Saturday, March 9, 2013

ክቧ አምባሳደርበሜዳ ተመተሽ
ሳሎን ተንከባለሽ
ለፍቅር ለሰላም መስዋዕት የከፈልሽ
በሰባቱ አህጉራት በእህጩነት ያለፍሽ
አንች ክቧ መሪ አምባሳደርም ነሽ።

ጥላቻን አስወግደሽ
እንድህ ተንከባለሽ

ጋሀንዲ ነሽ ማንደላ
ማርቲን ነሽ ወይ ሌላ።

ዚዙ ወይስ ጎቾ ፐሌ ማራዶና
ፀብን በማስወገድ ምበልጡሽ በዝና።

የነፃነት ተምሳለት የሰላም አምባሳደር
ሁሉም በየፊናዉ ስላንች ይዘምር
እንፎክር ይፎከር
ይዘፈን ይዘመር
ነፃነት ላመጣች ለክቧ አምባሳደር።
xayouluma

No comments: