Wednesday, March 13, 2013

የሜጋ ፕሮጀክቶች ዘመን

የሜጋ ፕሮጀክቶች ዘመን
መግቢያ
 ሃገራችን ኢትዮጵያ መንግስት በነደፋቸዉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በመመራት ከድህነት ጋር ባደረገችዉ ትንቅንቅ ላለፉት 10 ዓመታት ባለ ሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገብ ችላለች፡፡ ይህንኑ እድገት ለማስቀጠል እና ከድህነት ተስፈንጥራ በመዉጣት መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ ከ2003 ጀምሮ እስከ 2007 እ.ኢ.አ ተግባራዊ የሚሆን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ነድፋ በመንቀሳቀስ ላይ ናት፡፡
በዚህ ድህነትን ተረት ለማድረግ በተጀመረዉ ፍልሚያ ትላልቅ ወሳኝ ፕሮጀክቶች (ሜጋ ፕሮጀክቶች) ተነድፈዉ ባለፉት ሁለት አመታት ዉስጥ በተያዘላቸዉ እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ ናቸዉ፡፡ ከነዚህም ሜጋ ፕሮጀክቶች ዉስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
1.ባቡር-   የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ከመቶ አመታት በላይ ታሪክ ያለው ቢሆንም ዘርፉ ያለምንም ለውጥ እስከዛሬ ዘልቋል። በተነደፈው የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለሀገራዊ የባቡር ኔት-ዎርክ ዝርጋታ ትኩረት ተሰጥቶት ሀገሪቱን የሚያገናኙ የባቡር መስመሮች በ3 ኮሪደሮችና በ5 መስመሮች ለመዘርጋት የታቀደ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማም ከሰሜን ደቡብ ከምዕራብ ምስራቅ አቅጣጫ የቀላል ባቡር ዝርጋታ ግንባታ ተጀምሯል፡፡
-ከአዲስ አበባ -ድሬዳዋ-ደወሌ 656 ኪ.ሜ
-ከአዋሽ-ወልዲያ-መቀሌ 556.2 ኪ.ሜ
-ከወልዲያ-ሰመራ-ጋላፊ 256.4 ኪ.ሜ
-ከአ/አበባ-ኢጃጂ-ጂማ-በደሌ 339.3 ኪ.ሜ
-ከሞጆ-ኮንሶ-ወዪጦ 587 ኪ.ሜ
-በአዲስ አበባ ከተማ ከምስራቅ ወደ ምዕራብና ከሰሜን ወደ ደቡብ 34 ኪ.ሜ ቀላል የባቡር መስመር ግንባታ ይከናወናል፡፡ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ግንባታ ከ150 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅ ከሚኖረው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በተጨማሪ በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩ ዜጎች በግንባታ ወቅትና ከግንባታ በኋላ የስራ እድል እንደሚፈጥር ግልጽ ነው።
 

No comments: