እ ጎ አ በ 1875፣ የድምጽ ሞገድ በሽቦ ወደ ኤሌክትሪክ ሞገድ ተለውጦ እንዲተላለፍና ፤ ምልክቱ፤ በድምፅ ፤
በቃላት እንዲሰማ ያበቃውን ፤ ስልክ የተባለውን መሣሪያ ፣አለክሳንደር ግርሃም ቤል ከሠራ ወዲህ፤እ ጎ አ በ 1876
በተሽከርካሪ « ዲስክ»
እ ጎ አ በ 1875፣ የድምጽ ሞገድ በሽቦ ወደ ኤሌክትሪክ ሞገድ ተለውጦ እንዲተላለፍና ፤ ምልክቱ፤
በድምፅ ፤ በቃላት እንዲሰማ ያበቃውን ፤ ስልክ የተባለውን መሣሪያ ፣አለክሳንደር ግርሃም ቤል ከሠራ ወዲህ፤እ ጎ አ
በ 1876 በተሽከርካሪ « ዲስክ» ላይ በኤሌክትሪክ ርዳታ፣ ምስል ማሳየት እንደሚቻል ጀርመናዊው Paul
Gottlieb Nipkow ካሳወቀና እስኮትላንዳዊው ጆን ሎጊ ቤርድ፣ ራሱ በተናጠል ባካሄደው ተመሳሳይ ምርምር
የቴሌቭዥንን ምሥጢር ለህዝብ ካሳዬ በኋላ፣በሩሲያዊ አሜሪካዊው ቭላዲሚር ዝቮሪኪን ፣ እ ጎ በ 1933 ኛዎቹ ዓመታት
፤ በ 1940ኛዎቹ ዓመታት ይበልጥ እስኪሻሻል ድረስ፤ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች እንዲሠራጩ ለማድረግ ማብቃቱ
ተረጋገጠ። በኋላም እንደገና BAIRD ባለቀለም ምስሎችን በቴሌቭዥን ማሠራጨት የሚቻልበትን አብነት አግኝቶ ማሠራጨት
እንደሚቻል ካመላከበት ዘመን አንስቶ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ በመስታውት ሣጥን የሚታይበት አስደናቂ የሥነ ቴክኒክ ግኝት በዓለም ውስጥ መዛመቱ አልቀረም። ከዚያም የኮምፒዩተር ዘመን ከተተካ በኋላ፤ ውሎ አድሮ ፤ መዳፍ በሚያክል የሥነ ቴክኒክ ውጤት ያለሽቦ ድምጽንም ምስልንም የሚያቀብሉም የሚያሠራጩም መሣሪያዎች ቀርበዋል።