀበሻ ልጅ ስማ የሰማ ላልገባዉ ያስረዳ ያልሰማ የሰማን ይጠይቃ !!




ኡ አጨብጫቢና አኮብኳቢ መቆምያ ልያሳጣን ነው።
በየስርቻዉ በየጥጋጥጉ ያሉ የጥቅም አሳዳጆች ቀልባችን ልጠፉ ነው።ካልመረጣችሁን ካመረጣችሁን እየተባልን ነዉ።እኛ ስንቴ እንምረጣችሁ ባለፈዉ ለምርጫዉ አራት ሳምንት ስቀረዉ በየቀበለዉ ቅፅ ፎርም ላይ ፓርቲያችሁን እህአዴግን ከመረጥን ይሄዉ ሁለት ሳምን ከምናምን አለፈን። ኧረ ተዉን ፈጣሪን ፍሩት እኛም እንደናንተዉ ሴዎች ነን ጥቅም እንፈልጋለን የምንፈልገዉ ጥቅም ግን ህዝባዊ ጥቅም ነዉ። ጥቅቱን ተጠቃሞ አብላጫዉ የምጎዳበትን ቀመር አንፈልግም።በቃ ሰምታችኋል..................

Wednesday, May 13, 2015

ንድፍ ነበር ያልሽኝ?

ንድፍ ነበር ያልሽኝ?
አሁን ነዉ የገባኝ ቀድሞ መታነጹ
ላንች ተጠቦልሽ በእጆቹ መቅረጹ
ምንም ንድፍ ብሆን ብዙም የማልረባ
ካንች ዑደት ህይዎት ከቁብ ከማይገባ
ከዛች ትርፍ ጎነ አንችን የመቅረጹ
አሁን ነው የገባኝ ቀድሞ መታነጹ

ካንች ለላ መቶ ስድስት አሉ
በሱ ተማምነዉ ከኔ የተጠለሉ
ባይሆን ንድፏ አንች ነሽ
ለተጠለሉብኝ ጎኖቸ ናሙና የሆንሽ
ከኔ ዘንድ ፻፮ አንችዎች አሉ
መጠጊያ በማጣት ከኔ የተጠለሉ።
ባይሆን ንድፏ አንች ነሽ
የምረን አንች ነሽ
ለተጠለሉብኝ ናሙናቸዉ የሆንሽ።
ኻዮሉማ/xayouluma
may 2015

እጠጣዋለሁ



መጠጥን ጎጅ ነዉ አትበሉኝ
መረነ ቢስ ምክራችሁን በከንቱ አትለግሱኝ
ጠጥቸ ነዉ ሁሉን የረሳሁት
ጨልጨ ነዉ መከራዬን ያለፍኩት
ባልጠጣ ኖሮ የትናንቱን ረሃብ እንዴት እረሳለሁ?
የዛሬንስ ጥጋብ በምን አከስማለሁ?

አልኮል ነዉ አትበሉኝ
መርዝ ነው አትበሉኝ
ገዳይ ነዉ አትበሉኝ

ጠዋት ማታ ባልጠጣ እንደት እኖራለሁ
እሷን ባልጨጣት በምን እከርማለሁ