Saturday, March 9, 2013

የእናቴ ጎጆ


አያቴ በዕድሜዉ ለኛ ያወረሰዉ
   ከሰዉ ልምድ ተጋርቶ
   እንጎቻ አ ንጉቶ
   በዕድሜ ዘመኑ ለኛ ያወረሰዉ
   እኛ የማንኖርበት አንድ ጎጆ አለዉ።

   ዝናብ ዉሽንፍሩ
    በፀሐይ ሀሩሩ
    በመንገድ ስንቀዋለል
    ታች ላይ ስባትል
    መግቢያ ጠፍቶኝ እንዳይመስልሽ
                                       መታረዘ ታይቶሽ።
    


 ጎዳና መቅረተን ምስጥሩን ልንገርሽ?
     ጎጆ አልባነተን የልበን ላዋይሽ?



   የነገርኩሽ አያቴ ለኛ ያወረሰዉ
   ባለ አንድ ሰቀላ ሁለት መግቢያ ያለዉ
   ለያንዳንዱ ክፍል አንድ መስኮት አለዉ
   የሚገባበት የሚወጣበት አስር መግቢያም አለዉ።

   አያቴ በሞቱ ሌት ሳይናዘዝ ብሞት
   የነበረን ፍቅር መተሳሰብ ርቆን
   አንተ ታንስ እኔ እበልጥ እየተባባልን
   የ አያተን አንድ ሰቀላ ለሁለት ከፈልን።
   አጎቴ አንዱን ክፍል የራሳቸዉ አድርገዉት
   የናቴን ለመንጠቅ ሌት ተቀን ስቃጡት
   ላስራ ሰባት ቀናት በጸብና ቅናት
   መፋቀሩ ቀርቶ ባይን በመገለማመጥ
   ዳግም ላይተያዩ መተላለፊያዉን ዘጉት
   አጎቴ ወድያዉኑ የቤቱን ግድግዳ
   አድስ ቀለም ቀቡት ከሳሎኑም ጓዳ።

   የናቴ መቃተት
   ዘዉትር መንከራተት
   ቆይታዉ አልፎላት
   የማህጸኗ ኗሪ ለወረት አድገዉላት
   ጭንቋን አባባሱት
    እያንዳንዱን ክፍል ልወርሱ ጠየቋት።

   ይሄ ነዉ ታርኩ
          የኔ ጎጆ አልባነት
          የኔ ወፍ ዘራሽነት
          መጠልያ አጥቸ እንድህ መንከራተት።

  የናቴ ወንድሞች
  የናቴ ልጆች
  አድርባይ ታጋዮች

  ላያፈቅሩ እንፋቀር የምሉ
  ላያከብሩን እንከባበር የምሉ
  መልክ የምቀያይሩ እስ ስቶችም አሉ።
  እስከዛሬ ድረስ ባፌ የምያወራዉ
  ለሰፈርቴኛዉ የልበን የምያዋየዉ
  የዘመመችዉን ጎጆ ለማያድሱ ለናቴ ልጆች
  በዘመመዉ ጎጆ የዘመመ ህይወት መሪዎች።

  አያቴ በዕድሜዉ ለኛ ያወረሰዉ
  አንዱ ሰቀላ ባለሁለት መዉጪያ ነዉ
  ዙርያዉን የተሰካ አስር መስኮት አለዉ

  ደስ የምለኝ

  የናቴን ጎጆ ልዩ የምያደርገዉ
  ሳሎኑ አድሳባ
  የታችኛዉ በር ባዋሳ
  የግራዉ መስኮቱ ባሶሳ
  የፀሐይ መግብያዉ በድሬ ብር
  የመታጠብያኡው ባዝ ከዉቧ ባህርዳር

  ጅግጅጋ፣ ሰመራ፣ ጋምበላ፣ አዳማና ሐረር
  የናቴ ጎጆ ሞጎስና ክብር
  ያያቴ ዉርስ የናቴ አንጡር።

  ሁለት መግቢያ ኖሮት
  ከማስወጣት በቀር ማስገባት ተስኖት
  እናቴን ለልመና እኔን ለጎዳ
  እርካታን አገኙ ለዥ ዳረጉና።

  ይህን የምልሽ
            ጎጆ አልባነት
            ወፍ ዘራሸንት
            የለማኝ ልጅነት
            ዘዉትር ተመጸዋችነት
        ሌላ እንዳይመስልሽ
        ያልኩሽን ከሰማሽ
       
        የናቴ ልጆች
        የለማኟ ልጆች
        የዘመመ ጎጆ ለመቀራመት
        ለኔም ጎጆ አልባነት
        እልፍ አእላፍ እያሉ
        ህዝብ ያታልላሉ

        የናቴ ወንድሞች
        የናቴ ልጆች
        አድርባይ ታጋዮች.....
       

        አያቴ በሞቱ ለኛ ያወረሰዉ
        እኛ የማንኖርበት አንድ ጎጆ አለዉ.........xayouluma

No comments: