መስፍን ወልደማርያም
በበጎ ስራቸው "ኢትዮዽያዊው ዮሴፍ" የሚል ቅጽል ስም ያተረፉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም.
በአዲስ አበባ ተወለዱ። በልጅነታቸው የቤተክርስትያን ትምህርት በመከታተል ድቁናን ተቀብለዋል። በተፈሪ መኮንን
የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለው በ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. በጥሩ ውጤት በማጠናቀቅ በጊዜው የላቀ ውጤት
ላመጡ ተማሪዎች የሚሰጠውን የውጪ አገር የትምህርት እድል አሸንፈው ወደ ህንድ አገር በመሄድ የመጀመሪያ
ዲግሪያቸውን ከፑንጃብ[Punjab] ዩኒቨርሲቲ በ፲፱፻፵፭ ዓ.ም. እንዲሁም አሜሪካን አገር ከሚገኘው ክላርክ
[Clark] ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዴግሪያቸውን በ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. ተቀብለዋል።
መስፍን የውጪ አገር ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ወደሀገራቸው ከተመለሱ በሗላ በቀድሞው "ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ" ያሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ፲፬ አመታት ከ፲፱፻፶፩ እስከ ፲፱፻፷፭ ዓ.ም በመምህርነት እንዲሁም የጂኦግራፊ ትምህርት ክፍል ዋና ሀላፊ በመሆን ሠርተዋል። በ፲፱፻፸ዎቹ መጀመሪያ በድጋሚ ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመልሰው ለረጅም አመታት በጡረታ እስከተገለሉበት ጊዜ ድረስ በዩኒቨርሲቲው በመምህርነት አገልግለዋል።
በረዥም ጊዜ የአካዳሚክ ህይወታቸው በርከት ያሉ ጥናታዊ ጽሑፎችን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ጦማር/መጻሕፍት አሳትመዋል ጂኦግራፊ፣ኢኮኖሚ፣ታሪክ፣ፖለቲካ፣ ድርቅና ረሀብ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥበቃን በተመለከተ ምሁራዊ ሃሳባቸውን በመጽሐፎቻቸው እንዲሁም በየግዜው በተለያዩ መጽሔት እና ጋዜጦች ላይ በሚጽፏቸው መጣጥፎች ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር በተጋባዥነት በተሳተፉባቸው በተለያዩ አለምአቀፍ ጉባኤዎች ኢትዮዽያን በተመለከተ ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሁፎችን በማቅረብ ያላቸውን ፍልስፍና፣ ሃሳብና፣ አመለካከት በሰፊው አካፍለዋል።
ፕሮፌሰር የስነግጥም ተሰጥኦም እንዳላቸው በ፲፱፻፷፯ ዓ.ም ያሳተሙት ከ፴ በላይ ግጥሞችን ያካተተችው "እንጉርጉሮ" የተሰኘችው የግጥም መድብል ምስክር ሆናለች። እንጉርጉሮ የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮችን ተከትሎ በጊዜው ያቆጠቆጠውን የሞራል ውድቀት እያነሳች የአንባቢን ህሊና አጣብቂኝ ውስጥ ከታ ትኮረኩራለች።
ከብዙ በጥቂቱ ፕሮፌሰር መስፍን በእንግሊዘኛ ካሳተሞቸው መጻሕፍት The horn of Africa : conflict and poverty 1999, Somalia : the problem child of Africa 1977, Suffering under Gods environment 1991 ይጠቀሳሉ በአማርኛ "አገቱኒ ተምረን ወጣን"፣ "ሥልጣን ባህልና አገዛዝ ፖለቲካና ምርጫ"፣ እንዲሁም በቅርቡ ያሳተሙት "አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ"፣ ይገኙባቸዋል።
ፕሮፌሰርን ከሌሎች ኢትዮዽያውያን ምሁራን ልዩ የሚያደርጋቸው አስቸጋሪ ጊዜዎችን ሁሉ በመቋቋም ከሀገራቸው ሳይወጡ እድሜያቸውን ሙሉ ያላቸውን እውቀት፣ሀሳብና ምክር ለማካፈል አለመሰልቸታቸው ነው። በአሁኑም ወቅት በአዲሱ ትውልድ ጭምር ተወዳጅና አራያነታቸው ቀጥሏል። ከፍተኛ ተሰሚነት ካላቸው ኢትዮዽያ በ፷ አመት ውስት ካፈራቻቸው ምሁራን ውስጥ ግንባር ቀደሙን ስፍራ ይይዛሉ።

No comments:
Post a Comment