Tuesday, April 2, 2013

ሽብርተኞች ይፈለጋሉ!!

የኣሜሪካ ፌደራል የምርመራ ቢሮ ሁለት የኣሜረካ ዜጎች የኣሸባሪው ኣልሸባብ ኣባላት ጠቁሞ ላስያዘ 10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደሚሰጥ ኣስታወቀ፡ ፡ ኣልሸባብ የጎረቤት ኣገራችንን ማዕከላዊና ደቡባዊ ክፍል ተቆጣጥሮ ከ 2008 ጀምሮ ተከታታይ ጥቃቶችን የፈጸመ ኣሸባሪ ድርጅት ነው፡ ፡ኣልሸባብ በኣሜሪካም በኢትዮጵያም እንደ ኣሸባሪ ድርጅት በይፋ የተፈረጀ ብቸኛ ሶማሊያዊ ድርጅት ነው፡ ፡
ሁለቱ ኣሜካውያን ተፈላጊ ኣሸባሪዎች ጀሃድ ሙስጦፋና ዑመር ሓማሚ ናቸው፡ ፡

የምርመራ ቢሮው ሁለቱም ኣሁንም ሶማሊያ እንደሚገኙ ያምናል፡ ፡ 
ባለ ሰማያዊ ዓይን ቀለም ተፈላጊዎቹ በዜግነት ኣሜሪካውያ ሲሆኑ 1 በካሊፎርንያ የሳንዲየጎ ኗሪ ነበር፡ ፡

እንደ ፌደራል የምርመራ ቢሮው መግለጫ ከሆነ ጀሃድ ወደ ሶማሊያ የተጓዘው በ 2005 ነው፡ ፡ ኣሜሪካዊው በኣሸባሪ ድርጅቱ ዉስጥ በ ሚድያ ኣማካሪነት ከማገልገሉም በላይ የ ኣሸባሪው ድርጅት የዉጭ ኣገር ኣባላት ኣስተባባሪም ነው፡ ፡ ኣሸባሪው ጀሃድ ሙስጦፋ ከ 2009 ጀምሮ ኣሸባሪዎችን በ ስንቅና በትጥቅ እየደገፈ ሽብርተኛ እቅዶችን ነድፎ በመተግበር ተጠርጥሮ ሲፈለግ ቆይቷል፡ ፡ ሁለት የትዉልድ ዓምት በመጠቀምና ኣሕመድ ጉረይ ፡ኣንዋር ኣልምርኪ፡ ኣሚር ኣንዋር በሚሉ ስሞች እንደሚንቀሳቀስ ይታወቃ፡ ፡ የ ዓይን ቀለሙ ሰማያዊ የሆነው ጀሃድ ሙስጦፋ ቡናዊ የጸጉር ቀለም ጢማም መነጽር የሚጠቀምና በቀጭ እጁ ልዩ ምልክት ጠባሳ በ ግራ ጠቋሚ ጣቱ መጠነኛ ጉዳት የደረሰበት እንደሆነ ቢሮው ባወጣው መግለጫ ሰፍሯል፡ ፡ ሙስጥፋ በኤኮኖሚክስ የባችለር ዲግሪ ያለውና ኣረብኛ ሶማሊኛና እንግሊዝኛ ኣሳምሮ የሚናገር ነው፡ ፡ ኤፍ.ቢ. ኣይ  ጀሃድ ሙስጦፋ የመን ኢትዮጵያ ወይንም ከንያ ሊጎበኝ እንደሚችል ሳይጠቅስ ኣላለፈም፡ ፡
.
ሓማሚም ኣሜሪካዊ ዜጋ ነው፡ ፡ በኣለባም ደፍነ ኗሪ ነበር፡ ፡ እናቱ ክርስትያን ኣባቱ ደግሞ ሙስሊም ሶርያዉያን ናቸው፡ ፡ ሶማሊያ የገባዉ በ 2006 ሲሆን በሙስሊም ኣክራሪዎቹ ስልጠና ተሰጥቶታል፡ ፡ የኣልሸባብን ፕሮፓጋንዳ ከማሰራጨቱ ባሻገር ወጣት እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሽብርተኞችን ለመመልመልም የተክስት የ ሲዲና የ ቪድዮ ክሊፖችን በመጠቀም ኣወናብዶ ለሽብር ድርጊት ሲያሰመራ ቆይቷል፡ ፡

No comments: