Saturday, March 9, 2013

ሰቀቀን ጎረሳት


ተወልዳ
በፍዳ
በናቷ ጡት አድጋ

የ አያት ምርቃት
የቤተሰብ ጭንቀት

የጓደኛ ምስጥር
የስብና ክብር

የንሰሀ ስብከት
የፅድቅ አገልግሎት

ስለጎደለባት ለመናገር ፈርታ
ሰቀቀን ጎረሳት መነሻዋን ረስታ።    

No comments: