የአውሮፓ ህብረት ልኡካን ቡድን የኢትዮጵያን አደጋ የመከላከል እና የመቋቋም ስኬታማ ልምዶች በመስክ ለመመልከትና ለመቀመር በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረገ ነው::
ልኡካን ቡድኑ ኢትዮጵያ ድርቅን ተከትሎ የሚመጡ ተጋላጭነቶችን በመቋቋም ረገድ እያሳየች ያለችውን ሁነኛ መሻሻል ይገመግማል፣ በህብረቱ እየተረቀቁ ያሉ ፖሊሲዎችንም የማካተት እቅድ ይዟል::
የአደጋ መከላከል ስራውን ከዘላቂ የልማት ስራዎች ጋር በማስተሳሰር ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦቸን ዘላቂ በሆነ መልኩ ማደላደል የሚቻልበትን አማራጭ መገምገምም የጉብኝቱ አብይ አላማ እንደሆነም ተገልጿል::
የልኡካን
ቡድኑ በአዲስ አበባ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ሀገሪቱ ላለፉት ረጅም አመታት የከፋ ጉዳት ሲያደርስባት የነበረውን
ድርቅና ረሃብ ከአለም አቀፍ ተባባሪዎች ጋር በመሆን በተሳካ መልኩ መቋቋም መቻሏ ለሌሎች ሀገራትም ምሳሌ ያደርጋታል
ብሏል::
ከከባቢ አየር ለውጥ ጋር ለሚተሳሰሩ አደጋዎች ያላትን ተጋላጭነት በተሳካ መልኩ መቋቋም በመቻል ረገድም ሁነኛ አብነቶች ማቅረብ የምትችል ሀገር ነች ብሏል ቡድኑ::
የህብረቱ የሰብአዊና የምግብ እርዳታ ሊቀመንበር ዴቪድ ብረክ በሌሎች አገሮች ስራ ላይ መዋል የሚችሉ ምርጥ ልምዶችን ከኢትዮጵያ ጉብኝታቸው እንደሚያገኙ እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል::
ይህንኑ ለማሳካት ቡድኑ በድሬዳዋና አካባቢው የአደጋ ተጋላጭነትን ለመከላከል የተሰሩ ስራዎችን እንደሚጎበኝ ተናግረዋል::
የህብረቱ
የልማት ትብብር ማስተባበሪያ ሊቀመንበር ሲራ ኦብራየን በበኩላቸዉ ኢትዮጵያ እንደ ፈረንጆቹ በ2011 በምስራቅ
አፍሪካ ያጋጠመውን ድርቅና ተጋላጭነት የተቋቋመችበትን ስኬታማ ስልት የተቀናጀ የአደጋ ጌዜ ምላሽ ስርአት የመኖሩ
ማሳያ አድርገውታል::
ኢትዮጵያ ፈጠራ የታከለበት የተቀናጀ አሰራር ባትዘረጋ ኖሮ በቀጠናው በ60 አመት ውስጥ ተከስቶ የማያውቀውን አስከፊ የርሀብ አደጋ በተሳካ መልኩ መቋቋም አትችልም ነበር ብለዋል ሲራ ኦብራየን ::
የልምድ ልውውጡ እየተካሄደ ያለው የአውሮፓ ህብረት እና የአየርላንድ መንግስት ባደረጉት ድጋፍ ነዉ::
|
No comments:
Post a Comment