Monday, March 11, 2013

የጡቶችሽ እንባ



እንጭጭ ሳሉ ጡት የምጠቡ
                    ወተት የምመገቡ
ካደጉ በኃላ አጥንት በቅልጥሙ
 ቆረጣጥመዉ ሀገርን ስያለሙ

ዛሬ ላይ:-

ባንጃ ተከፋፍለዉ በመቅደስ የገቡ
አቅም ልያሳጡን በመጋብነት የምመግቡ
ወተትሽን ጠጥተዉ ለኛ እንባሽን አጠቡ።

ያም ሆኖ:-

በጡቶችሽ የወርደዉ እንባ
ልቤን እያባባ
ባፌ እየገባ
እንጀራ ከሆነልኝ አድስ ዘመን ጠባ።



የመከራሽ እንባ
በጡት ሽ ሰገባ
ዛሬም እየነባ
አካለን ገነባ።

እማዬ:-

ስቆቃ በዝቶብሽ
ሁለ እያስጨነቀሽ
አይንሽ ፍም ሆኖብሽ
ተወጥሮ ጡት ሽ
ሟሽቆብሽ ተክለ ስጋሽ
የሉሲ እህት መስለሽ
ባደባባይ ቆመሽ
ዘወትር መማጸንሽ
ለማን ነዉ ልፋትሽ?
ይህ ሁሉ ድካምሽ።

ላፍርቃዊዉ ላዉሮጳዊዉ
ለኢስያዊዉ ለምስራቅ ምራባዊዉ
በናትነት ፍቅር ቆመሽ ምታጠብዉ
ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ወይስ
                ለዝያ ለመጋቢዉ
               ወተት ሽን በእንባ ለቀየረዉ ......................?
                                                 xayouluma

No comments: